1 ULB በእግዚአብሔር ፈቃድ ሐዋርያ ሊሆን በክርስቶስ ኢየሱስ የተጠራ ጳውሎስና ወንድማችን ሶስቴንስ በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት። BSB BSB: Paul, called to be an apostle of Christ Jesus by the will of God, and our brother Sosthenes,
2 ULB የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት ደግሞ እንጽፍላቸዋለን። BSB BSB: To the church of God in Corinth, to those sanctified in Christ Jesus and called to be holy, together with all those everywhere who call on the name of our Lord Jesus Christ, their Lord and ours:
3 ULB ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። BSB BSB: Grace and peace to you from God our Father and the Lord Jesus Christ.
4 ULB ክርስቶስ ኢየሱስ ከሰጣችሁ ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ሁልጊዜ ስለእናንተ አምላኬን አመሰግናለሁ። BSB BSB: I always thank my God for you because of the grace He has given you in Christ Jesus.
5 ULB በነገር ሁሉ፤በንግግርና በዕውቀት ሁሉ ባለጸጋ እንድትሆኑ አድርጎአችኋልና። BSB BSB: For in Him you have been enriched in every way, in all speech and all knowledge,
6 ULB ስለክርስቶስ የተሰጠው ምስክርነት በመካከላችሁ እውነት ሆኖ እንደጸና ሁሉ ባለጸጎች አድርጎአችኋል። BSB BSB: because our testimony about Christ was confirmed in you.
7 ULB ስለዚህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ በጉጉት ስትጠባበቁ አንድም መንፈሳዊ ስጦታ አይጎድልባችሁም። BSB BSB: Therefore you do not lack any spiritual gift as you eagerly await the revelation of our Lord Jesus Christ.
8 ULB እርሱ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል። BSB BSB: He will sustain you to the end, so that you will be blameless on the day of our Lord Jesus Christ.
9 ULB ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው። BSB BSB: God, who has called you into fellowship with His Son Jesus Christ our Lord, is faithful.
11 ULB በመካከላችሁ መከፋፈል እንደተፈጠረ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛል። BSB BSB: My brothers, some from Chloe’s household have informed me that there are quarrels among you.
12 ULB ይህን የምላችሁ፦ እያንዳንዳችሁ፦ "እኔ ከጳውሎስ ጋር ነኝ፥ ወይም ከአጵሎስ ጋር ነኝ፤ ወይም እኔ ከኬፋ ጋር ነኝ፤ ወይም እኔ ከክርቶስ ጋር ነኝ" ትላላችሁ። BSB BSB: What I mean is this: Individuals among you are saying, “I follow Paul,” “I follow Apollos,” “I follow Cephas,” or “I follow Christ.”
13 ULB ለመሆኑ ክርስቶስ ተከፍሎአልን? ጳውሎስስ ስለ እናንተ ተሰቅሎአልን? ወይም የተጠመቃችሁት በጳውሎስስ ስም ነውን? BSB BSB: Is Christ divided? Was Paul crucified for you? Were you baptized into the name of Paul?
14 ULB ከቀርስጶስና ከጋይዮስ በቀር ማናችሁንም ስላላጠመቅሁ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። BSB BSB: I thank God that I did not baptize any of you except Crispus and Gaius,
15 ULB ስለዚህ ማናችሁም በእኔ ስም እንደተጠመቃችሁ ለመናገር አትችሉም። (የእስጢፋኖስን ቤተ ሰብ ደግሞ አጥምቄአለሁ። BSB BSB: so no one can say that you were baptized into my name.
16 ULB ከዚህ ውጪ ሌላ ማንን አጥምቄ እንደሆነ አላውቅም።) BSB BSB: Yes, I also baptized the household of Stephanas; beyond that I do not remember if I baptized anyone else.
17 ULB ክርስቶስ ወንጌልን እንድሰብክ እንጂ እንዳጥምቅ አላከኝም። በሰው ጥበብ እንድሰብክ አልላከኝም፤ እንዲሁም የክርስቶስ መስቀል ኃይሉ ከንቱ መሆን ስለሌለበት በሰው የንግግር ጥበብ አልሰብክም። BSB BSB: For Christ did not send me to baptize, but to preach the gospel, not with words of wisdom, lest the cross of Christ be emptied of its power.
19 ULB "የጥበበኖችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል ከንቱ አደርጋለሁ" ተብሎ ተጽፎአልና። BSB BSB: For it is written: “I will destroy the wisdom of the wise; the intelligence of the intelligent I will frustrate.”
21 ULB ዓለም በጥበብዋ እግዚአብሔርን ስላላወቀች በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖአል። BSB BSB: For since in the wisdom of God the world through its wisdom did not know Him, God was pleased through the foolishness of what was preached to save those who believe.
22 ULB አይሁድ ታዓምራትን ይፈልጋሉ፤ የግሪክ ሰዎችም ጥበብን ይሻሉ። BSB BSB: Jews demand signs and Greeks search for wisdom,
24 ULB ነገር ግን እግዚአብሔር ለጠራቸው ለአይሁዶችም ሆነ ለግሪክ ሰዎች የእግዚአብሔር ኃይልና ጥበብ የሆነውን ክርስቶስን እንሰብካለን። BSB BSB: but to those who are called, both Jews and Greeks, Christ the power of God and the wisdom of God.
25 ULB ምክንያቱም የእግዚአብሔር ሞኝነት የሚመስለው ነገር ከሰዎች ጥበብ ይበልጣል፤ እንዲሁም የእግዚአብሔር ድካም የሚመስለው ነገር ከሰዎች ብርታት ይበልጣል። BSB BSB: For the foolishness of God is wiser than man’s wisdom, and the weakness of God is stronger than man’s strength.
26 ULB ወንድሞችና እህቶች ሆይ፤ በእናንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ጥሪ ተመልከቱ። ብዙዎቻችሁ በሰው መስፈርት ጥበበኞች አልነበራችሁም። ብዙዎቻችሁ ኃያላን አልነበራችሁም፤ ብዙዎቻችሁም ከመሳፍንት አልነበራችሁም። BSB BSB: Brothers, consider the time of your calling: Not many of you were wise by human standards; not many were powerful; not many were of noble birth.
27 ULB ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ያሳፍር ዘንድ የዓለምን ሞኝ ነገር መረጠ። ብርቱንም ነገር ለማሳፈር የዓለምን ደካማ ነገር መረጠ። BSB BSB: But God chose the foolish things of the world to shame the wise; God chose the weak things of the world to shame the strong.
28 ULB ዓለም እንደ ከበረ ነገር የምትቆጥረውን ከንቱ ለማድረግ እግዚአብሔ የዓለምን ምናምንቴ ነገር መረጠ። የተናቀውንና ያልሆነውን ነገር መረጠ። BSB BSB: He chose the lowly and despised things of the world, and the things that are not, to nullify the things that are,
29 ULB ይህን ያደረገው ማንም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመመካት ምክንያት እንዳይኖረው ነው። BSB BSB: so that no one may boast in His presence.
30 ULB በክርስቶስ ኢየሱስ ለመሆን የበቃችሁት ከእግዚአብሔር ሥራ የተነሳ ነው፤ እርሱም ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፤ጽድቃችንና ቅድስናችን ቤዛችንም ሆኖአልና። BSB BSB: It is because of Him that you are in Christ Jesus, who has become for us wisdom from God: our righteousness, holiness, and redemption.
31 ULB እንግዲህ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ ፦"የሚመካ በጌታ ይመካ" ነው። BSB BSB: Therefore, as it is written: “Let him who boasts boast in the Lord.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.