2 ULB የሰበክሁላችሁን ቃል አጥብቃችሁ ብትይዙ፣በዚህ ወንጌል መዳን ይሆንላችኋል፣አለዚያ ግን ማመናችሁ ምንም ጥቅም የለውም። BSB BSB: By this gospel you are saved, if you hold firmly to the word I preached to you. Otherwise, you have believed in vain.
4 ULB ተቀበረ፣ በሦስተኛውም ቀን ተነሳ፣መጽሐፍትም ይህን ያረጋግጣሉ። BSB BSB: that He was buried, that He was raised on the third day according to the Scriptures,
5 ULB ለኬፋ ታየ፣ከዚያም ለእሥራ ሁለቱ። BSB BSB: and that He appeared to Cephas and then to the Twelve.
7 ULB ከዚያም ለያዕቆብ፣ደግሞም ለሐዋርያቱ ሁሉ ታየ። BSB BSB: Then He appeared to James, then to all the apostles.
8 ULB ከሁሉም በኋላ፣ያለ ጊዜው እንደተወለደ ልጅ ለሆንሁት ለእኔ ታየ። BSB BSB: And last of all He appeared to me also, as to one of untimely birth.
9 ULB ከሐዋርያት ሁሉ የማንስ ነኝና። የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን አሳድጃለሁና ሐዋርያ ተብዬ ልጠራ አይገባኝም። BSB BSB: For I am the least of the apostles and am unworthy to be called an apostle, because I persecuted the church of God.
10 ULB ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ የሆንሁትን ሆኜአለሁ፣በእኔ ውስጥ የነበረው ጸጋም በከንቱ አልነበረም። ይልቁን ከሁሉም በላይ ጠንክሬ ሠራሁ። ሆኖም ይህ የሆነው ከእኔ ሳይሆን ከእኔ ጋር ካለው የእግዚአብሔር ጸጋ የተነሳ ነው። BSB BSB: But by the grace of God I am what I am, and His grace to me was not in vain. No, I worked harder than all of them—yet not I, but the grace of God that was with me.
13 ULB ሙታን ትንሣኤ ከሌለ እንግዲያው ክርስቶስም ከሙታን አልተነሳማ። BSB BSB: If there is no resurrection of the dead, then not even Christ has been raised.
15 ULB እንግዲህ እኛም ስለ እግዚአብሔር የሐሰት ምስክሮች ሆነን ተገኝተናል፣ ምክንያቱም እርሱ ክርስቶስን ሳያስነሳ እኛ አስነስቶታል በማለታችን በእግዚአብሔር ላይ በሐሰት መስክረንበታል። BSB BSB: In that case, we are also exposed as false witnesses about God. For we have testified about God that He raised Christ from the dead, but He did not raise Him if in fact the dead are not raised.
16 ULB ሙታን ካልተነሱ፣ክርስቶስም አልተነሳም ማለት ነው። BSB BSB: For if the dead are not raised, then not even Christ has been raised.
17 ULB ክርስቶስ ካልተነሳ ደግሞ፣ እምነታችሁ ምንም ዋጋ የለውምናም አሁንም በኃጢአታችሁ አላችሁ። BSB BSB: And if Christ has not been raised, your faith is futile; you are still in your sins.
18 ULB ስለዚህ በክርስቶስ ሆነው የሞቱ ደግሞ ጠፍተዋል ማለት ነው። BSB BSB: Then those also who have fallen asleep in Christ have perished.
19 ULB ክርስቶስ ተስፋ ያደረግነው ለዚህ ሕይወት ብቻ ከሆነ፣ከሰዎች ሁሉ ይልቅ የምናሳዝን ነን። BSB BSB: If our hope in Christ is for this life alone, we are to be pitied more than all men.
22 ULB በአዳም ሁሉም እንደሞቱ፣ሁሉም ደግሞ በክርስቶስ ሕያው ይሆናሉ። BSB BSB: For as in Adam all die, so in Christ all will be made alive.
23 ULB ግን እያንዳንዱ በቅደም ተከተሉ መሠረት፦ ክርስቶስ በኩር፣ ቀጥሎ የክርስቶስ የሆኑት እርሱ ተመልሶ ሲመጣ ሕያዋን ይሆናሉ። BSB BSB: But each in his own turn: Christ the firstfruits; then at His coming, those who belong to Him.
24 ULB ከዚያም ክርስቶስ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር አብ ሲያስረክብ ፍጻሜ ይሆናል። ይህም የሚሆነው ግዛትን ሁሉ፣ ሥልጣንን ሁሉ፣ እና ኃይልን ሁሉ ሲደመስስ ነው። BSB BSB: Then the end will come, when He hands over the kingdom to God the Father after He has destroyed all dominion, authority, and power.
25 ULB ጠላቶቹን ሁሉ ከእግሮቹ ስር እስኪያደርግ ድረስ ሊነግሥ ይገባዋል። BSB BSB: For He must reign until He has put all His enemies under His feet.
26 ULB ሊደመሰስ የሚገባው የመጨረሻው ጠላት ሞት ነው። BSB BSB: The last enemy to be destroyed is death.
27 ULB "ሁሉን ከእግሮቹ በታች አደረገ።" ነገር ግን፣"ሁሉን አደረገ፣" ሲል፣ሁሉን እንዲገዛለት ያደረገውን እንደማይጨምር ግልጽ ነው። BSB BSB: For “God has put everything under His feet.” Now when it says that everything has been put under Him, this clearly does not include the One who put everything under Him.
28 ULB ሁሉም ሲገዛለት፣ ልጁ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ለእርሱ ይገዛል። ይህ የሚሆነው እግዚአብሔር አብ ሁሉ በሁሉ እንዲሆን ነው። BSB BSB: And when all things have been subjected to Him, then the Son Himself will be made subject to Him who put all things under Him, so that God may be all in all.
29 ULB አለበዚያ ግን፤ ስለ ሙታን የሚጠመቁ ሰዎች ለምን ያደርጉታል? ሙታን ፈጽሞ የማይነሱ ከሆነ፣ስለምን ያጠምቁላቸዋል? BSB BSB: If these things are not so, what will those do who are baptized for the dead? If the dead are not raised at all, why are people baptized for them?
30 ULB ስለምንስ በየሰዓቱ አደጋ ውስጥ እንወድቃለን? BSB BSB: And why do we endanger ourselves every hour?
31 ULB ወንድሞች እና እህቶች፣ ስለ እናንተ በክርስቶስ ባለኝ ትምክህት ይህን እናገራለሁ፦ በየቀኑ እሞታለሁ። BSB BSB: I face death every day, brothers, as surely as I boast about you in Christ Jesus our Lord.
32 ULB በሰው ዓይን ሲታይ፣ በኤፌሶን ከአውሬዎች ጋር መጋደሌ፣ ሙታን የማይነሱ ከሆነ ምን ይጠቅመኛል? "ነገ መሞታችን ስለማይቀር፣እንብላ፣ እንጠጣ።" BSB BSB: If I fought wild beasts in Ephesus for human motives, what did I gain? If the dead are not raised, “Let us eat and drink, for tomorrow we die.”
33 ULB አትታለሁ፦ "መልካም ያልሆነ ግንኙነት መልካሙን ጠባይ ያበላሻል።" BSB BSB: Do not be deceived: “Bad company corrupts good character.”
34 ULB ራሳችሁን ተቆጣጠሩ! የጽድቅ ሕይወት ኑሩ! ኃጢአት ማድረግን አትቅጠጥሉ። አንዳንዶቻችሁ ስለ እግዚአብሔር ዕውቀት የላችሁም። ይህን የምላችሁ ላሳፍራችሁ ነው። BSB BSB: Sober up as you ought, and stop sinning; for some of you are ignorant of God. I say this to your shame.
36 ULB ዕውቀት የጎደላችሁ ናችሁ! የዘራችሁት ዘር ካልሞተ አይበቅልም። BSB BSB: You fool! What you sow does not come to life unless it dies.
37 ULB የዘራችሁት አካል ተምልሶ አይበቅልም፣ይልቁን ዘር ነው እንጂ። ስንዴ ወይም የተዘራውን ሌላ ዓይነት ዘር ሆኖ ይበቅላል። BSB BSB: And what you sow is not the body that will be, but just a seed, perhaps of wheat or something else.
38 ULB እግዚአብሔር እንደወደደ አካልን ይሰጠዋል፣ለእያንዳንዱም ዘር የራሱን አካል ይሰጠዋል። BSB BSB: But God gives it a body as He has designed, and to each kind of seed He gives its own body.
39 ULB ሥጋ ሁሉ አንድ ዓይነት አይደለም። ይልቁን፣ የሰው ሥጋ አለ፣ እንዲሁም የእንሰሳት ሥጋ አለ፣ የአእዋፍት ሥጋም እንዲሁ፣ ዓሣም ደግሞ ሌላ ዓይነት ሥጋ አለው። BSB BSB: Not all flesh is the same: Men have one kind of flesh, animals have another, birds another, and fish another.
40 ULB እንዲሁም ደግሞ ሰማያዊ አካልና ምድራዊ አካል አለ። ነገር ግን የሰማያዊ አካል ክብር አለ የምድራዊ አካል ክብር ደግሞ ሌላ ነው። BSB BSB: There are also heavenly bodies and earthly bodies. But the splendor of the heavenly bodies is of one degree, and the splendor of the earthly bodies is of another.
41 ULB የፀሐይ ክብር አለ፣ የጨረቃ ክብር ደግሞ ሌላ ነው፣ ከዋክብት ደግሞ ሌላ ክብር አላቸው። የአንዱ ኮከብ ክብር ከሌላው ኮከብ ይለያል። BSB BSB: The sun has one degree of splendor, the moon another, and the stars another; and star differs from star in splendor.
43 ULB ሲዘራ በውርደት ሲነሳ ግን በክብር ነው። ሲዘራ በድካም፣ሲነሳ ግን በኃይል ነው። BSB BSB: It is sown in dishonor; it is raised in glory. It is sown in weakness; it is raised in power.
44 ULB የተዘራው ፍጥረታዊ አካል፣የሚነሳው ግን መንፈሳዊ አካል ነው። ፍጥረታዊ አካል እንዳለ ሁሉ መንፈሳዊ አካልም አለ። BSB BSB: It is sown a natural body; it is raised a spiritual body. If there is a natural body, there is also a spiritual body.
45 ULB እንዲህም ተብሎ ተጽፎአል፣ "የመጀመሪያው አዳም ሕያው ነፍስ ሆነ።" የመጨረሻው አዳም ግን ሕይወት ሰጭ መንፈስ ሆነ። BSB BSB: So it is written: “The first man Adam became a living being”; the last Adam a life-giving spirit.
46 ULB መጀመሪያ የመጣው መንፈሳዊው ሳይሆን ፍጥረታዊው ነው፣ከዚያም መንፈሳዊው ተከተለ። BSB BSB: The spiritual, however, was not first, but the natural, and then the spiritual.
47 ULB የመጀመሪያው ሰው ከምድር ሲሆን የተሠራውም ከአፈር ነው። ሁለተኛው ሰው ከሰማይ ነው። BSB BSB: The first man was of the dust of the earth, the second man from heaven.
48 ULB አንዱ ከአፈር እንደተሠራ፣ከአፈር የተሠሩ ሁሉ እንዲሁ ናችው። እንዲሁም ከሰማይ እንደሆነው ሰው፣ ከሰማይ የሆኑትም እንዲሁ ናቸው። BSB BSB: As was the earthly man, so also are those who are of the earth; and as is the heavenly man, so also are those who are of heaven.
49 ULB ልክ እኛ ከአፈር የተሠራውን ሰው እንደምንመስል፣ እንዲሁ ደግሞ የሰማዩን ሰው መልክ እንይዛለን። BSB BSB: And just as we have borne the likeness of the earthly man, so also shall we bear the likeness of the heavenly man.
50 ULB ወንድሞች እና እህቶች፣ አሁን እንዲህ እላለሁ፣ሥጋ እና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርስ አይችልም። እንዲሁም የሚጠፋው የማይጠፋውን ሊወርስ አይችልም። BSB BSB: Now I declare to you, brothers, that flesh and blood cannot inherit the kingdom of God, nor does the perishable inherit the imperishable.
51 ULB ምስጢር የሆነ እውነት እነግራችኋለሁ፦ ሁላችን አንሞትም፣ግን ሁላችን እንለወጣለን። BSB BSB: Listen, I tell you a mystery: We will not all sleep, but we will all be changed—
52 ULB የመጨረሻው መለከት ሲነፋ፣ዐይን ተጨፍኖ እስኪገለጥ ባለ ፍጥነት ድንገት እንለወጣለን። መለከቱ ሲነፋ፣ ሙታን የማይጠፋውን አካል ለብሰው ይነሳሉ፣ እኛም እንለወጣለን። BSB BSB: in an instant, in the twinkling of an eye, at the last trumpet. For the trumpet will sound, the dead will be raised imperishable, and we will be changed.
53 ULB ይህ የሚጠፋው የማይጠፋውን ይለብሳል፣ ሟቹ ደግሞ የማይሞተውን ይለብሳል። BSB BSB: For the perishable must be clothed with the imperishable, and the mortal with immortality.
54 ULB የሚጠፋው የማይጠፋውን ሲለብስ፣እና ይህ ሟች የሆነው የማይሞተውን ሲለብስ፣ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ይፈጸማል፣"ሞት በድል ተዋጠ።" BSB BSB: When the perishable has been clothed with the imperishable and the mortal with immortality, then the saying that is written will come to pass: “Death has been swallowed up in victory.”
55 ULB ሞት ሆይ ድል ማድረግህ የት አለ? ሞት ሆይ መንደፊያህ የት አለ?" BSB BSB: “Where, O Death, is your victory? Where, O Death, is your sting?”
56 ULB የሞት መንደፊያ ኃጢአት ነው፣ የኃጢአት ኃይል ደግሞ ሕጉ ነው። BSB BSB: The sting of death is sin, and the power of sin is the law.
57 ULB ነገር ግን በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ ድል የሚሰጠን እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! BSB BSB: But thanks be to God, who gives us the victory through our Lord Jesus Christ!
58 ULB ስለዚህ ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣ የጸናችሁ እና የማትነቃነቁ ሁኑ። ሁልጊዜም የእግዚአብሔር ሥራ ይብዛላችሁ፣ምክንያቱም በጌታ የምትደክሙት ድካም በከንቱ አይደለም። BSB BSB: Therefore, my beloved brothers, be steadfast and immovable. Always excel in the work of the Lord, because you know that your labor in the Lord is not in vain.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.