3 ULB ኢየሱስን የማይቀበል መንፈስ ሁሉ ከእግዚአብሔር አይደለም። ይህ እንደሚመጣ የሰማችሁት የክርስቶስ ተቃዋሚው መንፈስ ነው፣ አሁን እንኳ በዓለም ውስጥ አለ፡፡ BSB BSB: and every spirit that does not confess Jesus is not from God. This is the spirit of the antichrist, which you have heard is coming and which is already in the world at this time.
4 ULB የተወደዳችሁ ልጆች! እናንተ ከእግዚአብሔር ስለሆናችሁ፣ እነዚህን መናፍስት አሸንፋችኋል፣ ምክንያቱም በዓለም ካለው ይልቅ በእናንተ ያለው ይበልጣል፡፡ BSB BSB: You, little children, are from God and have overcome them, because greater is He who is in you than he who is in the world.
5 ULB እነዚህ መናፍስት ከዓለም ናቸው፣ስለሆነም የሚናገሩት ሁሉ የዓለምን ነው፣ዓለምም ይሰማቸዋል፡፡ BSB BSB: They are of the world. That is why they speak from the world’s perspective, and the world listens to them.
6 ULB እኛ ከእግዚአብሔር ነን። እግዚአብሔርን የሚያውቅ ይሰማናል። ከእግዚአብሔር ያልሆነ ግን አይሰማንም። በዚህም የእውነት መንፈስንና ፣የስህተትን መንፈስን እናውቃለን፡፡ BSB BSB: We are from God. Whoever knows God listens to us; whoever is not from God does not listen to us. That is how we know the Spirit of truth and the spirit of deception.
7 ULB ወዳጆች ሆይ! እርስ በርስ እንዋደድ፣ምክንያቱም ፍቅር ከእግዚአብሔር ነውና፣ ፍቅር ያለው ከእግዚአብሔር ተወልዷል፣ እግዚአብሔርንም ያውቃል፡፡ BSB BSB: Beloved, let us love one another, because love comes from God. Everyone who loves has been born of God and knows God.
10 ULB ፍቅር እንደዚህ ነው፣እግዚአብሔርን ስለወደድነው ሳይሆን፣ እርሱ ስለወደደን ለኃጢያታችን ማስተሰረያ እንዲሆን ልጁን ላከ፡፡ BSB BSB: And love consists in this: not that we loved God, but that He loved us and sent His Son as the atoning sacrifice for our sins.
11 ULB ወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔር ይህን ያህል ከወደደን፣እኛም እርስ በርሳችን መዋደድ ይገባናል። BSB BSB: Beloved, if God so loved us, we also ought to love one another.
12 ULB ማንም እግዚአብሔርን አላየውም። እርስ በርሳችን ብንዋደድ፣ እግዚአብሔር በኛ ይኖራል፣ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል፡፡ BSB BSB: No one has ever seen God; but if we love one another, God remains in us, and His love is perfected in us.
13 ULB መንፈሱን ሰጥቶናልና፣ በዚህም እኛ በእርሱ እንደምንኖር፣ እርሱም በኛ እንደሚኖር እናውቃለን። BSB BSB: By this we know that we remain in Him, and He in us: He has given us of His Spirit.
14 ULB እኛም አይተናል፣እግዚአብሔር ልጁን የዓለም አዳኝ አድርጐ እንደላከውም እንመሰክራለን፡፡ BSB BSB: And we have seen and testify that the Father has sent His Son to be the Savior of the world.
15 ULB ማንም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ቢቀበል፣ እግዚአብሔር በርሱ ይኖራል ፤እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል፡፡ BSB BSB: If anyone confesses that Jesus is the Son of God, God abides in him, and he in God.
17 ULB በፍርድ ቀን ድፍረት እንዲኖረን፣ይህም ፍቅር በመካከላችን ተፈጸሟል፣ እኛም በዚህ ዓለም እንደ እርሱ ነን፡፡ BSB BSB: In this way, love has been perfected among us, so that we may have confidence on the day of judgment; for in this world we are just like Him.
18 ULB በፍቅር ፍርሃት የለም። ነገር ግን ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል፣ ምክንያቱም ፍርሃት የሚያመለክተው ቅጣት መኖሩን ነው። የሚፈራ ግን ፍቅሩ ፍፁም አይደለም፡፡ BSB BSB: There is no fear in love, but perfect love drives out fear, because fear involves punishment. The one who fears has not been perfected in love.
19 ULB አስቀድሞእግዚአብሔር ወዶናልና፣እኛም እንወደዋለን። BSB BSB: We love because He first loved us.
20 ULB አንድ ሰው "እግዚአብሔርን እወዳለሁ" እያለ ወንድሙን ግን ቢጠላ ሃሰተኛ ነው፤የሚያየውን ወንድሙን የማይወድ፣ የማያየውን እግዚአብሔርን ሊወድ አይችልም። BSB BSB: If anyone says, “I love God,” but hates his brother, he is a liar. For anyone who does not love his brother, whom he has seen, cannot love God, whom he has not seen.
21 ULB እግዚአብሔርን የሚወድ ወንድሙን መውደድ አለበት፣የሚል ትእዛዝ ከእግዚአብሔር ተቀብለናል። BSB BSB: And we have this commandment from Him: Whoever loves God must love his brother as well.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.