1 ULB ከብዙ ጊዜ በኋላ በሦስተኛው ዓመት የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ እንዲህ ሲል መጣ፡- ሄደህ ራስህን ለንገሥ አከዓብ ግለጥለት እኔም በምድር ላይ ዝናብን አዘንባለሁ አለው፡፡ BSB BSB: After a long time, in the third year of the drought, the word of the LORD came to Elijah: “Go and present yourself to Ahab, and I will send rain upon the face of the earth.”
2 ULB ኤልያስም በታዘዘው መሠረት ወደ አከዓብ ሄደ፤ በዚህ ጊዜ በሰማርያ ረሃብ እጅግ ጸንቶ ነበር፡፡ BSB BSB: So Elijah went to present himself to Ahab. The famine was severe in Samaria,
3 ULB ስለዚህ ንጉሥ አክዓብ የቤተ መንግሥቱ ኃላፊ የሆነውን አብድዩን ጠራው፤ አብድዩ እግዚአብሔርን የሚፈራ መንፈሳዊ ሰው ነበር፡፡ BSB BSB: and Ahab summoned Obadiah, who was in charge of the palace. (Now Obadiah greatly feared the LORD,
4 ULB ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ታስገድል በነበረበት ጊዜ አብድዩ አንድ መቶ የሚሆኑትን የእግዚአብሔርን ነቢያት ከሁለት ከፍሎ ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻዎች ከሸሸጋቸው በኋላ እህልና ውሃ በማቅረብ መግቦአቸው ነበር፡፡ BSB BSB: for when Jezebel had slaughtered the prophets of the LORD, Obadiah had taken a hundred prophets and hidden them, fifty men per cave, providing them with food and water.)
5 ULB አከዓብ አብድዩን ፈረሶችንና በቅሎዎችን ከሞት የምናድንበት በቂ ሣር እናገኝ እንደሆን በምድሪቱ ወደሚገኘው ምንጭና ወንዝ እስቲ ሂድና እይ፡፡ ምናልባት እንስሳትን ከሞት ማዳን እንችል ይሆናል አለው፡፡ BSB BSB: Then Ahab said to Obadiah, “Go throughout the land to every spring and every valley. Perhaps we will find grass to keep the horses and mules alive so that we will not have to destroy any livestock.”
6 ULB እያንዳንዳቸው በአገሪቱ ወደየትኛው ክፍል ሄደው መፈለግ እንዳባቸው ከተስማሙ በኋላ አክዓብና አብድዩ ለየብቻቸው በሁለት አቅጣጫ ተሰማሩ፡፡ BSB BSB: So they divided the land to explore. Ahab went one way by himself, and Obadiah went the other way by himself.
7 ULB አብድዩ በሚሄድበት መንገድ ላይ ሳለ በድንገት ኤልያስን አገኘው፤ ኤልያስ መሆኑንም ስላወቀ በግንባሩ ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ከነሣው በኋላ ጌታዬ ኤልያስ በእውነት አንተ ነህን? ሲል ጠየቀው፡፡ BSB BSB: Now as Obadiah went on his way, Elijah suddenly met him. When Obadiah recognized him, he fell facedown and said, “Is it you, my lord Elijah?”
8 ULB ኤልያስም አዎን እኔ ነኝ፤ እዚህ መሆኔን ሄደህ ለጌታህ ንገረው ሲል መለሰለት፡፡ BSB BSB: “It is I,” he answered. “Go tell your master, ‘Elijah is here!’”
9 ULB አብድዩም እንዲህ አለው፤ ንጉሥ አክዓብ እኔን ባሪያህን ይገድለኝ ዘንድ በእጁ አሳልፈህ የምትሰጠኝ ምን በደል ሠርቼ ነው? BSB BSB: But Obadiah replied, “How have I sinned, that you are handing your servant over to Ahab to put me to death?
10 ULB ንጉሡ አንተን ለማግኘት ፈልጎ በዓለም ላይ መልእክተኛ ያልላከበት አገር እንደሌለ በአምላክህ በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ የአንድ አገር መሪ አንተ በአገሩ ውስጥ አለመኖርህን ለንጉሥ አክዓብ በመሐላ እያረጋገጠለት ቆይቶአል፡፡ BSB BSB: As surely as the LORD your God lives, there is no nation or kingdom where my lord has not sent someone to search for you. When they said, ‘He is not here,’ he made that kingdom or nation swear that they had not found you.
11 ULB አሁን አንተ ግን ኤልያስ ተገኝቶአል ብለህ ለጌታህ ንገር ትለኛለህ፡፡ BSB BSB: And now you say, ‘Go tell your master that Elijah is here!’
12 ULB እኔ ከዚህ እንደ ሄድኩ ወዲያውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ አንተን ወዳልታወቀ ቦታ ቢወስድህ እኔ ምን ይበጀኛል? አንተ በዚህ ቦታ መኖርህን ለአከዓብ ነግሬው ሳያገኝህ ቢቀር እኔን በሞት ይቀጣኛል፤ ከልጅነቴ ጀምሬ እግዚአብሔርን የምፈራ ሰው መሆኔን አስታውስ፡፡ BSB BSB: I do not know where the Spirit of the LORD may carry you off when I leave you. Then when I go and tell Ahab and he does not find you, he will kill me. But I, your servant, have feared the LORD from my youth.
13 ULB ደግሞስ ኤልዛቤል የእግዚአብሔርን ነቢያት ስታስገድል በነበረችበት ጊዜ አንድ መቶ የሚሆኑትን ነቢያት ከሁለት በመክፈል ኀምሳ ኀምሳውን በዋሻ ውስጥ ሸሽጌ እህልና ውሃ በማቅረብ ስመግባቸው መኖሬን አልሰማህምን? BSB BSB: Was it not reported to my lord what I did when Jezebel slaughtered the prophets of the LORD? I hid a hundred prophets of the LORD, fifty men per cave, and I provided them with food and water.
14 ULB ታዲያ፣ አሁን አንተ እዚህ መሆንህን ሄደህ ለንጉሥ አክአብ ንገር ትለኛለህን? ይህን ባደርግ ንጉሡ ይገድለኛል!» BSB BSB: And now you say, ‘Go tell your lord that Elijah is here!’ He will kill me!”
15 ULB ኤልያስም «ዛሬ ለንጉሡ እንደምገለጥለት በማገለግለውና ሁሉን ቻይ በሆነው በእግዞአብሔር ስም ቃል እገባልሃለሁ!» ሲል መለሰለት፡፡ BSB BSB: Then Elijah said, “As surely as the LORD of Hosts lives, before whom I stand, I will present myself to Ahab today.”
16 ULB ከዚህ በኋላ አብድዩ ሄዶ ለንጉሥ አክዓብ ነገረው፤ አክዓብም ተነሥቶ ኤልያስን ለመገናኘት ሄደ፤ BSB BSB: So Obadiah went to inform Ahab, who went to meet Elijah.
17 ULB አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜም «በእስራኤል ላይ ይህን ችግር ያመጣህ አንተ እዚህ ነህን?» አለው፡፡ BSB BSB: When Ahab saw Elijah, he said to him, “Is that you, O troubler of Israel?”
18 ULB ኤልያስም እንዲህ ሲል መለሰ፡- «የእግዚአብሔርን ትእዛዛት በመጣስ ባዓል ተብሎ ለሚጠራው የባዕድ አምላክ ምስሎች በመስገድ ችግር የምታመጡ አንተና የአባትህ ቤተ ሰብ ናችሁ እንጂ እኔ በእስራኤል ላይ ችግር የማመጣ አይደለሁም! BSB BSB: “I have not troubled Israel,” Elijah replied, “but you and your father’s house have, for you have forsaken the commandments of the LORD and have followed the Baals.
19 ULB ይልቅስ እስራኤላውያንን ሁሉ እንዳገኛቸው አራት መቶ ሃምሳ የበዓል ነቢያትንና በንግሥት ኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ የኤሼራ ነቢያትን በቀርሜሎስ ተራራ ሰብስብልኝ፡፡» BSB BSB: Now summon all Israel to meet me on Mount Carmel, along with the four hundred and fifty prophets of Baal and the four hundred prophets of Asherah who eat at Jezebel’s table.”
21 ULB ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፡- «እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ እግዚአብሔር እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!» አላቸው፡፡ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም፡፡ BSB BSB: Then Elijah approached all the people and said, “How long will you waver between two opinions? If the LORD is God, follow Him. But if Baal is God, follow him.” But the people did not answer a word.
22 ULB ከዚህ በኋላ ኤልያስ እንዲህ አለ፡- «ከእግዚአብሔር ነቢያት የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፡፡ አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያት ግን እነሆ በዚህ አሉ፡፡ BSB BSB: Then Elijah said to the people, “I am the only remaining prophet of the LORD, but Baal has four hundred and fifty prophets.
23 ULB እንግዲህ ሁለት ኮርማዎችን አምጡና የባዓል ነቢያት አንዱን ወስደው ይረዱት፤ ሥጋውንም ቆራርጠው እንጨት በመረብረብ በዚያ ላይ ያኑሩት፤ ነገር ግን እሳት አያድርጉበት፡፡ እኔም ሁለተኛውን ኮርማ ወስጄ እንደዚሁ አደርጋለሁ፡፡ BSB BSB: Get two bulls for us. Let the prophets of Baal choose one bull for themselves, cut it into pieces, and place it on the wood but not light the fire. And I will prepare the other bull and place it on the wood but not light the fire.
24 ULB ከዚህ በኋላ የባዓል ነቢያት ወደ አምላካቸው ይጸልዩ፤ እኔም ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ፤ እሳትን ወደ መሥዋዕቱ በመላክ መልስ የሚሰጥ እርሱ እውነተኛ አምላክ ይሁን፡፡ ሕዝቡም ድምፁን ከፍ አድረጎ ይህ መልካም ነው በማለት መልስ ሰጡ፡፡ BSB BSB: Then you may call on the name of your god, and I will call on the name of the LORD. The God who answers by fire, He is God.” And all the people answered, “What you say is good.”
25 ULB ከዚህ በኋላ ኤልያስ የባዓልን ነቢያት እናንተ ብዙ ስለ ሆናችሁ በመጀመሪያ አንዱን ኮርማ መርጣቸሁ በማረድ ወደ አምላካችሁ ጸልዩ፤ ነገር ግን እንጨቱ ላይ እሳት አታደርጉበት አላቸው፡፡ BSB BSB: Then Elijah said to the prophets of Baal, “Since you are so numerous, choose for yourselves one bull and prepare it first. Then call on the name of your god, but do not light the fire.”
26 ULB እነርሱም የመጣላቸውን ኮርማ ወስደው በመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ፡፡ ባዓል ሆይ እባክህ ስማን! እያሉ ጮኹ፡፡ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እየዘፈኑ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም፡፡ BSB BSB: And they took the bull that was given them, prepared it, and called on the name of Baal from morning until noon, shouting, “O Baal, answer us!” But there was no sound, and no one answered as they leaped around the altar they had made.
27 ULB እኩለ ቀን ሲሆን ኤልያስ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጸልዩ! እርሱ አምላክ አይደለም እንዴ? እርሱ በአሳብ ተውጦ ይሆናል! ወይም ራሱን ያዝናና ይሆናል! ወይም ወደ ሩቅ አገር ሄዶ ይሆናል! ወይም ተኝቶ ያንቀላፋ ይሆናልና እንዲነቃ ቀስቅሱት! እያለ ያፌዝባቸው ጀመር፡፡ BSB BSB: At noon Elijah began to taunt them, saying, “Shout louder, for he is a god! Perhaps he is deep in thought, or occupied, or on a journey. Perhaps he is sleeping and must be awakened!”
28 ULB ስለዚህም ነቢያቱ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየጸለዩ በሥርዓታቸው መሠረት ደማቸው እስኪፈስ ድረስ በቢላዋና በጩቤ ሰውነታቸውን ያቆስሉ ነበር፡፡ BSB BSB: So they shouted louder and cut themselves with knives and lances, as was their custom, until the blood gushed over them.
29 ULB እኩለ ቀን ካለፈም በኋላ የሠርክ መሥዋዕት እስከሚቀርብበት ጊዜ ድረስ እየተራወጡ ይቀባጥሩ ነበር፤ ይሁን እንጂ ምንም መልስ አላገኙም፤ ድምፅም አልተሰማም፡፡ BSB BSB: Midday passed, and they kept on raving until the time of the evening sacrifice. But there was no response; no one answered, no one paid attention.
30 ULB ከዚህ በኋላ ኤልያስ ሰዎቹን ወደ እኔ ቅረቡ አላቸው፤ ሁሉም በዙሪያው ተሰበሰቡ፤ እርሱም ፈርሶ የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ በማደስ ሠራው፡፡ BSB BSB: Then Elijah said to all the people, “Come near to me.” So all the people approached him, and he repaired the altar of the LORD that had been torn down.
31 ULB እግዚአብሔር ከዚያ በፊት እስራኤል ብሎ ከሰየመው ከያዕቆብ ልጆች በዐሥራ ሁለቱ ነገዶች ስም ዐሥራ ሁለት ድንጋዮችን ወሰደ፡፡ BSB BSB: And Elijah took twelve stones, one for each tribe of the sons of Jacob, to whom the word of the LORD had come and said, “Israel shall be your name.”
32 ULB እነዚህንም ድንጋዮች ረብርቦ በእግዚአብሔር ስም መሠዊያ ሠራ፡፡ በዙሪያውም ዐሥራ አራት ሊትር ውሃ የሚይዝ ጉድጓድ ማሰ፡፡ BSB BSB: And with the stones, Elijah built an altar in the name of the LORD. Then he dug a trench around the altar large enough to hold two seahs of seed.
33 ULB እንጨቱንም በመሠዊያው ላይ በመረብረብ ኮርማውን በብልት በብልቱ ቆራርጦ በእንጨቱ ላይ አኖረ፡፡ BSB BSB: Next, he arranged the wood, cut up the bull, placed it on the wood,
34 ULB በአራት ጋን ውሃ ሞልታችሁ በመሥዋዕቱና በእንጨቱ ላይ አፍስሱት! አላቸው፡፡ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፤ አሁንም ጨምሩበት አላቸው፤ እነርሱም እንዲሁ አደረጉ፡፡ BSB BSB: and said, “Fill four waterpots and pour the water on the offering and on the wood.” “Do it a second time,” he said, and they did it a second time. “Do it a third time,” he said, and they did it a third time.
35 ULB ውሃውም በመሠዊያው ዙሪያ ፈሰሰ፤ ጉድጓዱንም ሞላው፡፡ BSB BSB: So the water ran down around the altar and even filled the trench.
36 ULB ከቀትር በኋላ የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበት ሰዓት ነቢዩ ኤልያስ ወደ መሠዊያው ቀርቦ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ የእስራኤል አምላክ መሆንህን፣ እኔም እግዚአብሔር ሆይ፣ የአንተ አገልጋይ መሆኔን፣ እኔም ይህንን ሁሉ ያደረግኹት በቃልህ መሠረት መሆኑን አንተ ራስህ ግለጥ፡፡ BSB BSB: At the time of the evening sacrifice, Elijah the prophet approached the altar and said, “O LORD, God of Abraham, Isaac, and Israel, let it be known this day that You are God in Israel and that I am Your servant and have done all these things at Your command.
37 ULB አምላኬ ሆይ፣ ይህ ሕዝብ አንተ እውነተኛ አምላክ መሆንህንና ወደ አንተም ያቀረብከው አንተ ራስህ መሆንህን እንዲያውቅ እባክህ መልስ ስጠኝ፤ አምላክ ሆይ ስማኝ! BSB BSB: Answer me, O LORD! Answer me, so that this people will know that You, the LORD, are God, and that You have turned their hearts back again.”
38 ULB ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እሳትን ላከ፤ ያ እሳት መሥዋዕቱን፣ እንጨቱንና ድንጋዩን በላ፤ ምድሩንም ለበለበ፤ በጉድጓዱ የነበረውንም ውሃ አደረቀ፡፡ BSB BSB: Then the fire of the LORD fell and consumed the sacrifice, the wood, the stones, and the dust, and it licked up the water in the trench.
39 ULB ሰዎቹም ይህን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው በመደነቅ እግዚአብሔር አምላክ ነው! እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው! አሉ፡፡ BSB BSB: When all the people saw this, they fell facedown and said, “The LORD, He is God! The LORD, He is God!”
40 ULB ኤልያስም የባዓል ነቢያትን ያዙ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ ሲል አዘዘ፡፡ ሕዝቡም በሙሉ ያዛቸው፤ ኤልያስም ወደ ቂሶን ወንዝ እየመራ ወስዶ በዚያ ሁሉንም ገደላቸው፡፡ BSB BSB: Then Elijah ordered them, “Seize the prophets of Baal! Do not let a single one escape.” So they seized them, and Elijah brought them down to the Kishon Valley and slaughtered them there.
41 ULB ከዚህ በኋላ ኤልያስ ንጉሥ አክዓብን እንግዲህ ሄደህ እህልና ውሃ ቅመስ፤ እኔ አሁን የከባድ ዝናም ነጎድጓድ ድምፅ መቃረቡን እየሰማሁ ነው አለው፡፡ BSB BSB: And Elijah said to Ahab, “Go up, eat and drink, for there is the sound of a heavy rain.”
42 ULB አክዓብ እህልና ውሃ ለመቅመስ ሲሄድም ኤልያስ ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣ፤ እዚያም በሁለቱ ጉልበቶቹ መካከል ራሱን ወደ መሬት ደፋ፡፡ BSB BSB: So Ahab went up to eat and drink. But Elijah climbed to the summit of Carmel, bent down on the ground, and put his face between his knees.
43 ULB አገልጋዩን፣ ሂድና ወደ ባሕሩ አቅጣጫ ተመልከት አለው፡፡ አገልጋዩም ሄዶ ሲመለስ ምንም ነገር አይታየኝም አለው፤ አገልጋዩ እየተመላለሰ ያይ ዘንድ ኤልያስ ሰባት ጊዜ አዘዘው፤ BSB BSB: “Go and look toward the sea,” he said to his servant. So the servant went and looked, and he said, “There is nothing there.” Seven times Elijah said, “Go back.”
44 ULB በሰባተኛውም ጊዜ አገልጋዩ ተመልሶ ከአንድ ሰው መዳፍ የማትበልጥ ትንሽ ደመና ከባሕር ስትወጣ አየሁ አለው፡፡ ኤልያስም ወደ ንጉሥ አክዓብ ሂድና ዝናቡ ሳያቆምህ በፍጥነት ወደ ሠረገላህ ገብተህ ወደ ቤትህ ተመልሰህ ሂድ ብለህ ንገረው ሲል አዘዘው፡፡ BSB BSB: On the seventh time the servant reported, “There is a cloud as small as a man’s hand rising from the sea.” And Elijah replied, “Go and tell Ahab, ‘Prepare your chariot and go down before the rain stops you.’”
45 ULB ከጥቂት ጊዜም በኋላ ሰማዩ በጥቁር ደመና ተሸፈነ፤ ነፋሱም ነፈሰ፤ ብርቱ ዝናብም ይዘንብ ጀመረ፡፡ ነጉሥ አክዓብም በሠረገላው ተቀምጦ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤ BSB BSB: Meanwhile, the sky grew dark with clouds and wind, and a heavy rain began to fall. So Ahab rode away and went to Jezreel.
46 ULB የእግዚአብሔርም ኃይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን በወገቡ ዙሪያ ጠበቅ አድረጎ በመታጠቅ እስከ ኢይዝራኤል መግቢያ በር ድረስ በአክዓብ ፊት ቀድሞ ይሮጥ ነበር፡፡ BSB BSB: And the hand of the LORD came upon Elijah, and he tucked his cloak into his belt and ran ahead of Ahab all the way to Jezreel.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.