1 ULB ፍልስጥኤማውያንም ሰራዊታቸውን ሁሉ አፌቅ ላይ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ። BSB BSB: Now the Philistines brought all their forces together at Aphek, while Israel camped by the spring in Jezreel.
2 ULB የፍልስጥኤማውያኑ መሳፍንት በመቶዎችና በሺዎች እየሆኑ አለፉ፤ ዳዊትና ሰዎቹም ከአንኩስ ጋር በደጀንነት አለፉ። BSB BSB: As the Philistine leaders marched out with their units of hundreds and thousands, David and his men marched behind them with Achish.
3 ULB ከዚያም የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ "እነዚህ ዕብራውያን እዚህ ምን ይሠራሉ?" አሉ። አንኩስም ለሌሎቹ የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ "ይህ በእነዚህ ቀናት ሁሉ ከእኔ ጋር የነበረው፥ የእስራኤል ንጉሥ የሳኦል አገልጋይ ዳዊት አይደለምን? ደግሞም በእነዚህ ዓመታት ሁሉ ወደ እኔ ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁበትም” አላቸው። BSB BSB: Then the commanders of the Philistines asked, “What about these Hebrews?” Achish replied, “Is this not David, the servant of King Saul of Israel? He has been with me all these days, even years, and from the day he defected until today I have found no fault in him.”
4 ULB ነገር ግን የፍልስጥኤም መሳፍንት በእርሱ ላይ ተቆጥተው፥ “ያንን ሰው ወደ ሰጠኸው ወደ ስፍራው እንዲመለስ አሰናብተው፥ በውጊያው ውስጥ ጠላት እንዳይሆንብን ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት አትላከው። ይህ ሰው ከጌታው ጋር ሰላምን የሚፈጥረው በምንድነው? የሰዎቻችንን አንገት በመቁረጥ አይደለምን? BSB BSB: But the commanders of the Philistines were angry with Achish and told him, “Send that man back and let him return to the place you assigned him. He must not go down with us into battle only to become our adversary during the war. What better way for him to regain the favor of his master than with the heads of our men?
5 ULB ይህ በዘፈን እየተቀባበሉ፥ 'ሳኦል ሺዎችን ገደለ፥ ዳዊት ዐሥር ሺዎችን ገደለ" ያሉለት ዳዊት አይደለምን?" አሉት። BSB BSB: Is this not the David about whom they sing in their dances: ‘Saul has slain his thousands, and David his tens of thousands’?”
6 ULB ከዚያም አንኩስ ዳዊትን ጠርቶ፥ "ሕያው እግዚአብሔርን! አንተ ጥሩ ሰው ነህ፥ በእኔ አመለካከት በሰራዊቱ ውስጥ መውጣትህና መግባትህ መልካም ነው፤ ወደ እኔ ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ እስከዛሬው ቀን ድረስ ምንም ስህተት አላገኘሁብህም። ይሁን እንጂ መሳፍንቱ አልደገፉህም። BSB BSB: So Achish summoned David and told him, “As surely as the LORD lives, you have been upright, and it seems right in my sight that you should march in and out with me in the army, because I have found no fault in you from the day you came to me until this day. But you are not good in the sight of the leaders.
7 ULB ስለዚህ አሁን የፍልስጥኤም መሳፍንት ቅር እንዳይሰኙ ተመለስና በሰላም ሂድ" አለው። BSB BSB: Therefore turn back now and go in peace, so that you will not do anything to displease the leaders of the Philistines.”
8 ULB ዳዊትም አንኩስን፥ “ግን ምን አድርጌአለሁ፥ እንዳልሄድና ከጌታዬ ከንጉሡ ጠላቶች ጋር እንዳልዋጋ በእነዚህ በፊትህ በኖርኩባቸው ቀናት በአገልጋይህ ላይ ምን አግኝተህብኛል?” አለው። BSB BSB: “But what have I done?” David replied. “What have you found against your servant, from the day I came to you until today, to keep me from going along to fight against the enemies of my lord the king?”
9 ULB አንኩስም ለዳዊት፥ “አንተ በእኔ ዕይታ ነቀፌታ እንደማይገኝበት እንደ እግዚአብሔር መልአክ ነህ፤ ይሁንና የፍልስጥኤም መሳፍንት፥ 'ከእኛ ጋር ወደ ጦርነት አይሄድም' ብለዋል። BSB BSB: Achish replied, “I know that you are as pleasing in my sight as an angel of God. But the commanders of the Philistines have said, ‘He must not go into battle with us.’
10 ULB ስለዚህ ከአንተ ጋር ከመጡት ከጌታህ አገልጋዮች ጋር ማልዳችሁ ተነሡ፤ ማልዳችሁ ተነሡና ሲነጋላችሁ ሂዱ" ብሎ መለሰለት። BSB BSB: Now then, get up early in the morning, along with your master’s servants who came with you, and go as soon as it is light.”
11 ULB ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ በጠዋት ለመሄድ፥ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ለመመለስ ማልደው ተነሡ። ፍልስጥኤማውያን ግን ወደ ኢይዝራኤል ወጡ። BSB BSB: So David and his men got up early in the morning to return to the land of the Philistines. And the Philistines went up to Jezreel.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.