1 ULB በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ፣ እንዴት መመላለስና እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት እንዳለባችሁ ከእኛ በተቀበላችሁት ትምህርት መሠረት አሁን እንደምትኖሩት ሁሉ ከዚህም አብልጣችሁ እንድታደርጉ በጌታ በኢየሱስ እንመክራችኋለን እናደፋፍራችሁማለን። BSB BSB: Finally, brothers, we ask and encourage you in the Lord Jesus to live in a way that is pleasing to God, just as you have received from us. This is how you already live, so you should do so all the more.
2 ULB በጌታ በኢየሱስ በኩል እንዴት ያለውን ትዕዛዝ እንደሰጠናችሁ ታውቃላችሁና፤ BSB BSB: For you know the instructions we gave you by the authority of the Lord Jesus.
3 ULB በቅድስና መኖራችሁ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፣ BSB BSB: For it is God’s will that you should be holy: You must abstain from sexual immorality;
4 ULB ከእናንተ እያንዳንዱ ከዝሙት በመራቅ የራሱን አካል በቅድስናና በክብር ማግኘት እንዳለበት ታውቃላችሁ፣ BSB BSB: each of you must know how to control his own body in holiness and honor,
5 ULB እግዚአብሔርን እንደማያውቁ እንደ አሕዛብ የፍትወት ምኞት አይሁን፣ BSB BSB: not in lustful passion like the Gentiles who do not know God;
6 ULB በዚህ ጉዳይ ማንም አይተላለፍ ወንድሙንም አያታልል፣ ምክንያቱም አስቀድመን እንደነገርናችሁና እንዳስጠነቀቅናችሁ ጌታ ስለነዚህ ነገሮች ሁሉ የሚበቀል ነውና። BSB BSB: and no one should ever violate or exploit his brother in this regard, because the Lord will avenge all such acts, as we have already told you and solemnly warned you.
7 ULB እግዚአብሔር ለቅድስና እንጂ ለእርኩሰት አልጠራንም። BSB BSB: For God has not called us to impurity, but to holiness.
8 ULB ስለዚህ ይህንን የማይቀበል ሰውን ሳይሆን የማይቀበለው ቅዱስ መንፈሱን የሰጣችሁን እግዚአብሔርን ነው። BSB BSB: Anyone, then, who rejects this command does not reject man but God, the very One who gives you His Holy Spirit.
9 ULB የወንድማማች መዋደድን በተመለከተ ማንም ሊጽፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፣ እርስ በርስ ስለመዋደድ እናንተው ራሳችሁ ከእግዚአብሔር ተምራችኋልና። BSB BSB: Now about brotherly love, you do not need anyone to write to you, because you yourselves have been taught by God to love one another.
10 ULB በመቄዶንያ ላሉ ወንድሞች ሁሉ ይህንን ታደርጋላችሁ፣ ይሁን እንጂ ወንድሞች ሆይ፣ ከዚህም አብልጣችሁ እንድታደርጉት ደግሞ እንመክራችኋለን። BSB BSB: And you are indeed showing this love to all the brothers throughout Macedonia. But we urge you, brothers, to excel more and more
11 ULB ደግሞም ልክ እንዳዘዝናችሁ በጸጥታ እንድትኖሩ፣ በራሳችሁ ጉዳይ ላይ እንድታተኩሩና በገዛ እጆቻችሁ እንድትሠሩ እንመክራችኋለን። BSB BSB: and to aspire to live quietly, to attend to your own matters, and to work with your own hands, as we instructed you.
12 ULB በማያምኑት ዘንድ በአግባብ እንድትመላለሱና በኑሮአችሁ ምንም የሚጎድላችሁ እንዳይኖር ይህንን አድርጉ። BSB BSB: Then you will behave properly toward outsiders, without being dependent on anyone.
14 ULB ኢየሱስ እንደሞተና እንደተነሳ ካመንን በእርሱ አምነው ያንቀላፉትን እግዚአብሔር ከኢየሱስ ጋር ያመጣቸዋል። BSB BSB: For since we believe that Jesus died and rose again, we also believe that God will bring with Jesus those who have fallen asleep in Him.
15 ULB በጌታ ቃል የምንነግራችሁ ይህንን ነው፣ ጌታ በሚመጣበት ጊዜ እኛ ሕያዋን ሆነን የቀረነው አስቀድመው ያንቀላፉትን በርግጥ አንቀድምም። BSB BSB: By the word of the Lord, we declare to you that we who are alive and remain until the coming of the Lord will by no means precede those who have fallen asleep.
17 ULB ከዚያም እኛ ሕያዋን ሆነን የምንገኘው ጌታን በአየር ላይ ለመገናኘት ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፣ ሁልጊዜም ከጌታ ጋር እንሆናለን። BSB BSB: After that, we who are alive and remain will be caught up together with them in the clouds to meet the Lord in the air. And so we will always be with the Lord.
18 ULB ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በእነዚህ ቃላት ተጽናኑ። BSB BSB: Therefore encourage one another with these words.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.