1 ULB የእግዚአብሔር መንፈስ በዖዴድ ልጅ በዓዛርያስ ላይ መጣ፡፡ BSB BSB: Now the Spirit of God came upon Azariah son of Oded.
2 ULB አሳንም ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አለው፦ "አሳ፥ ይሁዳ ሁሉና ቢኒያም ሆይ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ስትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፡፡ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል፡፡ BSB BSB: So he went out to meet Asa and said to him, “Listen to me, Asa and all Judah and Benjamin. The LORD is with you when you are with Him. If you seek Him, He will be found by you, but if you forsake Him, He will forsake you.
3 ULB እስራኤል ለረጅም ጊዜ ያለ እውነተኛ አምላክ፥ ያለ አስተማሪ ካህን እና ያለ ሕግ ይኖሩ ነበር፡፡ BSB BSB: For many years Israel has been without the true God, without a priest to instruct them, and without the law.
4 ULB በጭንቃቸው ጊዜ ግን ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ሲፈልጉት ይገኝላቸው ነበር፡፡ BSB BSB: But in their distress they turned to the LORD, the God of Israel, and sought Him, and He was found by them.
5 ULB በዚያን ዘመን ርቆ ለሚሄደውና ወደዚህ ቅርብ ለሚመጣው ሰላም አልነበረም፤ ይልቁንም በምድሪቱ በሚኖሩ ሁሉ ላይ ታላቅ ጭንቅ ነበር፡፡ BSB BSB: In those days there was no safety for travelers, because the residents of the lands had many conflicts.
6 ULB እግዚአብሔር በሁሉም ዓይነት መከራዎች ያስጨንቃቸው ስለነበር ፍርስርሳቸው ወጥቶ ነበር፤ ህዝብ ከህዝብ ጋር፥ ከተማም ከከተማ ጋር ይዋጋ ነበር፡፡ BSB BSB: Nation was crushed by nation, and city by city, for God afflicted them with all kinds of adversity.
7 ULB እናንተ ግን ሥራችሁ ብድራት ስለአለው በርቱ እጃችሁም እንዲደክም አትፍቀዱ፡፡" BSB BSB: But as for you, be strong; do not be discouraged, for your work will be rewarded.”
8 ULB ይህንን ቃል፥ የነቢዩን የዖዴድን ትንቢት በሰማ ጊዜ ብርታት አግኝቶ ከይሁዳና ከቢኒያም ምድር ሁሉ፥ ከተራራማው የኤፍሬም አገር ከያዛቸው ከተሞች ጸያፉን ነገር አስወገደ፤ በእግዚአብሔርም ቤት መተላለፊያ ፊት ለፊት የነበረውን የእግዚአብሔር መሠዊያ እንደገና ሠራ፡፡ BSB BSB: When Asa heard these words and the prophecy of Azariah son of Oded the prophet, he took courage and removed the detestable idols from the whole land of Judah and Benjamin and from the cities he had captured in the hill country of Ephraim. He then restored the altar of the LORD that was in front of the portico of the LORD’s temple.
9 ULB ይሁዳንና ቢኒያምን ሁሉ፥ ከኤፍሬምና ከምናሴም ከስምዖንም ወገን የሆኑትን ከእርሱም ጋር የዘለቁትን ሰበሰበ፡፡ እግዚአብሔር አምላኩ ከእርሱ ጋር እንደነበር ሲያዩ ከእስራኤል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ወደ እርሱ መጡ፡፡ BSB BSB: And he assembled all Judah and Benjamin, along with those from the tribes of Ephraim, Manasseh, and Simeon who had settled among them, for great numbers had come over to him from Israel when they saw that the LORD his God was with him.
10 ULB በመሆኑም አሳ በነገሠ በአስራ አምስተኛው ዓመት በሦስተኛው ወር በኢየሩሳሌም በአንድ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ BSB BSB: So they gathered together in Jerusalem in the third month of the fifteenth year of Asa’s reign.
11 ULB በዚያም ቀን ካመጡት ምርኮ የተወሰነውን ሰባት መቶ በሬዎችና ሰባት ሺህ በጎችና ፍየሎች ለእግዚአብሔር ሠዉ፡፡ BSB BSB: At that time they sacrificed to the LORD seven hundred oxen and seven thousand sheep from all the plunder they had brought back.
12 ULB የአባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን በሙሉ ልባቸውና በሙሉ ነፍሳቸው ሊፈልጉት ቃል ኪዳን አደረጉ፡፡ BSB BSB: Then they entered into a covenant to seek the LORD, the God of their fathers, with all their heart and soul.
13 ULB የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን የማይፈልግ ማንም ቢኖር ሰውየው ታናሽ ይሁን ታላቅ፥ ወንድ ወይም ሴት ሊገደል እንደሚገባው ተስማሙ፡፡ BSB BSB: And whoever would not seek the LORD, the God of Israel, would be put to death, whether young or old, man or woman.
14 ULB በታላቅ ድምጽና በጩኸት፥ በእምቢልታና በቀንደ መለከት ለእግዚአብሔር ማሉ፡፡ BSB BSB: They took an oath to the LORD with a loud voice, with shouting, trumpets, and rams’ horns.
15 ULB በሙሉ ልባቸው መሐላውን ስለፈጸሙ፥ እግዚአብሔርንም በሙሉ ፍላጎታቸው ስለፈለጉት እርሱም ተገኝቶላቸው ስለነበር ይሁዳ ሁሉ በመሐላው ደስ አላቸው፡፡ እግዚአብሔር በዙሪያቸው ሁሉ ሰላምን ሰጣቸው፡፡ BSB BSB: And all Judah rejoiced over the oath, for they had sworn it with all their heart. They had sought Him earnestly, and He was found by them. So the LORD gave them rest on every side.
16 ULB ንጉሡም አሳ ሴት አያቱ መዓካ ከማምለኪያ አጸድ አስጸያፊ ምስል/ጣኦት ስላበጀች ከንግሥትነትዋ አስወገዳት፡፡ አሳም አስጸያፊ ምስሏን/ጣኦቷን ቆርጦ አቧራ አድርጎ ፈጨው፤ በቄድሮንም ወንዝ አጠገብ አቃጠለው፡፡ BSB BSB: King Asa also removed his grandmother Maacah from her position as queen mother because she had made a detestable Asherah pole. Asa chopped down the pole, crushed it, and burned it in the Kidron Valley.
17 ULB መስገጃዎቹ ግን ከእስራኤል አልራቁም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የአሳ ልብ በዘመኑ ሁሉ ፍጹም ታማኝና ታዛዥ ነበር፡፡ BSB BSB: The high places were not removed from Israel, but Asa’s heart was fully devoted all his days.
18 ULB የእግዚአብሔር የሆኑትን የአባቱን ነገሮችና የገዛ ራሱን ነገሮች፥ የብርና የወርቅ ዕቃዎች ወደ እግዚአብሔር ቤት ውስጥ አስገባቸው፡፡ BSB BSB: And he brought into the house of God the silver and gold and the articles that he and his father had dedicated.
19 ULB አሳም እስከነገሠበት እስከ ሠላሳ አምስተኛው ዓመት ድረስ ከዚያ ወዲያ ጦርነት አልነበረም፡፡ BSB BSB: And there was no war until the thirty-fifth year of Asa’s reign.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.