1 ULB በተጨማሪም የናሱን መሠዊያ ሠራ፤ ርዝመቱ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር፤ ቁመቱም አሥር ክንድ ነበር፡፡ BSB BSB: He made a bronze altar twenty cubits long, twenty cubits wide, and ten cubits high.
2 ULB ክፈፉ ከጫፍ እስከ ጫፉ አሥር ክንድ የሆነ ከቀለጠ ብረት ትልቅ ክብ ውሃ መያዣ ኩሬም ሠራ፡፡ ቁመቱም አምስት ክንድ ነበር፤ ዙሪያውም ሰላሳ ክንድ ነበር፡፡ BSB BSB: He also made the Sea of cast metal. It was circular in shape, measuring ten cubits from rim to rim, five cubits in height, and thirty cubits in circumference.
3 ULB ውሃ መያዣው ቀልጦ ሲሰራ ከአርሱ ጋር አብረው የተሠሩ ከውሃ መያዣው ዙሪያ ከክፈፉ በታች በእያንዳንዱ ክንድ ርቀት አሥር ኮርማዎች ነበሩበት፡፡ BSB BSB: Below the rim, figures of oxen encircled it, ten per cubit all the way around the Sea, cast in two rows as a part of the Sea.
4 ULB ውሃ መያዣው ሦስቱ ወደ ሰሜን በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ምዕራብ በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ደቡብ በሚመለከቱ፥ ሦስቱ ወደ ምሥራቅ በሚመለከቱ በአሥራ ሁለት በሬዎች ላይ ተቀምጦ ነበር፡፡ ውሃ መያዣው በላያቸው ላይ ሆኖ የጀርባ የሠውነት ክፍላቸው በስተ ውስጥ ነበር፡፡ BSB BSB: The Sea stood on twelve oxen, three facing north, three facing west, three facing south, and three facing east. The Sea rested on them, with all their hindquarters toward the center.
5 ULB ውፍረቱም አንድ ጋት ያህል ነበር፡፡ የአፉ ክፈፍም እንደ ጽዋ ከንፈር እንደ ፈነዳ የሱፍ አበባ ሆኖ ተሠርቶ ነበር፡፡ ሦስት ሺህም የባዶስ መስፈሪያ ውሃ ይይዝ ነበር፡፡ BSB BSB: It was a handbreadth thick, and its rim was fashioned like the brim of a cup, like a lily blossom. It could hold three thousand baths.
6 ULB ደግሞም የተለያዩ ነገሮችን ማጠቢያ አሥር ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፤ አምስቱን በስተግራ አምስቱንም በስተቀኝ አኖራቸው፤ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ለማቅረብ ጥቅም የሚሰጡ ነገሮች በውስጣቸው ይታጠቡባቸው ነበር፡፡ የውሃ መያዣው ኩሬ ግን ለካህናቱ መታጠቢያ ነበር፡፡ BSB BSB: He also made ten basins for washing and placed five on the south side and five on the north. The parts of the burnt offering were rinsed in them, but the priests used the Sea for washing.
7 ULB ለንድፋቸው በተሰጠው መመሪያ መሠረት አሥሩን የወርቅ መቅረዞች ሠራ፤ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አምስቱን በስተግራ አምስቱን በስተቀኝ አኖራቸው፡፡ BSB BSB: He made ten gold lampstands according to their specifications and placed them in the temple, five on the south side and five on the north.
8 ULB አሥሩንም ገበታዎች ሠርቶ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አምስቱን በስተግራ አምስቱን በስተቀኝ አኖራቸው፡፡ አንድ መቶ የወርቅ ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፡፡ BSB BSB: Additionally, he made ten tables and placed them in the temple, five on the south side and five on the north. He also made a hundred gold bowls.
9 ULB በተጨማሪም የካህናቱን አደባባይ እና ታላቁንም አደባባይ የአደባባዮቹንም በሮች ሠራ፤ በሮቻቸውንም በናስ ለበጠ፡፡ BSB BSB: He made the courtyard of the priests and the large court with its doors, and he overlaid the doors with bronze.
10 ULB የውሃ መያዣውንም ኩሬ በቤቱ በስተቀኝ በስተምስራቅ ፊቱን ወደ ደቡብ አዙሮ አኖረው፡፡ BSB BSB: He put the Sea on the south side, at the southeast corner.
11 ULB ኪራምም ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹንና መሠዊያውን መርጪያ ጎድጓዳ ሳህኖች ሠራ፡፡ ኪራምም እንደዚህ ለንጉሥ ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት የሠራውን ሥራ ሁሉ- BSB BSB: Additionally, Huram made the pots, shovels, and sprinkling bowls. So Huram finished the work that he had undertaken for King Solomon in the house of God:
12 ULB ሁለቱን አዕማድ፥ በሁለቱ አዕማድ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች፥ በሁለቱ አዕማድ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች የሚሸፍኑትን ሁለቱን ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች ጨረሰ፡፡ BSB BSB: the two pillars; the two bowl-shaped capitals atop the pillars; the two sets of network covering both bowls of the capitals atop the pillars;
13 ULB በአዕማዱ ጫፍ ላይ የነበሩትን ጉልላቶች ለሚሸፍኑት ሁለቱ ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች ለእያንዳንዳቸው ሁለት ተርታ ሮማኖች አድርጎ ለሁለቱ ጌጠኛ ቅርፃ ቅርፆች አራት መቶ ሮማኖች ሠራ፡፡ BSB BSB: the four hundred pomegranates for the two sets of network (two rows of pomegranates for each network covering both the bowl-shaped capitals atop the pillars);
14 ULB ማቆሚያዎቹንና በማቆሚያዎቹ ላይ የሚቀመጡትን የመታጠቢያ ሰሃኖችንም ሠራ፤ BSB BSB: the stands; the basins on the stands;
15 ULB አንድ የውሃ መያዣ ኩሬ እና ከስሩ የሚሆኑትን አስራ ሁለት ኮርማዎች፥ BSB BSB: the Sea; the twelve oxen underneath the Sea;
16 ULB እንዲሁም ምንቸቶቹን፥ መጫሪያዎቹን፥ ሜንጦዎቹን እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ቁሳቁሶችን ሁሉ ሠራ፤ ኪራም ለንጉሥ ሰለሞን ለእግዚአብሔር ቤት ከአንፀባራቂ ናስ ሠራቸው፡፡ BSB BSB: and the pots, shovels, meat forks, and all the other articles. All these objects that Huram-abi made for King Solomon for the house of the LORD were of polished bronze.
17 ULB ንጉሡም በዮርዳኖስ ሜዳ በሱኮትና ዛሬታን መካከል በሸክላው መሬት ውስጥ ብረታ ብረቱ እንዲቀልጥ አስደረገ፡፡ BSB BSB: The king had them cast in clay molds in the plain of the Jordan between Succoth and Zeredah.
18 ULB ሰለሞንም እነዚህን እቃዎች ሁሉ በብዛት እንዲሰሩ አስደረገ፤ በእርግጥም የናሱ ክብደት ሊታወቅ አይችልም ነበር፡፡ BSB BSB: Solomon made all these articles in such great abundance that the weight of the bronze could not be determined.
19 ULB ሰለሞን በእግዚአብሔር ቤት የነበሩትን የቤት ዕቃዎች፥ የወርቁን መሠዊያ፥ የመገኘቱ ሕብስት የሚቀመጥባቸውን ገበታዎች፥ BSB BSB: Solomon also made all the furnishings for the house of God: the golden altar; the tables on which was placed the Bread of the Presence;
20 ULB በቅድስተ ቅዱሳን ፊት ያበሩ ዘንድ የታቀዱትን መቅረዞችን ከቀንዲሎቹ ጋር ሠራ፡፡እነዚህ ከንጹሕ ወርቅ የተሰሩ ነበሩ፡፡ BSB BSB: the lampstands of pure gold and their lamps, to burn in front of the inner sanctuary as prescribed;
21 ULB አበባዎቹም፥ ቀንዲሎቹና መኮስተሪያዎቹም የጥሩ ወርቅ ነበሩ፡፡ BSB BSB: the flowers, lamps, and tongs of gold—of purest gold;
22 ULB ጉጠቶቹም፥ ጎድጓዳ ሳህኖቹም፥ ማንኪያዎቹም፥ እጣን ማጨሻዎቹም ሁሉ ከንጹህ ወርቅ የተሰሩ ነበሩ፡፡ ወደ ቤቱ ውስጥ መግቢያዎቹን በተመለከተ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የሚያስገቡት የውስጥ በሮች እና የቤቱ ማለትም የቤተ መቅደሱ በሮች ከወርቅ የተሠሩ ነበሩ፡፡ BSB BSB: the wick trimmers, sprinkling bowls, ladles, and censers of pure gold; and the gold doors of the temple: the inner doors to the Most Holy Place as well as the doors of the main hall.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.