1 ULB ከሽማግሌው በእውነት ለምወዳችሁና እኔም ብቻ ሳልሆን እውነትን የሚያውቁ ሁሉ ለሚወዱአችሁ ለተመረጥች እመቤትና ለልጆችዋ። BSB BSB: The elder, To the chosen lady and her children, whom I love in the truth—and not I alone, but also all who know the truth—
2 ULB ይህም ፍቅር በውስጣችን ካለውና ለዘላለም ከእኛ ጋር ከሚሆነው እውነት የተነሳ ነው። BSB BSB: because of the truth that abides in us and will be with us forever:
3 ULB በእውነትና በፍቅር ከእግዚአብሔር አብ ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ምህረትና ሠላም ከሁላችን ጋር ይሁን። BSB BSB: Grace, mercy, and peace from God the Father and from Jesus Christ, the Son of the Father, will be with us in truth and love.
4 ULB ከልጆችሽ መካከል ከአብ በተቀበልነው ትዕዛዝ መሠረት በእውነት ሲሄዱ በማግኘቴ እጅግ ሀሴት አደርጋለሁ። BSB BSB: I was overjoyed to find some of your children walking in the truth, just as the Father has commanded us.
5 ULB እንግዲህ እመቤት አሁን አዲስ ትዕዛዝ እንደምሰጥ ሳይሆን እርስ በእርሳችን እንዋደድ ብዬ ከመጀመሪያው በነበረን ትዕዛዝ እለምንሻለሁ። BSB BSB: And now I urge you, dear lady—not as a new commandment to you, but one we have had from the beginning—that we love one another.
6 ULB ይህም በትዕዛዛቱ መሰረት ልንጓዝበት የሚገባን ፍቅር ነው። ይህ ትዕዛዝ ከመጀመሪያው እንደሰማችሁት ልትራመዱበት የሚገባ ትዕዛዝ ነው። BSB BSB: And this is love, that we walk according to His commandments. This is the very commandment you have heard from the beginning, that you must walk in love.
7 ULB ምክንያቱም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ እንደመጣ የማያምኑ ብዙ አሳቾች ወደ ዓለም ወጥተዋል። ይህም አሳቹና የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው። BSB BSB: For many deceivers have gone out into the world, refusing to confess the coming of Jesus Christ in the flesh. Any such person is the deceiver and the antichrist.
8 ULB ሙሉ ዋጋችሁን እንድትቀበሉ እንጂ እኛ ሁላችን የደክምንባቸውን ነገሮች እንዳታጡ ስለራሳችሁ ተጠንቀቁ። BSB BSB: Watch yourselves, so that you do not lose what we have worked for, but that you may be fully rewarded.
9 ULB በክርስቶስ ትምህርት ሳይጸና ዝም ብሎ ወደፊት የሚገሰግስ እግዚአብሄርን አያውቅም። በዚህ ትምህርት የሚጸና አብና ወልድ አሉት። BSB BSB: Anyone who runs ahead without remaining in the teaching of Christ does not have God. Whoever remains in His teaching has both the Father and the Son.
10 ULB ማንም ወደ እናንተ መጥቶ ይህን ትምህርት ባያስተምር ወደ ቤታችሁ እንዲገባ አትፍቀዱለት ሠላምም አትበሉት። BSB BSB: If anyone comes to you but does not bring this teaching, do not receive him into your home or even greet him.
11 ULB ምክንያቱም ሠላምታ የሚሰጠው ሁሉ በክፉ ሥራው ይካፈላል። BSB BSB: Whoever greets such a person shares in his evil deeds.
12 ULB የምጽፍላችሁ ብዙ ነገር ነበረኝ ነገር ግን በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልፈለግሁም። ነገር ግን ደስታችን ሙሉ ይሆን ዘንድ ወደ እናንተ ልመጣና ፊት ለፊት ላወራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። BSB BSB: I have many things to write to you, but I would prefer not to do so with paper and ink. Instead, I hope to come and speak with you face to face, so that our joy may be complete.
13 ULB የተመረጠችው እህትሽ ልጆች ሠላምታ ያቀርቡልሻል። BSB BSB: The children of your elect sister send you greetings.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.