1 ULB ሐሰተኞች ነቢያት በእስራኤላውያን መካከል ነበሩ፤ በእናንተ መካከል ደግሞ ሐሰተኞች መምህራን ይኖራሉ፤ እነርሱ ጥፋትን የሚያስከትል ሐሰተኛ ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ የዋጃቸውንም ጌታ ክደው ፈጣን ጥፋትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ። ብዙዎች የእነርሱን መዳራት ይከተላሉ። BSB BSB: Now there were also false prophets among the people, just as there will be false teachers among you. They will secretly introduce destructive heresies, even denying the Master who bought them—bringing swift destruction on themselves.
2 ULB ከእነርሱም አድራጎት የተነሣ የእውነት መንገድ ይሰደባል። BSB BSB: Many will follow in their depravity, and because of them the way of truth will be defamed.
3 ULB እነዚህ ሐሰተኞች መምህራን ለገንዘብ ከመስገብገባቸው የተነሣ የሚያታልሉ ቃላትን በመጠቀም ይበዘብዙአችኋል። በእነርሱ ላይ ያለው ፍርድ አይዘገይም፤ መጥፊያቸውም የራቀ አይደለም። BSB BSB: In their greed, these false teachers will exploit you with deceptive words. The longstanding verdict against them remains in force, and their destruction does not sleep.
4 ULB እግዚአብሔር ኀጢአት የሠሩትን መላእክት ሳይራራላቸው ወደ ገሐነም ከጣላቸውና በሰንሰለት አስሮ እስከ ፍርድ ጊዜ ድረስ በጨለማ ውስጥ ካስቀመጣቸው፣ BSB BSB: For if God did not spare the angels when they sinned, but cast them deep into hell, placing them in chains of darkness to be held for judgment;
5 ULB የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ ለጥንቱ ዓለም ሳይራራ በኀጢአተኞች ላይ የጥፋት ውሃ ካመጣ፣ BSB BSB: if He did not spare the ancient world when He brought the flood on its ungodly people, but preserved Noah, a preacher of righteousness, among the eight;
7 ULB በሕገ ወጦች ሴሰኝነት ነፍሱ እየተጨነቀ ይኖር የነበረውን ጻድቁን ሎጥን ግን አዳነው፤ BSB BSB: and if He rescued Lot, a righteous man distressed by the depraved conduct of the lawless
8 ULB ያ ጻድቅ ሰው በመካከላቸው ሲኖር በየቀኑ ያየውና ይሰማው በነበረው ሕገ ወጥ ድርጊታቸው ጻድቅ ነፍሱ ትጨነቅ ነበር። BSB BSB: (for that righteous man, living among them day after day, was tormented in his righteous soul by the lawless deeds he saw and heard)—
9 ULB ጌታ፣ እግዚአብሔርን የሚመስሉትን ሰዎች ከፈተና እንዴት እንደሚያድናቸውና ዐመፀኞችን እየቀጣ ለፍርድ ቀን እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል። BSB BSB: if all this is so, then the Lord knows how to rescue the godly from trials and to hold the unrighteous for punishment on the day of judgment.
10 ULB በተለይም ብልሹ የሥጋ ምኞታቸውን የሚከተሉትንና ሥልጣንን የሚንቁትን ለፍርድ ጠብቆ ያቈያቸዋል። እነዚህ ሰዎች ደፋሮችና እብሪተኞች ስለ ሆኑ የከበሩትን ሲሳደቡ አይፈሩም፤ BSB BSB: Such punishment is specially reserved for those who indulge the corrupt desires of the flesh and despise authority. Bold and self-willed, they are unafraid to slander glorious beings.
11 ULB መላእክት ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ብርታትና ችሎታ ያላቸው ሆነው ሳሉ፣ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ ዘለፋ ያዘለ የፍርድ ቃል አይሰነዝሩም። BSB BSB: Yet not even angels, though greater in strength and power, dare to bring such slanderous charges against them before the Lord.
12 ULB እነዚህ አእምሮ እንደ ጎደላቸው እንስሳት ለምርኮና ለጥፋት የተፈጠሩ ናቸው፤ የሚሳደቡትን ስለማያውቁ ይጠፋሉ። BSB BSB: These men are like irrational animals, creatures of instinct, born to be captured and destroyed. They blaspheme in matters they do not understand, and like such creatures, they too will be destroyed.
13 ULB እነርሱ የዐመፃቸውን ዋጋ ይቀበላሉ፤ በቀን በመስከርና ያለ ልክ በመፈንጠዝ ይኖራሉ፤ እነርሱ አሳፋሪዎችና ነውረኞች ናቸው። ከእናንተ ጋር ግብዣ ላይ ሲገኙ፣ በአታላይ ፈንጠዝያቸው ሐሴት ያደርጋሉ። BSB BSB: The harm they will suffer is the wages of their wickedness. They consider it a pleasure to carouse in broad daylight. They are blots and blemishes, reveling in their deception as they feast with you.
14 ULB ዐይናቸው ቅንዝር የተሞላ በመሆኑ ኀጢአትን ከመሥራት ከቶ አይቈጠቡም፤ ጽኑ ያልሆኑትን ሰዎች ያስታሉ፤ መመኘትን የለመደ ልብ አላቸው፤ የተረገሙ ልጆች ናቸው። BSB BSB: Their eyes are full of adultery; their desire for sin is never satisfied; they seduce the unstable. They are accursed children with hearts trained in greed.
15 ULB ቀናውን መንገድ ትተው፣ በክፉ ሥራ የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ስተዋል፤ BSB BSB: They have left the straight way and wandered off to follow the way of Balaam son of Beor, who loved the wages of wickedness.
16 ULB እርሱ ስለ መተላለፉ ተገሥጾአል፤ መናገር የማይችል አህያ በሰው ቋንቋ ተናግሮ የነቢዩን እብደት አስቍሟልና። BSB BSB: But he was rebuked for his transgression by a donkey, otherwise without speech, that spoke with a man’s voice and restrained the prophet’s madness.
17 ULB እነዚህ ሰዎች እንደ ደረቁ ምንጮችና በዐውሎ ነፋስ እንደሚነዱ ደመናዎች ናቸው፤ የሚጠብቃቸውም ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ BSB BSB: These men are springs without water and mists driven by a storm. Blackest darkness is reserved for them.
18 ULB ፍሬ ቢስ የዕብሪት ቃል በመናገር፥ በሥጋዊ ፍትወታቸው ሰዎችን ያጠምዳሉ፤ ከተሳሳተና ከብልሹ የሕይወት ዘይቤ ለማምለጥ የሚሞክሩትን ሰዎች ያጠምዳሉ። BSB BSB: With lofty but empty words, they appeal to the sensual passions of the flesh and entice those who are just escaping from others who live in error.
19 ULB እነርሱ ራሳቸው የጥፋት ባሪያዎች ሆነው ሳሉ፣ ሌሎችን ነጻ ትወጣላችሁ እያሉ ተስፋ ይሰጧቸዋል፤ ሰው ለሚሸነፍለት ለማንኛውም ነገር ባሪያ ነውና። BSB BSB: They promise them freedom, while they themselves are slaves to depravity. For a man is a slave to whatever has mastered him.
21 ULB የጽድቅን መንገድ ካወቁ በኋላ ከተሰጣቸው ቅዱስ ትእዛዝ ወደ ኋላ ከሚመለሱ፣ ቀድሞውኑ የጽድቅን መንገድ ባያውቋት ይሻላቸው ነበር። BSB BSB: It would have been better for them not to have known the way of righteousness than to have known it and then to turn away from the holy commandment passed on to them.
22 ULB «ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል» እንዲሁም «ዐሣማ ቢታጠብም ተመልሶ በጭቃ ላይ ይንከባለላል» የሚለው ምሳሌ እውን ይሆንባቸዋል። BSB BSB: Of them the proverbs are true: “A dog returns to its vomit,” and, “A sow that is washed goes back to her wallowing in the mud.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.