1 ULB እግዚአብሔር ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፣ “በአንድ ከተማ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ባለጠጋ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ድኻ ነበረ፡፡ BSB BSB: Then the LORD sent Nathan to David, and when he arrived, he said, “There were two men in a certain city, one rich and the other poor.
2 ULB ባለጠጋው እጅግ ብዙ መንጋዎችና የቀንድ ከብቶች ነበሩት፤ BSB BSB: The rich man had a great number of sheep and cattle,
3 ULB ድኻው ግን ከገዛትን ካሳደጋት ከአንዲት መሲና በግ በስተቀር ሌላ አልነበረውም፡፡ ይህች በግ ከእርሱ ጋር ኖረች ከልጆቹም ጋር አደገች፡፡ በጊቱ እንዲያውም ከእርሱ ጋር ትበላ፣ ከጽዋውም ትጠጣ ነበር፤ በእቅፉም ትተኛ ነበር፣ ለእርሱም እንደ ሴት ልጁ ነበረች፡፡ BSB BSB: but the poor man had nothing except one small ewe lamb that he had bought. He raised it, and it grew up with him and his children. It shared his food and drank from his cup; it slept in his arms and was like a daughter to him.
4 ULB አንድ ቀን አንድ እንግዳ ወደ ባለጠጋው ቤት መጣ፤ ባለጠጋው ግን ለእንግዳው ምግብ ለማቅረብ ከራሱ መንጋ ወይም ከቀንድ ከብቶቹ አንድ እንሰሳ ለመውሰድ ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ ከዚያ ይልቅ የድኻውን መሲና ጠቦት ወስዶ ለእንግዳው ምግብ አድርጎ አዘጋጀለት፡፡” BSB BSB: Now a traveler came to the rich man, who refrained from taking one of his own sheep or cattle to prepare for the traveler who had come to him. Instead, he took the poor man’s lamb and prepared it for his guest.”
5 ULB ዳዊትም በባለጠጋው ላይ ቁጣው ነደደ፣ በንዴትም ለናታን፣ “ሕያው እግዚአብሔርን ይህን ያደረገው ሰው ሞት ይገባዋል! BSB BSB: David burned with anger against the man and said to Nathan: “As surely as the LORD lives, the man who did this deserves to die!
6 ULB እንዲህ ያለውን ነገር በማድረጉና ለደኻውም ባለመራራቱ ስለ በጊቱ አራት ዕጥፍ መክፈል አለበት፡፡” BSB BSB: Because he has done this thing and has shown no pity, he must pay for the lamb four times over.”
7 ULB ከዚያ በኋላም ናታን ለዳዊት፣ “ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንደዚህ ይላል፣ ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ ከሳኦልም እጅ ታደግሁህ፤ BSB BSB: Then Nathan said to David, “You are that man! This is what the LORD, the God of Israel, says: ‘I anointed you king over Israel, and I delivered you from the hand of Saul.
8 ULB የጌታህን ቤት ሰጠሁህ፣ የጌታህንም ሚስቶች በብትህ አስታቀፍሁህ፤ የእስራኤልና የይሁዳን ቤት ሰጠሁህ፤ ይህም ሁሉ አንሶህ ቢሆን ብዙ ሌሎች ነገሮችንም ጨምሬ በሰጠሁህ ነበር፡፡ BSB BSB: I gave your master’s house to you and your master’s wives into your arms. I gave you the house of Israel and Judah, and if that was not enough, I would have given you even more.
9 ULB ስለዚህ በእርሱ ፊት ክፉ የሆነውን ታደርግ ዘንድ የእግዚአብሔርን ሕግ ለምን አቃለልህ? ኬጢያዊውን ኦርዮንን በሰይፍ ገደለህ፣ ሚስቱንም ወስደህ የራስህ ሚስት አደረግኸት፡፡ ኦርዮንን በአሞናውያን ሠራዊት ሰይፍ ገደልኸው፡፡ BSB BSB: Why then have you despised the command of the LORD by doing evil in His sight? You put Uriah the Hittite to the sword and took his wife as your own. You have slain him with the sword of the Ammonites.
10 ULB እኔን አቃለኸኛልና የኬጢያዊውንም የኦርዮንን ሚስት ሚስትህ አድርገህ ወስደሃልና ሰይፍ ከቤትህ በፍጹም አይርቅም፡፡’ BSB BSB: Now, therefore, the sword will never depart from your house, because you have despised Me and have taken the wife of Uriah the Hittite to be your own.’
11 ULB እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ ‘ከራስህ ቤት ጥፋት አስነሳብሃለሁ፤ ዓይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለጎረቤትህ እሰጠዋለሁ፣ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል፡፡ BSB BSB: This is what the LORD says: ‘I will raise up adversity against you from your own house. Before your very eyes I will take your wives and give them to another, and he will lie with them in broad daylight.
12 ULB አንተ ኃጢአትህን በስውር እኔ ግን ይህንን ነገር በቀን ብርሃን በእስራኤል ሁሉ ፊት እገልጠዋለሁ፡፡’” BSB BSB: You have acted in secret, but I will do this thing in broad daylight before all Israel.’”
13 ULB ከዚያም ዳዊት ለናታን፣ “እግዚአብሔርን በድያለሁ” አለው፡፡ ናታንም ለዳዊት መለሰለት፣ “እግዚአብሔር ኃጢአትህን አስወግዶልሃል፡፡ አንተ አትሞትም፤ BSB BSB: Then David said to Nathan, “I have sinned against the LORD.” “The LORD has taken away your sin,” Nathan replied. “You will not die.
14 ULB ይሁን እንጂ በዚህ ድርጊትህ እግዚአብሔርን ስላቃለልህ የተወለደልህ ልጅ በእርግጥ ይሞታል፡፡” BSB BSB: Nevertheless, because by this deed you have shown utter contempt for the word of the LORD, the son born to you will surely die.”
15 ULB ከዚያ በኋላ ናታን ወጥቶ ወደ ቤቱ ሄደ፡፡ እግዚአብሔርም የኦርዮን ሚስት ለዳዊት የወለደችለትን ልጅ እግዚአብሔር አስጨነቀው እጅግም ታመመ፡፡ BSB BSB: After Nathan had gone home, the LORD struck the child that Uriah’s wife had borne to David, and he became ill.
16 ULB ዳዊት ስለ ልጁ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ጾመም ከዚያም ወደ ክፍሉ ገብቶ ሌሊቱን ወለሉ ላይ ተኝቶ አደረ፡፡ BSB BSB: David pleaded with God for the boy. He fasted and went into his house and spent the night lying in sackcloth on the ground.
17 ULB የቤተሰቡ ሽማግሌዎችም ከወለሉ ላይ ያነሱት ዘንድ በአጠገቡ ቆሙ፣ እርሱ ግን አልተነሳም፣ ከእነርሱም ጋር አልበላም፡፡ BSB BSB: The elders of his household stood beside him to help him up from the ground, but he was unwilling and would not eat anything with them.
18 ULB በሰባተኛውም ቀን ልጁ ሞተ፡፡ “እነሆ፣ ልጁ ገና በሕይወት ሳለ ስናነጋግረው ድምፃችንን አልሰማንም፣ ታዲያ፣ ልጁ ሞቶአል ብንለው በራሱ ላይ ምን ያደርግ ይሆን?!” ብለው ስለነበረ፣ የዳዊት አገልጋዮች ልጁ እንደ ሞተ ለመንገር ፈርተው ነበር፡፡ BSB BSB: On the seventh day the child died. But David’s servants were afraid to tell him that the child was dead, for they said, “Look, while the child was alive, we spoke to him, and he would not listen to us. So how can we tell him the child is dead? He may even harm himself.”
19 ULB ነገር ግን እርስ በርሳቸው ሲንሾካሾኩ ዳዊት በተመለከተ ጊዜ፣ ልጁ እንደ ሞተ ዳዊት ተገነዘበ፤ ለአገልጋዮቹም፣ “ልጁ ሞተ?” ብሎ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም፣ “ሞቶአል” ብለው መለሱለት፡፡ BSB BSB: When David saw that his servants were whispering to one another, he perceived that the child was dead. So he asked his servants, “Is the child dead?” “He is dead,” they replied.
20 ULB ከዚያም ዳዊት ከወለሉ ላይ ተነስቶ ታጠበ፣ ቅባት ተቀባ ደግሞም ልብሱን ለወጠ፤ ወደ እግዚአብሔር ቤትም ሄዶ አምልኮ አቀረበ፣ ከዚያ በኋላም ወደ ራሱ ቤተ መንግሥት ተመለሰ፡፡ ምግብ እንዲያቀርቡለት በጠየቀ ጊዜ አቀረቡለት፣ እርሱም በላ፡፡ BSB BSB: Then David got up from the ground, washed and anointed himself, changed his clothes, and went into the house of the LORD and worshiped. Then he went to his own house, and at his request they set food before him, and he ate.
21 ULB ከዚያ በኋላ አገልጋዮቹ፣ “እንደዚህ ያደረግኸው ለምንድን ነው? ልጁ በሕይወት እያለ ጾምህ አለቀስህም፤ ልጁ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ በላህ” አሉት፡፡ BSB BSB: “What is this you have done?” his servants asked. “While the child was alive, you fasted and wept, but when he died, you got up and ate.”
22 ULB ዳዊትም፣ “ልጁ ገና በሕይወት ሳለ ጾምሁ አለቀስሁም፤ ‘ልጁ በሕይወት ይኖር ዘንድ እግዚአብሔር ቸርነት ያደርግልኝ እንደሆነ ማን ያውቃል’ ብዬ ነበር፡፡ BSB BSB: David answered, “While the child was alive, I fasted and wept, for I said, ‘Who knows? The LORD may be gracious to me and let him live.’
23 ULB አሁን ግን፣ እርሱ ሞቶአልና ለምን እጾማለሁ? መልሼ ላመጣው እችላለሁን? እኔ ወደ እርሱ እሄዳለሁ እንጂ እርሱ ወደ እኔ አይመለስም፡፡” BSB BSB: But now that he is dead, why should I fast? Can I bring him back again? I will go to him, but he will not return to me.”
24 ULB ከዚያም ዳዊት ሚስቱን ቤርሳቤህን አጽናናት፤ ወደ እርሷም ገብቶ አብሮአት ተኛ፡፡ ከዚህም የተነሣ ወንድ ልጅ ወለደች፣ ልጁም ሰሎሞን የሚል ስም ተሰጠው፤ እግዚአብሔርም ወደደው፡፡ BSB BSB: Then David comforted his wife Bathsheba, and he went to her and lay with her. So she gave birth to a son, and they named him Solomon. Now the LORD loved the child
25 ULB ስለሆነም እግዚአብሔር ስለወደደው ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ፡፡ BSB BSB: and sent word through Nathan the prophet to name him Jedidiah because the LORD loved him.
26 ULB በዚያን ጊዜም ኢዮአብ የአሞናውያን የንጉሥ ከተማ የነበረችውን ረባትን ወግቶ ምሽጉን ያዘ፡፡ BSB BSB: Meanwhile, Joab fought against Rabbah of the Ammonites and captured the royal fortress.
27 ULB ስለሆነም ኢዮአብ ወደ ዳዊት መልእክተኞችን በመላክ እንዲህ አለው፣ “ረባትን ወግቼ የከተማይቱን የውሃ ማከፋፈያ ይዤአለሁ፡፡ BSB BSB: Then Joab sent messengers to David to say, “I have fought against Rabbah and have captured the water supply of the city.
28 ULB እንግዲህ አሁን፣ የቀረውን ሠራዊት አሰባስበህ በከተማይቱ ዙሪያ ሠፍረህ ያዛት፤ ምክንያቱም እኔ ከተማይቱን ከያዝኳት በስሜ መጠራቷ ነው፡፡” BSB BSB: Now, therefore, assemble the rest of the troops, lay siege to the city, and capture it. Otherwise I will capture the city, and it will be named after me.”
29 ULB ስለዚህ ዳዊት መላውን ሠራዊት አሰባስቦ ወደ ረባት ሄዶ ከተማይቱን ወግቶ ያዛት፡፡ BSB BSB: So David assembled all the troops and went to Rabbah; and he fought against it and captured it.
30 ULB ዳዊት ከሞሎክ ራስ ላይ ዘውዱን ወሰደ፤ የዘውዱም ክብደት አንድ መክሊት ወርቅ ሲሆን የከበረ ዕንቁም በላዩ ላይ ነበረበት፡፡ ዘውዱም በዳዊት ራስ ላይ ተጫነ፡፡ ከዚያም እጅግ ብዙ የከተማይቱን ምርኮ አመጣ፡፡ BSB BSB: Then he took the crown from the head of their king. It weighed a talent of gold and was set with precious stones, and it was placed on David’s head. And David took a great amount of plunder from the city.
31 ULB በከተማይቱ የነበሩትንም ሰዎች አውጥቶ በመጋዝ፣ በብረት መቆፈሪያና በመጥረቢያ እንዲሠሩ አስገደዳቸው፤ የሸክላ ጡብም እንዲሠሩ አደረጋቸው፡፡ ዳዊት የአሞን ሕዝብ ከተሞች ሁሉ ይህንኑ ተግባር እንዲፈጽሙ አደረጋቸው፡፡ ከዚያም ዳዊትና ሠራዊቱ በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፡፡ BSB BSB: David brought out the people who were there and put them to work with saws, iron picks, and axes, and he made them work at the brick kilns. He did the same to all the Ammonite cities. Then David and all his troops returned to Jerusalem.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.