1 ULB የእስራኤል ነገዶች በሙሉ ወደ ኬብሮን ወደ ዳዊት መጥተው እንዲህ አሉ፣ “እነሆ እኛ የዐጥንትህ ፍላጭ የሥጋህ ቁራጭ ነን፤ BSB BSB: Then all the tribes of Israel came to David at Hebron and said, “Here we are, your own flesh and blood.
2 ULB ሳኦል በእኛ ላይ ነግሦ በነበረበት ባለፈው ጊዜ የእስራኤልን ሠራዊት የምትመራ አንተ ነበርህ፤ እግዚአብሔርም፣ ‘ሕዝቤን እስራኤልን ትጠብቃለህ፣ በእስራኤልም ላይ ገዥ ትሆናለህ’ ብሎህ ነበር፡፡” BSB BSB: Even in times past, while Saul was king over us, you were the one who led Israel out and brought them back. And to you the LORD said, ‘You will shepherd My people Israel, and you will be ruler over them.’”
3 ULB ስለዚህም የእስራኤል ሽማግሌዎች በሙሉ ወደ ንጉሡ ወደ ኬብሮን መጡ፤ ንጉሥ ዳዊትም ኬብሮን ላይ በእግዚአብሔር ፊት ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ እነርሱም ዳዊትን ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት፡፡ BSB BSB: So all the elders of Israel came to the king at Hebron, where King David made with them a covenant before the LORD. And they anointed him king over Israel.
4 ULB ዳዊት በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረr፤ አርባ ዓመትም ገዛ፡፡ BSB BSB: David was thirty years old when he became king, and he reigned forty years.
5 ULB በኬብሮን በይሁዳ ላይ ለሰባት ዓመት ከስድስት ወር፣ ኢየሩሳሌም ሆኖም በመላው እስራኤልና በይሁዳ ላይ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነገሠ፡፡ BSB BSB: In Hebron he reigned over Judah seven years and six months, and in Jerusalem he reigned thirty-three years over all Israel and Judah.
7 ULB ይሁን እንጂ ዳዊት የጽዮንን አምባ ያዘ፤ ይህችም አሁን የዳዊት ከተማ የሆነችው ነች፡፡ BSB BSB: Nevertheless, David captured the fortress of Zion (that is, the City of David).
8 ULB በዚያን ጊዜ ዳዊት እንደዚህ አለ፣ “ኢያቡሳውያንን የሚያጠቃ በውሃ መተላለፊያው ሽቅብ መውጣት አለበት፤ በዚያም ዳዊትን የሚጠሉትን ዕውሮችንና አንካሶችን ያገኛል፡፡” እንግዲህ ሰዎች፣ “አንካሶችና ዕውሮች ወደ ቤተ መንግሥት መግባት አይችሉም” ያሉት ከዚህ የተነሣ ነው፡፡ BSB BSB: On that day he said, “Whoever attacks the Jebusites must use the water shaft to reach the lame and blind who are despised by David.” That is why it is said, “The blind and the lame will never enter the palace.”
10 ULB የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለነበረ፣ ዳዊት እጅግ እየበረታ ሄደ፡፡ BSB BSB: And David became greater and greater, for the LORD God of Hosts was with him.
12 ULB እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ንጉሥ አድርጎ እንዳጸናውና ስለ ሕዝቡም ስለ እስራኤል ሲል መንግሥቱን ከፍ እንዳደረገለት ዳዊት አወቀ፡፡ BSB BSB: And David realized that the LORD had established him as king over Israel and had exalted his kingdom for the sake of His people Israel.
13 ULB ኬብሮንን ትቶ ወደ ኢየሩሳሌም ከመጣ በኋላ ዳዊት በኢየሩሳሌም ተጨማሪ ቁባቶችን አስቀመጠ ሚስቶችንም አገባ፤ ተጨማሪ ወንዶችና ሴቶች ልጆችም በኢየሩሳሌም ተወለዱለት፡፡ BSB BSB: After he had arrived from Hebron, David took more concubines and wives from Jerusalem, and more sons and daughters were born to him.
14 ULB በኢየሩሳሌም የተወለዱለትም ልጆች ስም፣ ሳሙስ፣ ሶባብ፣ ናታን፣ ሰሎሞን፣ BSB BSB: These are the names of the children born to him in Jerusalem: Shammua, Shobab, Nathan, Solomon,
15 ULB ኢያቤሔር፣ ኤሊሱዔ፣ ናፌቅ፣ ናፍያ፣ BSB BSB: Ibhar, Elishua, Nepheg, Japhia,
16 ULB ኤሊሳማ፣ ኤሊዳሄ፣ ኤሊፋላት ይባሉ ነበር፡፡ BSB BSB: Elishama, Eliada, and Eliphelet.
17 ULB ዳዊት በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ መቀባቱን ፍልስጥኤማውያን በሰሙ ጊዜ፣ እርሱን ለመፈለግ በሙሉ ኃይላቸው ወጡ፤ ዳዊት ግን ይህን ሰምቶ ወደ ምሽጉ ወረደ፡፡ BSB BSB: When the Philistines heard that David had been anointed king over Israel, they all went in search of him; but David learned of this and went down to the stronghold.
18 ULB በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን መጥተው በራፋይም ሸለቆ ተበታትነው ሰፈሩ፡፡ BSB BSB: Now the Philistines had come and spread out in the Valley of Rephaim.
19 ULB ዳዊትም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ ሲል ዕርዳታ ጠየቀ፣ “ፍልስጥኤማውያንን ወጥቼ ልውጋቸውን? በእነርሱስ ላይ ድል ትሰጠኛለህ?” እግዚአብሔርም ለዳዊት፣ “በፍልስጥኤማውያን ላይ በእርግጥ ድል እሰጥሃለሁና ውጋቸው” አለው፡፡ BSB BSB: So David inquired of the LORD, “Should I go up against the Philistines? Will You deliver them into my hand?” “Go up,” replied the LORD, “for I will surely deliver the Philistines into your hand.”
20 ULB ስለዚህ ዳዊት በበአልፐራሲም ወጋቸው በዚያም ድል አደረጋቸው፡፡ እርሱም፣ “የጎርፍ ውሃ ጥሶ በመውጣት እንደሚያፈራርስ እግዚአብሔርም ጠላቶቼን በፊቴ አፈራረሳቸው” በማለት ስሜቱን ገለጸ፡፡ ከዚህ የተነሣም የዚያ ቦታ ስም በአልፐራሲም ተባለ፡፡ BSB BSB: So David went to Baal-perazim, where he defeated the Philistines and said, “Like a bursting flood, the LORD has burst out against my enemies before me.” So he called that place Baal-perazim.
21 ULB ፍልስጥኤማውያን ጣዖቶቻቸውን እዚያ ትተው ስለነበር ዳዊትንና ሰዎቹን ወሰዷቸው፡፡ BSB BSB: There the Philistines abandoned their idols, and David and his men carried them away.
22 ULB ፍልስጥኤማውያን እንደ ገና መጥተው በራፋይም ሸለቆ በድጋሚ ተበታትነው ሰፈሩ፡፡ BSB BSB: Once again the Philistines came up and spread out in the Valley of Rephaim.
23 ULB ስለዚህ ዳዊት እንደገና ከእግዚአብሔር ዕርዳታ ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፣ “በፊት ለፊት በኩል አትውጋቸው፤ ይልቁኑ በስተኋላቸው በኩል በመክበብ በበለሳኑ ዛፎች ፊት ለፊት ግጠማቸው፡፡ BSB BSB: So David inquired of the LORD, who answered, “Do not march straight up, but circle around behind them and attack them in front of the balsam trees.
24 ULB በበለሳኑ ዛፎች ጫፍ ላይ የሰልፍ ጉዞ ድምፅ ስትሰማ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ለመምታት እግዚአብሔር ቀድሞ ወጥቶአልና በዚያን ጊዜ በኃይል አጥቃ” አለው፡፡ BSB BSB: As soon as you hear the sound of marching in the tops of the balsam trees, move quickly, because this will mean that the LORD has gone out before you to strike the camp of the Philistines.”
25 ULB ስለዚህም ዳዊት እግዚአብሔር እንዳዘዘው ፍልስጥኤማውያንን ከገባዖን እስከ ጌዘር ድረስ ገደላቸው፡፡ BSB BSB: So David did as the LORD had commanded him, and he struck down the Philistines all the way from Gibeon to Gezer.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.