1 ULB አንፊጶልና አጶሎንያ በተባሉ ከተሞች በኩል ካለፉ በኋላም፣ ተሰሎንቄ ወደ ተባለች ከተማ መጡ፤ በዚያም ከተማ የአይሁድ ምኵራብ ነበረ። BSB BSB: When they had passed through Amphipolis and Apollonia, they came to Thessalonica, where there was a Jewish synagogue.
2 ULB ጳውሎስም እንደ ልማዱ፣ ወደ አይሁድ ሄዶ፣ ለሦስት ሰንበታት ያህል ከቅዱሳት መጻሕፍት እየጠቀሰ ከእነርሱ ጋር ይነጋገር ነበር። BSB BSB: As was his custom, Paul went into the synagogue, and on three Sabbaths he reasoned with them from the Scriptures,
3 ULB ቅዱሳት መጻሕፍትንም እየገለጠ፣ ክርስቶስ መከራን መቀበልና ከሙታን መነሣት እንደ ነበረበት እያስረዳም፣ «ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው» ይላቸው ነበር። BSB BSB: explaining and proving that the Christ had to suffer and rise from the dead. “This Jesus I am proclaiming to you is the Christ,” he declared.
4 ULB ከአይሁድም አንዳንዶቹ መልእክቱን ተቀብለው ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ፤ በተጨማሪም ለእግዚአብሔር ያደሩ ግሪኮች፣ የከበሩ ብዙ ሴቶችና ከፍተኛ ቍጥር ያላቸው ሰዎች ከእነርሱ ጋር ሆኑ። BSB BSB: Some of the Jews were persuaded and joined Paul and Silas, along with a large number of God-fearing Greeks and quite a few leading women.
5 ULB ሌሎች ያላመኑ አይሁድ ግን፣ በቅንዓት በመነሣሣትና ክፉ ሰዎችን ከጎዳና ላይ በማሰባሰብ ሕዝብን አከማችተው ከተማዋን አወኩአት። የኢያሶንን ቤት በዐመፅ በመክበብም፣ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ለሕዝቡ ለማስረከብ ፈለጉ። BSB BSB: The Jews, however, became jealous. So they brought in some troublemakers from the marketplace, formed a mob, and sent the city into an uproar. They raided Jason’s house in search of Paul and Silas, hoping to bring them out to the people.
7 ULB ኢያሶን በቤቱ የተቀበላቸው እነዚህ ሰዎች የቄሣርን ሕግ የሚቃወሙ ናቸው፤ ኢየሱስ የሚባል ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ ነው።» BSB BSB: and Jason has welcomed them into his home. They are all defying Caesar’s decrees, saying that there is another king, named Jesus!”
8 ULB ሕዝቡና የከተማው ሹሞች እነዚህን ነገሮች ሲሰሙ፣ ታወኩ። BSB BSB: On hearing this, the crowd and city officials were greatly disturbed.
9 ULB ከኢያሶንና ከሌሎቹም የዋስትና ገንዘብ ተቀብለው ለቀቁአቸው። BSB BSB: And they collected bond from Jason and the others and then released them.
12 ULB ስለዚህ ከእነርሱ ብዙዎች አመኑ፤ በተጨማሪ አንዳንድ ተደማጭነት ያላቸው የግሪክ ሴቶችና ሌሎች ወንዶችም አመኑ። BSB BSB: As a result, many of them believed, along with quite a few prominent Greek women and men.
13 ULB በተሰሎንቄ የነበሩ አይሁድም ጳውሎስ በቤርያም ደግሞ ቃሉን እንደ ሰበከ ባወቁ ጊዜ፣ ወደዚያ ሄደው ሕዝቡን በማነሣሣት አወኩ። BSB BSB: But when the Jews from Thessalonica learned that Paul was also proclaiming the word of God in Berea, they went there themselves to incite and agitate the crowds.
14 ULB ወንድሞችም ወዲያው ጳውሎስን ወደ ባሕሩ አካባቢ እንዲሄድ አደረጉ፤ ሲላስና ጢሞቴዎስ ግን እዚያው ቆዩ። BSB BSB: The brothers immediately sent Paul to the coast, but Silas and Timothy remained in Berea.
15 ULB ጳውሎስን ይሸኙ የነበሩት ሰዎችም እስከ አቴና ድረስ ወሰዱት። ከዚያም ሲነሡ፣ ሲላስና ጢሞቴዎስ በተቻለው ፍጥነት ወደ እነሱ እንዲመጡ የሚል መልእክት ከጳውሎስ ተቀብለው ሄዱ። BSB BSB: Those who escorted Paul brought him to Athens and then returned with instructions for Silas and Timothy to join him as soon as possible.
17 ULB ስለዚህም ነገር በምኵራብ ከሚያገኛቸው አይሁድ፣ እግዚዘብሔርንም ከሚያመልኩ ሌሎች ሰዎችና ዘወትር በገበያ ቦታ ከሚያገኛቸው ሰዎች ጋር ይነጋገር ነበር። BSB BSB: So he reasoned in the synagogue with the Jews and God-fearing Gentiles, and in the marketplace with those he met each day.
18 ULB ከኤፌቆስና ከኢስጦኢኮች ወገን የሆኑ አንዳንድ ፈላስፎችም ደግሞ ጳውሎስን አገኙት። ከእነርሱም አንዳንዶች፣ «ይህ ለፍላፊ ምን እያለ ነው?» አሉ። ሌሎቹም፣ ስለ ኢየሱስና ስለ ትንሣኤው ሲሰብክ ስለ ሰሙት፣ «ስለ እንግዳ አማልክት የሚሰብክ ይመስላል» አሉ። BSB BSB: Some Epicurean and Stoic philosophers also began to debate with him. Some of them asked, “What is this babbler trying to say?” Others said, “He seems to be advocating foreign gods.” They said this because Paul was proclaiming the good news of Jesus and the resurrection.
19 ULB ከዚያም፣ «አንተ የምትናገረውን ይህን ዐዲስ ትምህርት ማወቅ እንችላለን ወይ? BSB BSB: So they took Paul and brought him to the Areopagus, where they asked him, “May we know what this new teaching is that you are presenting?
20 ULB ምክንያቱም እየሰማናቸው ያሉ ነገሮች እንግዳ ናቸው። ስለዚህ፣ የእነዚህን ነገሮች ትርጕም ማወቅ እንሻለን» አሉት። BSB BSB: For you are bringing some strange notions to our ears, and we want to know what they mean.”
21 ULB አቴናውያንና ሌሎች በዚያ የሚኖሩ እንግዶች ሁሉ ጊዜአቸውን የሚያሳልፉት በሌላ ጉዳይ ሳይሆን፣ ስለ ዐዳዲስ ነገሮች በማውራት ወይም በመስማት ነበር። BSB BSB: Now all the Athenians and foreigners who lived there spent their time doing nothing more than hearing and articulating new ideas.
23 ULB ምክንያቱም ወዲያ ወዲህ እየተመላለስሁ የምታመልኳቸውን ስመለከት፣ ላልታወቀ አምላክ የሚል ጽሑፍ የተጻፈበት አንድ መሠዊያ አይቻለሁ። እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን አምላክ እኔ እነግራችኋለሁ። BSB BSB: For as I walked around and examined your objects of worship, I even found an altar with this inscription: TO AN UNKNOWN GOD. Therefore what you worship as something unknown, I now proclaim to you.
25 ULB ለሰዎች ሕይወት፣ እስትንፋስንና ሁሉንም ነገር የሚሰጠው እርሱ ራሱ ስለ ሆነ፣ እግዚአብሔር አንዳች እንደሚያስፈልገው በሰው እጅ አይገለገልም። BSB BSB: Nor is He served by human hands, as if He needed anything, because He Himself gives everyone life and breath and everything else.
29 ULB እንግዲህ የእግዚአብሔር ልጆች ከሆንን፣ መለኮትን በሰው ጥበብና እንደ ተቀረጸ ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ አድርገን ማሰብ የለብንም። BSB BSB: Therefore, being offspring of God, we should not think that the Divine Being is like gold or silver or stone, an image formed by man’s skill and imagination.
30 ULB ስለዚህ እግዚአብሔር የአለማወቅ ጊዜያትን አሳልፎ፣ አሁን ግን በየትኛውም ስፍራ ያሉ ሰዎች ሁሉ ንስሐ እንዲገቡ ያዛል። BSB BSB: Although God overlooked the ignorance of earlier times, He now commands all people everywhere to repent.
31 ULB ምክንያቱም በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ላይ የሚፈርድበትን ቀን አዘጋጅቶአል። እግዚአብሔር ይህን ሰው ከሙታን በማስነሣቱ ለሁሉ ሰው ማረጋገጫ ሰጥቶአል።" BSB BSB: For He has set a day when He will judge the world with justice by the Man He has appointed. He has given proof of this to everyone by raising Him from the dead.”
32 ULB የአቴና ሰዎች ስለ ሙታን ትንሣኤ በሰሙ ጊዜ፣ አንዳንዶቹ በጳውሎስ ላይ አፌዙ፤ሌሎች ግን፣ «ስለዚህ ጉዳይ ዳግመኛ እንሰማሃለን» አሉት። BSB BSB: When they heard about the resurrection of the dead, some began to mock him, but others said, “We want to hear you again on this topic.”
33 ULB ከዚህ በኋላ፣ ጳውሎስ ተለይቶአቸው ሄደ፤ BSB BSB: At that, Paul left the Areopagus.
34 ULB አንዳንድ ወንዶች ግን ከእርሱ ጋር ተባብረው አመኑ፤ በእነዚህም ውስጥ የአርዮስፋጎስ አመራር አባል ዲዮናስዮስ፣ ደማሪስ የተባለች ሴትና ሌሎችም ይገኛሉ። BSB BSB: But some joined him and believed, including Dionysius the Areopagite, a woman named Damaris, and others who were with them.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.