1 ULB ፊስጦስም ወደ ክፍለ ሀገሩ ገባ፤ ከሦስት ቀንም በኋላ ከቂሣርያ ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። BSB BSB: Three days after his arrival in the province, Festus went up from Caesarea to Jerusalem,
2 ULB የካህናት አለቃውና ታዋቂ የሆኑት አይሁድ ጳውሎስን ፊስጦስ ላይ ከሰሱት፤ ለፊስጦስም በኀይል ተናገሩ። BSB BSB: where the chief priests and Jewish leaders presented their case against Paul. They urged Festus
3 ULB በመንገድም ላይ ሊገድሉት ጳውሎስን ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያስጠራው ፊስጦስን ለመኑት። BSB BSB: to grant them a concession against Paul by summoning him to Jerusalem, because they were preparing an ambush to kill him along the way.
4 ULB ፊስጦስ ግን መልሶ ጳውሎስ በቂሣርያ እስረኛ እንደ ሆነ፣ እርሱ ራሱም ወደዚያ እንደሚመለስ ተናገረ። BSB BSB: But Festus replied, “Paul is being held in Caesarea, and I myself am going there soon.
5 ULB “ስለዚህ፣ የሚችሉ ከእኛ ጋር ወደዚያ መሄድ አለባቸው። ሰውየው ያጠፋው ነገር ካለ፣ ክሰሱት” አለ። BSB BSB: So if this man has done anything wrong, let some of your leaders come down with me and accuse him there.”
7 ULB ጳውሎስም በደረሰ ጊዜ፣ ከኢየሩሳሌም የመጡት አይሁድ በአጠገቡ ቆሙ፤ በማስረጃ ማረጋገጥ ያልቻሉትን ብዙ ከባድ ክስም አቀረቡ። BSB BSB: When Paul arrived, the Jews who had come down from Jerusalem stood around him, bringing many serious charges that they could not prove.
8 ULB ጳውሎስ፣ “በአይሁድ ስምም ላይ፣ በቤተ መቅደሱም ላይ፣ በቄሣርም ላይ በደል አልፈጸምሁም” ብሎ ራሱን ተከላከለ። BSB BSB: Then Paul made his defense: “I have committed no offense against the law of the Jews or against the temple or against Caesar.”
9 ULB ፊስጦስ ግን አይሁድን ለማስደሰት ፈለገ፤ ስለሆነም፣ “እስከ ኢየሩሳሌም መውጣትና ስለ እነዚህ ነገሮች በዚያ ፍርድ እንድሰጥህ ትፈልጋለህን?” ብሎ ጳውሎስን ጠየቀው። BSB BSB: But Festus, wishing to do the Jews a favor, said to Paul, “Are you willing to go up to Jerusalem to stand trial before me on these charges?”
10 ULB ጳውሎስም እንዲህ አለ፤ “ፍርድ ሊሰጠኝ በሚገባኝ በቄሣር የፍርድ ወንበር ፊት እቆማለሁ። አንተም ደግሞ በሚገባ እንደምታውቀው፣ አንድንም አይሁዳዊ አልበደልሁም። BSB BSB: Paul replied, “I am standing before the judgment seat of Caesar, where I ought to be tried. I have done nothing wrong to the Jews, as you yourself know very well.
11 ULB ብበድልና ሞት የሚገባውን ነገር አድርጌ ቢሆን እንኳ፣ አልሞትም አልልም። እነርሱ በእኔ ላይ የሚያቀርቡት ክስ ከንቱ ከሆነ ግን፣ ማንም ለእነርሱ አሳልፎ ሊሰጠኝ አይችልም። ለቄሣር ይግባኝ ብያለሁ።” BSB BSB: If, however, I am guilty of anything worthy of death, I do not refuse to die. But if there is no truth to their accusations against me, no one has the right to hand me over to them. I appeal to Caesar!”
12 ULB ከዚያም ፊስጦስ ከሸንጎው ጋር ተነጋግሮ፣ “ለቄሣር ይግባኝ ብለሃልና ወደ ቄሣር ትሄዳለህ” ብሎ መለሰ። BSB BSB: Then Festus conferred with his council and replied, “You have appealed to Caesar. To Caesar you will go!”
13 ULB ከጥቂት ቀናትም በኋላ ንጉሥ አግሪጳና በርኒቄ ፊስጦስን ለመጐብኘት ቂሣርያ ደረሱ። BSB BSB: After several days had passed, King Agrippa and Bernice came down to Caesarea to pay their respects to Festus.
14 ULB ንጉሥ አግሪጳ በዚያ ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኋላ፣ ፊስጦስ የጳውሎስን ጉዳይ ለንጉሡ አቀረበ፤ እንዲህም አለ፤ “ፊልክ አስሮ የተወው አንድ ሰው በዚህ አለ። BSB BSB: Since they were staying several days, Festus laid out Paul’s case before the king: “There is a certain man whom Felix left in prison.
15 ULB እኔ በኢየሩሳሌም በነበርሁ ጊዜ የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሽማግሌዎች ክስ መሥርተውበት ለእኔ አመለከቱ፤ እንድፈርድበትም ለመኑኝ። BSB BSB: While I was in Jerusalem, the chief priests and elders of the Jews presented their case and requested a judgment against him.
16 ULB ለዚህም፣ የተከሰሰው ሰው በከሳሾቹ ፊት ቀርቦ ለተከሰሰበት ነገር እንዲከላከል ዕድል ሳይሰጠው አንድን ሰው አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ልማድ አይደለም ብዬ መልስ ሰጠሁ።” BSB BSB: I told them that it is not the Roman custom to hand a man over before he has had an opportunity to face his accusers and defend himself against their charges.
17 ULB ስለዚህ፣ እነርሱ በአንድ ላይ ወደዚህ በመጡ ጊዜ፣ አልዘገየሁም፤ ነገር ግን በማግስቱ በፍርድ ወንበር ተቀምጬ ሰውዬውን እንዲያመጡት አዘዝሁ። BSB BSB: So when they came here with me, I did not delay. The next day I sat on the judgment seat and ordered that the man be brought in.
18 ULB ከሳሾቹ ቆመው በከሰሱት ጊዜ፣ ካቀረቡበት ክሶች ማንኛቸውም ከባድ አይደሉም ብዬ ዐሰብሁ። BSB BSB: But when his accusers rose to speak, they did not charge him with any of the crimes I had expected.
19 ULB ይልቁንም ስለ ገዛ ራሳቸው ሃይማኖትና ጳውሎስ ሕያው ነው ስለሚለው ሞቶ ስለ ነበረው ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ነበር። BSB BSB: They only had some contentions with him regarding their own religion and a certain Jesus who had died, but whom Paul affirmed to be alive.
20 ULB ይህን ጉዳይ እንዴት እንደምመረምር ግራ ገብቶኝ ነበር፤ ስለ እነዚህ ነገሮችም በዚያ ለመፋረድ ወደ ኢየሩሳሌም ይሄድ እንደ ሆነ ጳውሎስን ጠየቅሁት። BSB BSB: Since I was at a loss as to how to investigate these matters, I asked if he was willing to go to Jerusalem and be tried there on these charges.
21 ULB ጳውሎስ ግን የንጉሠ ነገሥቱን ውሳኔ እስኪያገኝ፣ በዘብ እንዲጠበቅ ይግባኝ ባለ ጊዜ፣ ወደ ቄሣር እስክሰደው ድረስ በጥበቃ ሥር እንዲሆን አዘዝሁት።” BSB BSB: But when Paul appealed to be held over for the decision of the Emperor, I ordered that he be held until I could send him to Caesar.”
22 ULB አግሪጳ፣ “እኔ ደግሞ ይህን ሰው ልሰማው እፈልጋለሁ” ብሎ ፊስጦስን አነጋገረው። ፊስጦስም፣ “ነገ ትሰማዋለህ” አለው። BSB BSB: Then Agrippa said to Festus, “I would like to hear this man myself.” “Tomorrow you will hear him,” Festus declared.
23 ULB ስለ ሆነም፣ በማግስቱ፣ አግሪጳና በርኒቄ በታላቅ ሥነ ሥርዓት ከወታደራዊ መኮንኖችና ከከተማዋ ታዋቂ ሰዎች ጋር ወደ አዳራሹ ገቡ። በፊስጦስ ትእዛዝም ጊዜ ጳውሎስን ወደ እነርሱ አመጡት። BSB BSB: The next day Agrippa and Bernice came with great pomp and entered the auditorium, along with the commanders and leading men of the city. And Festus ordered that Paul be brought in.
24 ULB ፊስጦስም እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ እዚህ ከእኛ ጋር ያላችሁትም ሰዎች ሁሉ፣ ይህን ሰው ተመልከቱት፤ በኢየሩሳሌምና እዚህም ያሉት የአይሁድ ሕዝብ ሁሉ ከእኔ ጋር ተማከሩ፤ ይህ ሰው ከእንግዲህ ወዲያ በሕይወት መኖር የለበትም ብለውም ጮኹብኝ። BSB BSB: Then Festus said, “King Agrippa and all who are present with us, you see this man. The whole Jewish community has petitioned me about him, both here and in Jerusalem, crying out that he ought not to live any longer.
25 ULB እኔ ግን ለሞት የሚያበቃው ምንም በደል አለመፍጸሙን ዐወቅሁ፤ ነገር ግን ወደ ንጉሠ ነገሥቱ ይግባኝ በማለቱ ልሰደው ወሰንሁ። BSB BSB: But I found he had done nothing worthy of death, and since he has now appealed to the Emperor, I decided to send him.
26 ULB ሆኖም ለንጉሠ ነገሥቱ ለመጻፍ አሳማኝ ነገር የለኝም። በዚህ ምክንያት ስለ ጉዳዩ የምጽፈው ነገር እንዲኖረኝ፣ በተለይ ንጉሥ አግሪጳ ሆይ፣ ወደ አንተ አምጥቼዋለሁ። BSB BSB: I have nothing definite to write to our sovereign about him. Therefore I have brought him before all of you, and especially before you, King Agrippa, so that after this inquiry I may have something to write.
27 ULB አንድን እስረኛ መስደድና የቀረበበትን ክስም አለመግለጽ ለእኔ ምክንያታዊ ያልሆነ ይመስለኛልና።” BSB BSB: For it seems unreasonable to me to send on a prisoner without specifying the charges against him.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.