1 ULB በእነዚህ ወራት፣ የደቀ መዛሙርት ቊጥር እየበዛ በሄደ ጊዜ፣ ከግሪክ የመጡት አይሁድ በዕብራውያን ላይ ማጕረምረም ጀመሩ፤ ምክንያቱም መበለቶቻቸው በየዕለቱ የምግብ ዕደላ ላይ ቸል ተብለውባቸው ነበር። BSB BSB: In those days when the disciples were increasing in number, the Grecian Jews among them began to grumble against the Hebraic Jews because their widows were being overlooked in the daily distribution of food.
2 ULB ዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት ደቀ መዛሙርቱን ሁሉ ጠርተው እንዲህ አሏቸው፤ “የምግብ አገልግሎትን ለመስጠት ብለን የእግዚአብሔርን ቃል መተው ለእኛ ተገቢ አይደለም። BSB BSB: So the Twelve summoned all the disciples and said, “It is unacceptable for us to neglect the word of God in order to wait on tables.
3 ULB ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፣ በዚህ ኀላፊነት ላይ ልንሾማቸው የምንችል መልካም አርአያነት ያላቸውን፣ መንፈስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ መካከል ምረጡ። BSB BSB: Therefore, brothers, select from among you seven men confirmed to be full of the Spirit and wisdom. We will assign this responsibility to them
4 ULB እኛ ግን፣ ሁልጊዜ በጸሎትና በቃሉ አገልግሎት እንቀጥላለን።” BSB BSB: and will devote ourselves to prayer and to the ministry of the word.”
5 ULB ንግግራቸው ሕዝቡን ሁሉ ደስ አሰኘ። ስለዚህ እምነትና መንፈስ ቅዱስ የሞላበትን እስጢፋኖስን፣ ፊልጶስን፣ ጵሮኮሮስን፣ ኒቃሮናን፣ ጢሞናን፣ ጳርሜናንና ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን አንጾኪያዊውን ኒቆላዎስን መረጡ። BSB BSB: This proposal pleased the whole group. They chose Stephen, a man full of faith and of the Holy Spirit, as well as Philip, Prochorus, Nicanor, Timon, Parmenas, and Nicolas from Antioch, a convert to Judaism.
6 ULB አማኞቹ እነዚህን ሰዎች፣ በጸለዩላቸውና ከዚያም እጃቸውን በላያቸው በጫኑት በሐዋርያት ፊት አቀረቧቸው። BSB BSB: They presented these seven to the apostles, who prayed and laid their hands on them.
7 ULB ስለዚህም የእግዚአብሔር ቃል አደገ፤ የደቀ መዛሙርት ቊጥርም በኢየሩሳሌም ውስጥ በብዛት ጨመረ፤ ከካህናትም ብዙዎቹ ለእምነት ታዛዦች ሆኑ። BSB BSB: So the word of God continued to spread. The number of disciples in Jerusalem grew rapidly, and a great number of priests became obedient to the faith.
8 ULB እስጢፋኖስ ጸጋንና ኀይልን ተሞልቶ፣ በሕዝቡ መካከል ታላላቅ ድንቆችንና ምልክቶችን ያደርግ ነበር። BSB BSB: Now Stephen, who was full of grace and power, was performing great wonders and signs among the people.
10 ULB ነገር ግን ሰዎቹ እስጢፋኖስ የተናረገረበትን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም። BSB BSB: but they could not stand up to his wisdom or the Spirit by whom he spoke.
11 ULB ከዚያም፣ “እስጢፋኖስ በሙሴና በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ሲናገር ሰምተናል” እንዲሉ አንዳንድ ሰዎችን በምስጢር አሳመኑ። BSB BSB: Then they prompted some men to say, “We heard Stephen speak words of blasphemy against Moses and against God.”
12 ULB ሰዎቹን፣ ሽማግሌዎቹን፣ የሕግ መምህራኖቹንም አነሣሡ፤ እስጢፋኖስንም ይዘው ወደ ሸንጎው አቀረቡት። BSB BSB: So they stirred up the people, elders, and scribes and confronted Stephen. They seized him and brought him before the Sanhedrin,
13 ULB እንዲህ ብለው የሚናገሩ ሐሰተኛ ምስክሮችንም አመጡ፤ “ይህ ሰው ይህን ቅዱስ ስፍራና ሕጉን ተቃውሞ መናገርን አያቆምም። BSB BSB: where they presented false witnesses who said, “This man never stops speaking against this holy place and against the law.
14 ULB ምክንያቱም ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል፤ ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዐትም ይለውጠዋል ሲል ሰምተነዋል።” BSB BSB: For we have heard him say that Jesus of Nazareth will destroy this place and change the customs that Moses handed down to us.”
15 ULB በሸንጎው ውስጥ የተቀመጡት ሁሉ አተኵረው ተመለከቱት፤ ፊቱም እንደ መልአክ ፊት ሆኖ አዩት። BSB BSB: All who were sitting in the Sanhedrin looked intently at Stephen, and they saw that his face was like the face of an angel.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.