1 ULB ሳውል በእስጢፋኖስ ሞት ተስማምቶ ነበር። በዚያም ጊዜ በኢየሩሳሌም በነበረችዋ ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ተነሣ፤ አማኞችም ሁሉ ከሐዋርያት በቀር በይሁዳና በሰማርያ ተበታተኑ። BSB BSB: And Saul was there, giving approval to Stephen’s death. On that day a great persecution broke out against the church in Jerusalem, and all except the apostles were scattered throughout Judea and Samaria.
2 ULB በመንፈሳዊ ነገር የተጉ ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ መሪር ልቅሶም አለቀሱለት። BSB BSB: God-fearing men buried Stephen and mourned deeply over him.
3 ULB ሳውል ግን ቤተ ክርስቲያንን በጣም ጐዳ፤ ከቤት ወደ ቤት በመሄድም ክርስቲያን ወንዶችንና ሴቶችን ጐትቶ አወጣቸው፤ ወኅኒ ቤት ውስጥም አስገባቸው። BSB BSB: But Saul began to destroy the church. Going from house to house, he dragged off men and women and put them in prison.
4 ULB የተበታተኑት አማኞች ግን ቃሉን እየሰበኩ በየቦታው ዞሩ። BSB BSB: Those who had been scattered preached the word wherever they went.
5 ULB ፊልጶስ ወደ ሰማርያ ከተማ ወረደ፣ ለሕዝቡም ክርስቶስን ሰበከላቸው። BSB BSB: Philip went down to a city in Samaria and proclaimed the Christ to them.
6 ULB እጅግ ብዙ ሰዎች ፊልጶስን ሲሰሙትና ያደረጋቸውንም ምልክቶች ሲያዩ፣ በአንድነት እርሱ ለተናገረው ትኵረት ሰጡ። BSB BSB: The crowds all paid close attention to Philip’s message and to the signs they saw him perform.
7 ULB ምክንያቱም ከብዙ ሰዎች ርኩሳን መናፍስት እየጮኹ ወጥተው፣ አያሌ ሽባዎችና ዐንካሶችም ተፈውሰው ነበር። BSB BSB: With loud shrieks, unclean spirits came out of many who were possessed, and many of the paralyzed and lame were healed.
8 ULB ስለዚህ በዚያች ከተማ ውስጥ ብዙ ደስታ ነበር። BSB BSB: So there was great joy in that city.
9 ULB ነገር ግን በዚያች ከተማ ውስጥ ቀደም ሲል የጥንቈላ ሥራ ይሠራ የነበረ ሲሞን የሚባል ሰው ነበረ፤ ተፈላጊ ሰው እንደ ሆነ እየተናገረ የሰማርያን ሰዎች ያስደንቅ ነበር። BSB BSB: Prior to that time, a man named Simon had practiced sorcery in the city and astounded the people of Samaria. He claimed to be someone great,
10 ULB ሳምራውያን በሙሉ ከትንሹ እስከ ትልቁ፣ “ይህ ሰው ታላቅ የሚባለው የእግዚአብሔር ኀይል ነው” እያሉ በሚገባ ያደምጡት ነበር። BSB BSB: and all the people, from the least to the greatest, heeded his words and said, “This man is the divine power called the Great Power.”
11 ULB በጥንቈላ ሥራው ለረጅም ጊዜ ያስገርማቸው ስለ ነበር አደመጡት። BSB BSB: They paid close attention to him because he had astounded them for a long time with his sorcery.
12 ULB ስለ እግዚአብሔር መንግሥትና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ፊልጶስ የሰበከውን ወንጌል ሲያምኑ ግን ወንዶችም ሴቶችም ተጠመቁ። BSB BSB: But when they believed Philip as he preached the gospel of the kingdom of God and the name of Jesus Christ, they were baptized, both men and women.
13 ULB ሲሞንም ደግሞ አመነ፤ ከተጠመቀም በኋላ ከፊልጶስ ጋር መሆንን ቀጠለ፤ የተደረጉ ምልክቶችንና ታላላቅ ተኣምራትን ባየ ጊዜም ተደነቀ። BSB BSB: Even Simon himself believed and was baptized. He followed Philip closely and was astounded by the great signs and miracles he observed.
14 ULB በኢየሩሳሌም የነበሩ ሐዋርያት ሰማርያ የእግዚአብሔርን ቃል የተቀበለች መሆኗን ሲሰሙ፣ ጴጥሮስንና ዮሐንስን ላኩላቸው። BSB BSB: When the apostles in Jerusalem heard that Samaria had received the word of God, they sent Peter and John to them.
15 ULB እነርሱም እዚያ ወርደው መንፈስ ቅዱስን እንዲቀበሉ ጸለዩላቸው። BSB BSB: On their arrival, they prayed for them to receive the Holy Spirit.
16 ULB መንፈስ ቅዱስ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በማንኛቸውም ላይ አልወረደም ነበርና፣ እነርሱ በጌታ ኢየሱስ ስም ብቻ ተጠምቀው ነበር። BSB BSB: For the Holy Spirit had not yet fallen upon any of them; they had simply been baptized into the name of the Lord Jesus.
17 ULB ከዚያም ጴጥሮስና ዮሐንስ እጃቸውን ጫኑባቸው፣ መንፈስ ቅዱስንም ተቀበሉ። BSB BSB: Then Peter and John laid their hands on them, and they received the Holy Spirit.
18 ULB በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንደሚሰጥ ሲያይ፣ ሲሞን ገንዘብ አቀረበላቸው። BSB BSB: When Simon saw that the Spirit was given through the laying on of the apostles’ hands, he offered them money.
19 ULB “እኔም እጁን የምጭንበት ሰው ሁሉ መንፈስ ቅዱስን መቀበል እንዲችል ይህን ሥልጣን ስጡኝ” አላቸው። BSB BSB: “Give me this power as well,” he said, “so that everyone on whom I lay my hands may receive the Holy Spirit.”
20 ULB ነገር ግን ጴጥሮስ እንዲህ አለው፤ “የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ ለማግኘት አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ። BSB BSB: But Peter replied, “May your silver perish with you, because you thought you could buy the gift of God with money!
21 ULB ልብህ ለእግዚአብሔር የቀና አይደለምና በዚህ ጉዳይ ውስጥ ዕድል ወይም ድርሻ የለህም። BSB BSB: You have no part or share in our ministry, because your heart is not right before God.
22 ULB እንግዲህ ለዚህ ክፋትህ ንስሓ ግባ፤ ምናልባትም ለልብህ ዐሳብ ይቅር ይልህ እንደ ሆነ ጌታን ለምን። BSB BSB: Repent, therefore, of your wickedness, and pray to the Lord. Perhaps He will forgive you for the intent of your heart.
23 ULB በኀጢአት እስራትና በመራርነት መርዝ ውስጥ እንዳለህ አያለሁና።” BSB BSB: For I see that you are poisoned by bitterness and captive to iniquity.”
24 ULB ሲሞንም መልሶ፣ “ከተናገራችኋቸው አንዱም በእኔ ላይ እንዳይፈጸም ወደ ጌታ ጸልዩልኝ” አላቸው። BSB BSB: Then Simon answered, “Pray to the Lord for me, so that nothing you have said may happen to me.”
25 ULB ጴጥሮስና ዮሐንስ ከመሰከሩና የጌታን ቃል ከተናገሩ በኋላ፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ፤ በመንገድም ለብዙ የሰማርያ መንደሮች ወንጌልን ሰበኩ። BSB BSB: And after Peter and John had testified and spoken the word of the Lord, they returned to Jerusalem, preaching the gospel in many of the Samaritan villages.
27 ULB እርሱም ተነሣና ሄደ። እነሆ፣ በኢትዮጵያውያን ንግሥት በሕንደኬ ሥር ትልቅ ሥልጣን የነበረው አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ነበረ። ሰውዬው በንግሥቲቱ ንብረት ሁሉ ላይ ኀላፊነት ነበረው። ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር። BSB BSB: So he started out, and on his way he met an Ethiopian eunuch, a court official in charge of the entire treasury of Candace, queen of the Ethiopians. He had gone to Jerusalem to worship,
28 ULB ከኢየሩሳሌም በመመለስ ላይ ሳለ፣ በሠረገላው ላይ ተቀምጦ ትንቢተ ኢሳይያስን እያነበበ ነበር። BSB BSB: and on his return was sitting in his chariot reading Isaiah the prophet.
29 ULB መንፈስ ፊልጶስን፣ “ሂድ ወደዚህ ሠረገላ ቅረብ” አለው። BSB BSB: The Spirit said to Philip, “Go over to that chariot and stay by it.”
31 ULB ኢትዮጵያዊውም፣ “የሚመራኝ ከሌለ እንዴት ልረዳው እችላለሁ?” አለው። ወደ ሠረገላው እንዲወጣና ዐብሮት እንዲቀመጥ ፊልጶስን ለመነው። BSB BSB: “How can I,” he said, “unless someone guides me?” And he invited Philip to come up and sit with him.
33 ULB በውርደቱ ፍርዱ ተወገደ፤ ትውልዱን ማን ይናገራል? ሕይወቱ ከምድር ተወግዶአልና።” BSB BSB: In His humiliation He was deprived of justice. Who can recount His descendants? For His life was removed from the earth.”
34 ULB ጃንደረባው ፊልጶስን፣ “እባክህ ነቢዩ ስለ ማን ነው የሚናገረው? ስለ ራሱ ወይስ ስለ ሌላ ነው?” አለው። BSB BSB: “Tell me,” said the eunuch, “who is the prophet talking about, himself or someone else?”
35 ULB ፊልጶስም መናገር ጀመረ፤ ከዚህም ከኢሳይያስ መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ሰበከው። BSB BSB: Then Philip began with this very Scripture and told him the good news about Jesus.
36 ULB እየሄዱ ሳሉ ውሃ አለበት ዘንድ ደረሱ፤ ጃንደረባው፣ “ተመልከት፣ እዚህ ውሃ አለ፤ እንዳልጠመቅ ምን ይከለክለኛል?” አለ። BSB BSB: As they traveled along the road and came to some water, the eunuch said, “Look, here is water! What is there to prevent me from being baptized?”
37 ULB ፊልጶስም፣ “በፍጹም ልብህ ካመንህ፣ መጠመቅ ትችላለህ” አለ። ኢትዮጵያዊውም መልሶ፣ “ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ አምናለሁ” አለ። BSB BSB: Not in the BSB
38 ULB ኢትዮጵያዊው ሠረገላው እንዲቆም አዘዘና፣ ፊልጶስም ጃንደረባውም ወደ ውሃው ወረዱ፤ ፊልጶስም አጠመቀው። BSB BSB: And he gave orders to stop the chariot. Then both Philip and the eunuch went down into the water, and Philip baptized him.
39 ULB ከውሃው ውስጥ ሲወጡ፣ የጌታ መንፈስ ፊልጶስን ወሰደው፤ ጃንደረባውም ከዚያ ወዲያ አላየውም፤ ደስ ብሎትም ጕዞውን ቀጠለ። BSB BSB: When they came up out of the water, the Spirit of the Lord carried Philip away, and the eunuch saw him no more, but went on his way rejoicing.
40 ULB ነገር ግን ፊልጶስ በአዛጦን ታየ። በዚያ አገር ውስጥ በማለፍ ቂሣርያ እስኪደርስ ድረስ፣ ለከተሞች ሁሉ ወንጌልን ሰበከ። BSB BSB: But Philip appeared at Azotus and traveled through that region, preaching the gospel in all the towns until he came to Caesarea.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.