1 ULB ብልቱ የተቀጠቀጠ ወይም የተቆረጠ ማናቸውም ሰው ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። BSB BSB: No man with crushed or severed genitals may enter the assembly of the LORD.
2 ULB ዲቃላም ይሁን፥ የዲቃላው ዘር የሆነ ሁሉ እስከ አሥር ትውልድ ድረስ እንኳን ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። BSB BSB: No one of illegitimate birth may enter the assembly of the LORD, nor may any of his descendants, even to the tenth generation.
3 ULB አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወይም ማናቸውም የእርሱ ዘር፥ እስከ አሥር ትውልድ እንኳ ቢሆን ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ አይግባ። BSB BSB: No Ammonite or Moabite or any of their descendants may enter the assembly of the LORD, even to the tenth generation.
4 ULB ምክንያቱም ከግብፅ ከወጣችሁ በኋላ በጉዞ ላይ በነበራችሁበት ጊዜ እህልና ውሃ ይዘው አልተቀበሏችሁም። በመስጴጦምያ በምትገኘው በፐቶር ይኖር የነበረውን የቢዖርን ልጅ በለዓምም እናንተን እንዲረግም በገንዘብ ገዙት። BSB BSB: For they did not meet you with food and water on your way out of Egypt, and they hired Balaam son of Beor from Pethor in Aram-naharaim to curse you.
5 ULB ነገር ግን እግዚአብሔር አምላካችሁ በብዓምን አልሰማውም፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ስለሚወዳችሁ ርግማኑን ወደ በረከት አደረገላችሁ። BSB BSB: Yet the LORD your God would not listen to Balaam, and the LORD your God turned the curse into a blessing for you, because the LORD your God loves you.
6 ULB በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ ሰላምን ለእነርሱ አትመኙ። BSB BSB: You are not to seek peace or prosperity from them as long as you live.
7 ULB ወንድማችሁ ስለ ሆነ ኤዶማዊውን አትጸየፈው፤ መጻተኛ ሆናችሁ በአገሩ ኖራችኋልና ግብፃዊውን አትጥሉት። BSB BSB: Do not despise an Edomite, for he is your brother. Do not despise an Egyptian, because you lived as a foreigner in his land.
8 ULB ለእነርሱ የተወለዳቸው የሦስተኛው ትውልድ ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ መግባት ይችላሉ። BSB BSB: The third generation of children born to them may enter the assembly of the LORD.
9 ULB ጠላታችሁን ለመውጋት ወጥታችሁ በሰፈራችሁ ጊዜ ከማናቸውም ርኩሰት ራሳችሁን ጠብቁ። BSB BSB: When you are encamped against your enemies, then you shall keep yourself from every wicked thing.
10 ULB ከመካከላችሁ ሌሊት ዘር በማፍሰስ የረከስሰው ቢኖር፥ ከሰፈር ወጥቶ እዚያው ይቆይ። BSB BSB: If any man among you becomes unclean because of a nocturnal emission, he must leave the camp and stay outside.
11 ULB እየመሸ ሲመጣ ግን ገላውን ይታጠብ ፀሐይ ስትጠልቅም ወደ ሰፈሩ ይመለስ። BSB BSB: When evening approaches, he must wash with water, and when the sun sets he may return to the camp.
12 ULB ለመጸዳጃ የሚሆንህን ቦታ ከሰፈር ውጭ አዘጋጅ። ከትጥቅህም ጋር መቆፍሪያ ያዝ፥ BSB BSB: You must have a place outside the camp to go and relieve yourself.
13 ULB በምትጸዳዳበት ጊዜ አፈር ቆፍረህ በዐይነ ምድርህ ላይ መልስበት። BSB BSB: And you must have a digging tool in your equipment so that when you relieve yourself you can dig a hole and cover up your excrement.
14 ULB እግዚአብሔር አምላክህ ሊጠብቅህ ጠላቶህንም በእጅህ አሳልፎ ሊሰጥህ በሰፈር ውስጥ ስለሚዘዋወር በመካከልህ አንዳች ነውር አይቶ ከአንተ እንዳይመለስ፥ ሰፈርህ የተቀደሰ ይሁን። BSB BSB: For the LORD your God walks throughout your camp to protect you and deliver your enemies to you. Your camp must be holy, lest He see anything unclean among you and turn away from you.
16 ULB ለአሳዳሪው አሳልፋችሁ አትስጡት፥ ደስ በሚያሰኘው ቦታን ራሱ በመረጠው ከተማ በመካከላችሁ ይኑር፤ እናንተም አታስጨንቁት። BSB BSB: Let him live among you wherever he chooses, in the town of his pleasing. Do not oppress him.
17 ULB ወንድ ወይም ሴት እስራኤላዊ የቤተ ጣዖት አመንዝራ አይኑራችሁ። BSB BSB: No daughter or son of Israel is to be a shrine prostitute.
18 ULB ለዝሙት አዳሪ ሴት ወይም ለወንድ ዝሙተኛ የተከፈለውን ዋጋ ለማናቸውም ስእለት አድርጋችሁ ለመስጠት ወደ እግዚአብሔር ወደ አምላካችሁ ቤት አታምጡ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ ሁለቱንም ይጸየፋቸዋልና። BSB BSB: You must not bring the wages of a prostitute, whether female or male, into the house of the LORD your God to fulfill any vow, because both are detestable to the LORD your God.
19 ULB የገንዘብ፥ የእህል ወይም የማንኛውንም ነገር ወለድ ለማግኘት ለወንድማችሁ በወለድ አታበድሩ። ባዕድ ለሆነ ሰው በወለድ ማበደር ትችላላችሁ። BSB BSB: Do not charge your brother interest on money, food, or any other type of loan.
20 ULB ነገር ግን ልትወርሱአት በምትገቡባት ምድር እጃችሁ በሚነካው በማናቸውም ነገር እግዚአብሔር አምላካችሁ እንዲባርካችሁ ለእስራኤልዊ ወንድማችሁ በወለድ አታበድሩት። BSB BSB: You may charge a foreigner interest, but not your brother, so that the LORD your God may bless you in everything to which you put your hand in the land that you are entering to possess.
21 ULB ለእግዚአብሔር ለአምልካችሁ ስእለት ከተሳላችሁ እግዚአብሔር አምላካችሁ አጥብቆ ከእናንተ ይሻዋልና፤ ኃጢአት እንዳይሆንባችሁ ለመክፈል አትዘግዩ። BSB BSB: If you make a vow to the LORD your God, do not be slow to keep it, because He will surely require it of you, and you will be guilty of sin.
22 ULB ሳትሳሉ ብትቀሩ ግን በደለኛ አትሆኑም። በአንደበታችሁ የተናገራችሁትን ሁሉ ለመፈጸም ጠንቃቃ ሁኑ፥ BSB BSB: But if you refrain from making a vow, you will not be guilty of sin.
23 ULB ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር በገዛ አንደበታችሁ ፈቅዳችሁ ስእለት ተስላችኋልና። BSB BSB: Be careful to follow through on what comes from your lips, because you have freely vowed to the LORD your God with your own mouth.
24 ULB ወደ ባልንጀራችሁ የወይን ተክል ቦታ በምትገቡበት ጊዜ ያሰኛችሁን ያህል መብላት ትችላላችሁ፤ ነገር ግን አንዳችም በዕቃችሁ አትያዙ። BSB BSB: When you enter your neighbor’s vineyard, you may eat your fill of grapes, but you must not put any in your basket.
25 ULB ወደ ባልንጀራችሁ እርሻ በምትገቡበት ጊዜ እሸት መቅጠፍ ትችላላችሁ፤ በሰብሉ ላይ ግን ማጭድ አታሳርፉበት። BSB BSB: When you enter your neighbor’s grainfield, you may pluck the heads of grain with your hand, but you must not put a sickle to your neighbor’s grain.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.