1 ULB ሙሴና የእስራኤል አለቆች ሕዝቡን እንዲህ ብለው አዘዙ፦ ዛሬ የማዛችሁን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ጠብቁ። BSB BSB: Then Moses and the elders of Israel commanded the people: “Keep all the commandments I am giving you today.
2 ULB አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ጥቂት ትልልቅ ድንጋዮችን አቁሙና በኖራ ለስኑአቸው። BSB BSB: And on the day you cross the Jordan into the land that the LORD your God is giving you, set up large stones and coat them with plaster.
3 ULB የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ማርና ወተት ወደምታፈሰው፥ አምላካችሁ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን ስትሻገሩ የዚህን ሕግ ቃላት ሁሉ ጻፉባቸው። BSB BSB: Write on them all the words of this law when you have crossed over to enter the land that the LORD your God is giving you, a land flowing with milk and honey, just as the LORD, the God of your fathers, has promised you.
4 ULB ዮርዳኖስን እንደ ተሻገራችሁም ዛሬ ባዘዙአችሁ መሠረት እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ ላይ ትከሉአቸው በኖራም ለስኑአቸው። BSB BSB: And when you have crossed the Jordan, you are to set up these stones on Mount Ebal, as I am commanding you today, and you are to coat them with plaster.
5 ULB እዚያም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የድንጋይ መሠዊያ ሥራ፥ በድንጋዮቹም ላይ ማናቸውንም የብረት መሣሪያ አታሳርፉባቸው። BSB BSB: Moreover, you are to build there an altar to the LORD your God, an altar of stones. You must not use any iron tool on them.
6 ULB የእግዚአብሔር የአምላካችሁን መሠዊያ ካልተጠረበ ድንጋይ ሥሩ፥ በላዩም ለእግዚአብሔር ለአምላካችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡበት። BSB BSB: You shall build the altar of the LORD your God with uncut stones and offer upon it burnt offerings to the LORD your God.
7 ULB በላዩም የኅብረት መሥዋዕት ሠዉ፤ ብሉም፤ በእግዚአብሔር በአምላካችሁ ፊት ደስ ይበላችሁ። BSB BSB: There you are to sacrifice your peace offerings, eating them and rejoicing in the presence of the LORD your God.
8 ULB በድንጋዮቹም ላይ የዚህ ሕግ ቃላት ሁሉ ግልጽ አድርጋችሁ ጻፉባቸው። BSB BSB: And you shall write distinctly upon these stones all the words of this law.”
9 ULB ሙሴና ሌዋውያን ካህናትም፥ ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ እስራኤል ሆይ፥ ጸጥ ብላችሁ አድምጡ! እናንተ ዛሬ የእግዚአብሔር የአላካችሁ ሕዝብ ሆናችኋል። BSB BSB: Then Moses and the Levitical priests spoke to all Israel: “Be silent, O Israel, and listen! This day you have become the people of the LORD your God.
10 ULB ስለዚይም እግዚአብሔር አምላካችሁን ታዘዙ፥ ዛሬ የሚሰጣችሁን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ጠብቁ። BSB BSB: You shall therefore obey the voice of the LORD your God and follow His commandments and statutes I am giving you today.”
11 ULB ሙሴ በዚያኑ ዕለት ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዘ፦ BSB BSB: On that day Moses commanded the people:
12 ULB ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ ስምዖን፥ ሌዊ፥ ይሁዳ፥ ይሳኮር፥ ዮሴፍና ብንያም ወገኖች ሕዝቡን ለመባረክ በገሪዛን ተራራ ላይ ይቁሙ። BSB BSB: “When you have crossed the Jordan, these tribes shall stand on Mount Gerizim to bless the people: Simeon, Levi, Judah, Issachar, Joseph, and Benjamin.
14 ULB ሌዋውያን ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብለው ይናገሩ፦ BSB BSB: Then the Levites shall proclaim in a loud voice to every Israelite:
16 ULB አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገም ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። BSB BSB: ‘Cursed is he who dishonors his father or mother.’ And let all the people say, ‘Amen!’
17 ULB የባልንጀራውን የድንበር ድንጋይ ከቦታው የሚያንቀሳቅስ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። BSB BSB: ‘Cursed is he who moves his neighbor’s boundary stone.’ And let all the people say, ‘Amen!’
18 ULB ዐይነ ስዉርን በተሳሳተ መንገድ የሚመራ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። BSB BSB: ‘Cursed is he who lets a blind man wander in the road.’ And let all the people say, ‘Amen!’
19 ULB በመጻተኛው፥ አባት በሌለውና ባል በሞተባት ላይ ፍትሕ የሚያዛባ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። BSB BSB: ‘Cursed is he who withholds justice from the foreigner, the fatherless, or the widow.’ And let all the people say, ‘Amen!’
20 ULB ከአባቱ ሚስት ጋር የሚተኛ የተረገመ ይሁን፤ የአባቱን መኝታ ያረክሳልና። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። BSB BSB: ‘Cursed is he who sleeps with his father’s wife, for he has violated his father’s marriage bed.’ And let all the people say, ‘Amen!’
21 ULB ከማናቸውም እንስሳ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚያደርግ የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ፤ አሜን ይበል። BSB BSB: ‘Cursed is he who lies with any animal.’ And let all the people say, ‘Amen!’
22 ULB የአባቱ ወይም የእናቱ ልጅ ከሆነችው ከእኅቱ ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን። BSB BSB: ‘Cursed is he who sleeps with his sister, the daughter of his father or the daughter of his mother.’ And let all the people say, ‘Amen!’
23 ULB ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። ከሚስቱ እናት ጋር የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚፈጽም የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። BSB BSB: ‘Cursed is he who sleeps with his mother-in-law.’ And let all the people say, ‘Amen!’
24 ULB በድብቅ ባልንጀራውን የሚገድል የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። BSB BSB: ‘Cursed is he who strikes down his neighbor in secret.’ And let all the people say, ‘Amen!’
25 ULB ንጹሕውን ሰው ለመግደል ጉቦ የሚቀበል የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። BSB BSB: ‘Cursed is he who accepts a bribe to kill an innocent person.’ And let all the people say, ‘Amen!’
26 ULB የዚህን ሕግ ቃሎች በመፈጸም የማይጸና የተረገመ ይሁን። ሕዝቡም ሁሉ አሜን ይበል። BSB BSB: ‘Cursed is he who does not put the words of this law into practice.’ And let all the people say, ‘Amen!’
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.