1 ULB እኔም በልቤ፥ "ና እንግዲህ፥ በደስታ እፈትንሃለሁ። ስለዚህ እንዳሻህ ተደሰት" አልኩ። ግን ተመልከት፥ ይህም ደግሞ ልክ የአፍታ እስትንፋስ ነበር። BSB BSB: I said to myself, “Come now, I will test you with pleasure; enjoy what is good!” But it proved to be futile.
2 ULB ስለ ሣቅ "እርሱ ዕብደት ነው"፥ ስለ ደስታም "ምን ይጠቅማል?" አልኩ። BSB BSB: I said of laughter, “It is folly,” and of pleasure, “What does it accomplish?”
3 ULB በወይን ጠጅ ራሴን እንዴት እንደማስደስተው በልቤ መረመርሁ። እስካሁን ሞኝነትን ብይዛትም አዕምሮዬ በጥበብ እንዲመራ ተውኩት። ሰዎች በሕይወት ዘመናቸው ከሰማይ በታች ሊያደርጉት የሚገባቸውን መልካም ነገር ለማግኘት ፈለግሁ። BSB BSB: I sought to cheer my body with wine and to embrace folly—my mind still guiding me with wisdom—until I could see what was worthwhile for men to do under heaven during the few days of their lives.
4 ULB ታላላቅ ነገሮችን አከናወንኩ። ለራሴ ቤቶችን ሠራሁ፥ ወይንንም ተከልሁ። BSB BSB: I expanded my pursuits. I built houses and planted vineyards for myself.
5 ULB የአትክልትና የመዝናኛ ቦታዎችን ለራሴ ሠራሁ፤ በእነርሱም ላይ ሁሉንም ዓይነት የፍሬ ዛፎች ተከልሁባቸው። BSB BSB: I made gardens and parks for myself, where I planted all kinds of fruit trees.
6 ULB ዛፎች የሚያድጉበትን ዱር የሚያጠጡ የውሃ ገንዳዎችን አበጀሁ። BSB BSB: I built reservoirs to water my groves of flourishing trees.
7 ULB ወንድና ሴት ባሪያዎችን ገዛሁ፤ በቤተ መንግሥቴ የተወለዱ ባሪያዎችም ነበሩኝ። ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነገሡት ሁሉ እጅግ የሚበልጥ የከብት መንጋና የቤት እንስሶች ነበሩኝ። BSB BSB: I acquired menservants and maidservants, and servants were born in my house. I also owned more herds and flocks than anyone in Jerusalem before me,
8 ULB ብርና ወርቅን፥ የነገሥታቱንና የአውራጃዎቹንም ሃብት ለራሴ አከማቸሁ። ለእኔ ለራሴ ወንድና ሴት አዝማሪዎች ነበሩኝ፤ እጅግ በበዙት ሚስቶቼና ቁባቶቼም በምድር ማንኛውንም ሰው ሊያስደስተው የሚችለውን ነገር አደረግሁ። BSB BSB: and I accumulated for myself silver and gold and the treasure of kings and provinces. I gathered to myself male and female singers, and the delights of the sons of men—many concubines.
9 ULB ከእኔ በፊት በኢየሩሳሌም ከነበሩት ሁሉ ይልቅ ታላቅና ባለጸጋ ሆንኩ፥ ጥበቤም ከእኔው ጋር ቆየች። BSB BSB: So I became great and surpassed all in Jerusalem who had preceded me; and my wisdom remained with me.
10 ULB ዓይኖቼ የፈለጉትን ማናቸውንም ነገር አልከለከልኳቸውም። በምሠራው ሁሉ ልቤ ስለ ተደሰተና ደስታ የሠራሁት ሥራ ሁሉ ብድራት ስለ ነበረ ከየትኛውም ደስታ ልቤን አልከለከልኩትም። BSB BSB: Anything my eyes desired, I did not deny myself. I refused my heart no pleasure. For my heart took delight in all my work, and this was the reward for all my labor.
11 ULB ከዚያም እጆቼ ያከናወኗቸውን ተግባራት ሁሉ፥ እኔም የሠራኋቸውን ሥራዎች ተመለከትኩ፥ ነገር ግን ሁሉም እንፋሎትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ነበር። በእርሱ ውስጥ ከፀሐይ በታች አንድም ትርፍ አልነበረበትም። BSB BSB: Yet when I considered all the works that my hands had accomplished and what I had toiled to achieve, I found everything to be futile, a pursuit of the wind; there was nothing to be gained under the sun.
12 ULB ከዚያም ጥበብን፥ ደግሞም ዕብደትንና ሞኝነትን ለመመርመር ራሴን መለስኩ። አስቀድሞ ከተደረገው በቀር ከዚህኛው ንጉሥ በኋላ የሚመጣው ንጉሥ ምን ለማድረግ ይችላል? BSB BSB: Then I turned to consider wisdom and madness and folly; for what more can the king’s successor do than what has already been accomplished?
13 ULB ከዚያም ልክ ብርሃን ከጨለማ እንደሚሻል ጥበብም ከሞኝነት የሚሻል መሆኑን መረዳት ጀመርሁ። BSB BSB: And I saw that wisdom exceeds folly, just as light exceeds darkness:
14 ULB ጥበበኛ ሰው የሚሄድበትን እንዲያውቅ ዓይኖቹን በራሱ ላይ አድርጎ ይጠቀምባቸዋል፥ ሞኙ ግን በጨለማ ይሄዳል፥ ቢሆንም ለእያንዳንዱ የተዘጋጀለት ፍጻሜ ተመሳሳይ መሆኑን አውቃለሁ። BSB BSB: The wise man has eyes in his head, but the fool walks in darkness. Yet I also came to realize that one fate overcomes them both.
15 ULB እኔም በልቤ፥ "በሞኙ ላይ የሚደርሰው በእኔም ላይ ይደርሳል። ስለዚህ በጣም ጥበበኛ ብሆን ምን ልዩነት ያመጣል?" አልኩ። "ይህም ደግሞ እንፋሎት ብቻ ነው" ብዬ በልቤ ደመደምኩኝ። BSB BSB: So I said to myself, “The fate of the fool will also befall me. What then have I gained by being wise?” And I said to myself that this too is futile.
16 ULB ምክንያቱም ጠቢቡም እንደ ሞኙ ለዘላለም አይታሰብም። በሚመጣው ዘመን ሁሉም ነገር የተረሳ ይሆናል። ልክ ሞኙ እንደሚሞት ጠቢቡም ሰው ይሞታል። BSB BSB: For there is no lasting remembrance of the wise, just as with the fool, seeing that both will be forgotten in the days to come. Alas, the wise man will die just like the fool!
17 ULB ከፀሐይ በታች የሚሠራው ሥራ ሁሉ ክፉ ስለሆነብኝ ሕይወትን ጠላሁ። ይህም የሆነው ሁሉም ነገር እንፋሎትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ስለሆነ ነው። BSB BSB: So I hated life, because the work that is done under the sun was grievous to me. For everything is futile and a pursuit of the wind.
18 ULB ከፀሐይ በታች በሥራ የደከምኩበትን ሁሉ ጠላሁ፥ ከእኔ በኋላ ለሚመጣው ሰው ልተውለት የግድ ነውና። BSB BSB: I hated all for which I had toiled under the sun, because I must leave it to the man who comes after me.
19 ULB እርሱ ጥበበኛ ወይም ሞኝ ይሆን እንደሆነ ማን ያውቃል? ሆኖም ከሰማይ በታች በጥበቤ በሠራሁት ሁሉ ላይ አዛዥ ይሆናል። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው። BSB BSB: And who knows whether that man will be wise or foolish? Yet he will take over all the labor at which I have worked skillfully under the sun. This too is futile.
20 ULB ከዚህ የተነሣ ከፀሐይ በታች በሠራሁት ሥራ ሁሉ ላይ ልቤ ተስፋ መቁረጥ ጀመረ። BSB BSB: So my heart began to despair over all the labor that I had done under the sun.
21 ULB ምክንያቱም አንዱ በጥበብ፥ በእውቀትና በብልሃት ይሠራ ይሆናል፥ ነገር ግን የነበረውን ነገር ሁሉ አንድም ላልለፋበት ሰው ይተውለታል። BSB BSB: When there is a man who has labored with wisdom, knowledge, and skill, and he must give his portion to a man who has not worked for it, this too is futile and a great evil.
22 ULB ይህም ደግሞ እንፋሎትና እጅግ የሚያሳዝን ነው። ከፀሐይ በታች ሰው ተግቶ በመሥራቱና ሥራውን ሁሉ ለማጠናቀቅ በልቡ በመሞከሩ ምን ያተርፋል? BSB BSB: For what does a man get for all the toil and striving with which he labors under the sun?
23 ULB የየዕለት ሥራው በስቃይና በውጥረት የተሞላ ነው፥ ስለዚህ ነፍሱ በሌሊት እረፍት አታገኝም። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው። BSB BSB: Indeed, all his days are filled with grief, and his task is sorrowful; even at night, his mind does not rest. This too is futile.
24 ULB ለማንኛውም ሰው ከመብላት፥ መጠጣትና ከሥራው መልካም በሆነው ከመርካት የሚበልጥበት ምንም ነገር የለም። ይህ እውነት የሚመጣው ከእግዚአብሔር እጅ እንደሆነም አየሁ። BSB BSB: Nothing is better for a man than to eat and drink and enjoy his work. I have also seen that this is from the hand of God.
25 ULB ከእግዚአብሔር ካልሆነ በስተቀር ማን ሊበላ ይችላል? ወይም የትኛውንም ዓይነት ደስታ ማን ሊደሰት ይችላል? BSB BSB: For apart from Him, who can eat and who can find enjoyment?
26 ULB እርሱን ደስ ለሚያሰኝ እግዚአብሔር ጥበብን፥ እውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል። እንዲሁም ለኃጢአተኛው የመሰብሰብንና የማከማቸትን ሥራ ይሰጠዋል፥ እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኘው ሰው ይሰጠው ዘንድ። ይህም ደግሞ እንፋሎትን ማብዛትና ነፋስን ለማገድ መሞከር ነው። BSB BSB: To the man who is pleasing in His sight, He gives wisdom and knowledge and joy, but to the sinner He assigns the task of gathering and accumulating that which he will hand over to one who pleases God. This too is futile and a pursuit of the wind.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.