1 ULB እንደገና ከፀሐይ በታች ስለሚደረገው ግፍ ሁሉ አሰብሁ። የሚጨቆኑትን ሰዎች ዕንባ ተመልከቱ። የሚያጽናናቸውም የለም። በጨቋኞቻቸው እጅ ኃይል አለ፥ ነገር ግን የተጨቆኑት ሰዎች አጽናኝ የላቸውም። BSB BSB: Again I looked, and I considered all the oppression taking place under the sun. I saw the tears of the oppressed, and they had no comforter; the power lay in the hands of their oppressors, and there was no comforter.
2 ULB ስለዚህ ካሉት የሞቱት፥ እስካሁን በሕይወት ካሉት ቀደም ሲል የሞቱት ይሻላሉ አልሁ። BSB BSB: So I admired the dead, who had already died, above the living, who are still alive.
3 ULB ሆኖም ከሁለቱ የሚሻለው ያልኖረው፥ ከፀሐይ በታች የሚደረገውን ክፉ ድርጊት ያላየው ነው። BSB BSB: But better than both is he who has not yet existed, who has not seen the evil that is done under the sun.
4 ULB ከዚያም የትኛውም ጥረትና የጥበብ ሥራ ባልንጀራውን ለቅንዓት እንደሚያነሣሣው አየሁ። ይህም ደግሞ እንፋሎትና ንፋስን ለማገድ መሞከር ነው። BSB BSB: I saw that all labor and success spring from a man’s envy of his neighbor. This too is futile and a pursuit of the wind.
5 ULB ሞኝ ሰው እጁን አጣምሮ ይቀመጣል፥ አይሠራምም፥ ስለዚህ የራሱ ሥጋ ምግቡ ነው። BSB BSB: The fool folds his hands and consumes his own flesh.
6 ULB ንፋስን ለማገድ በመሞከር ከሚገኝ ሁለት እፍኝ ይልቅ በጥሞና የተሠራ አንድ እፍኝ ይሻላል። BSB BSB: Better one handful with tranquility than two handfuls with toil and pursuit of the wind.
7 ULB ከዚያም እንደገና ስለሚበልጠው ከንቱነት፥ ከፀሐይ በታች በይበልጥ ተንኖ ስለሚጠፋው እንፋሎት አሰብሁ። BSB BSB: Again, I saw futility under the sun.
8 ULB ብቻውን የሆነ አንድ ሰው አለ። ወንድ ልጅም ሆነ አባት አንድም የለውም። ለሚሠራው ሁሉ ማለቂያ የለውም፥ ዓይኖቹም ባገኘው ብልጽግና አይረኩም። እርሱም፥ "የምለፋው ለማን ነው? ራሴንስ ከደስታ የማርቀው ለምንድነው?" ብሎ ይደነቃል። ይህ የከፋ ሁኔታ ደግሞም እንፋሎት ነው። BSB BSB: There is a man all alone, without even a son or brother. And though there is no end to his labor, his eyes are still not content with his wealth: “For whom do I toil and bereave my soul of enjoyment?” This too is futile—a miserable task.
9 ULB ከአንድ ሰው ይልቅ ሁለቱ የተሻለ ሥራ ይሠራሉ፤ በጋራ ለሥራቸው የተሻለ ገቢ ማግኘት ይችላሉ። BSB BSB: Two are better than one, because they have a good return for their labor.
10 ULB አንደኛው ቢወድቅ ሌላኛው ጓደኛውን ሊያነሣው ይችላልና። በመሆኑም በወደቀ ጊዜ የሚያነሣው ካልኖረ ብቸኛውን ሰው ሀዘን ይከተለዋል። BSB BSB: For if one falls down, his companion can lift him up; but pity the one who falls without another to help him up!
11 ULB ሁለቱ አብረው ቢተኙ ሊሞቃቸው ይችላል፥ ብቻውን ቢሆን ግን እንዴት ሊሞቀው ይችላል? BSB BSB: Again, if two lie down together, they will keep warm; but how can one keep warm alone?
12 ULB አንድ ሰው ብቻውን ሊሸነፍ ይችላል፥ ሁለቱ ግን ጥቃቱን መመከት ይችላሉ። በሦስት የተገመደ ገመድ ቶሎ አይበጠስም። BSB BSB: And though one may be overpowered, two can resist. Moreover, a cord of three strands is not quickly broken.
13 ULB ማስጠንቀቂያዎችን እንዴት መስማት እንዳለበት ከማያውቅ ሞኝ ሽማግሌ ንጉሥ ይልቅ ድሃ፥ ነገር ግን ጥበበኛ የሆነ ወጣት ይሻላል። BSB BSB: Better is a poor but wise youth than an old but foolish king who no longer knows how to take a warning.
14 ULB ወጣቱ ከወህኒ ወጥቶ ቢነግሥ ወይም በሀገሩ በድህነት ተወልዶ ቢያድግም ይህ አውነት ነው። BSB BSB: For the youth has come from the prison to the kingship, though he was born poor in his own kingdom.
15 ULB ይሁንና ከፀሐይ በታች ሕያው የሆነና የሚንቀሳቀሰው ሁሉ ራሳቸውን ንጉሥ ሆኖ ለተነሣው ለሌላው ወጣት ሲያስገዙ አየሁ። BSB BSB: I saw that all who lived and walked under the sun followed this second one, the youth who succeeded the king.
16 ULB አዲሱን ንጉሥ መታዘዝ ለሚፈልገው ሕዝብ ሁሉ መጨረሻ የለውም፥ በኋላ ላይ ግን ብዙዎቹ አያመሰግኑትም። በርግጥ ይህ ሁኔታ እንፋሎት፥ ንፋስንም ለማገድ መሞከር ነው። BSB BSB: There is no limit to all the people who were before them. Yet the successor will not be celebrated by those who come even later. This too is futile and a pursuit of the wind.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.