1 ULB ከውድ ሽቶ መልካም ስም ይሻላል፥ ከልደት ቀንም የሞት ቀን ይሻላል። BSB BSB: A good name is better than fine perfume, and one’s day of death is better than his day of birth.
2 ULB ወደ ግብዣ ቤት ከመሄድ ወደ ሀዘን ቤት መሄድ ይሻላል፥ በሕይወቱ መጨረሻ ሰው ሁሉ ሀዘን ይገጥመዋልና፥ ስለዚህ ሕያዋን የሆኑ ሰዎች ይህንን ልብ ማለት አለባቸው። BSB BSB: It is better to enter a house of mourning than a house of feasting, since death is the end of every man, and the living should take this to heart.
3 ULB ከሣቅ ጥልቅ ሐዘን ይሻላል፥ ከፊት ሐዘን በኋላ የልብ ደስታ ይመጣልና። BSB BSB: Sorrow is better than laughter, for a sad countenance is good for the heart.
4 ULB የጠቢብ ልቡ ሐዘን ቤት ውስጥ ነው፥ የሞኞች ልብ ግን በግብዣ ቤት ውስጥ ነው። BSB BSB: The heart of the wise is in the house of mourning, but the heart of fools is in the house of pleasure.
5 ULB የሞኞችን መዝሙር ከመስማት የጠቢብን ተግሳጽ መስማት ይሻላል። BSB BSB: It is better to heed a wise man’s rebuke than to listen to the song of fools.
6 ULB ከድስጥ ሥር የሚነድ እሾህ እንደሚንጣጣ የሞኞች ሣቅ ደግሞ እንደዚሁ ነው። ይህም ደግሞ እንፋሎት ነው። BSB BSB: For like the crackling of thorns under the pot, so is the laughter of the fool. This too is futile.
7 ULB ቀማኛነት ጠቢቡን ሰው ያለጥርጥር ሞኝ ያደርገዋል፥ ጉቦም ልቡን ያበላሸዋል። BSB BSB: Surely extortion turns a wise man into a fool, and a bribe corrupts the heart.
8 ULB የአንድ ነገር መጨረሻ ከጅማሬው ይሻላል፤ በመንፈሳቸው ትዕግስተኞች የሆኑ ሰዎች በመንፈሳቸው ከሚታበዩት ይሻላሉ። BSB BSB: The end of a matter is better than the beginning, and a patient spirit is better than a proud one.
9 ULB በመንፈስህ ለመቆጣት አትቸኩል፥ ቁጣ በሞኞች ልብ ያድራልና። BSB BSB: Do not be quickly provoked in your spirit, for anger settles in the lap of a fool.
10 ULB "ከእነዚህ ይልቅ ያለፉት ዘመናት ለምን ተሻሉ?" አትበል፥ ይህንን የምትጠይቀው ጥበበኛ ስለሆንክ አይደለምና። BSB BSB: Do not say, “Why were the old days better than these?” For it is unwise of you to ask about this.
11 ULB ጥበብ ከአባቶቻችን የምንወርሳቸውን ጠቃሚ ነገሮች ያህል መልካም ነው። እርሱ ፀሐይን ለሚያዩ ለእነዚያ ትርፍ ያስገኝላቸዋል። BSB BSB: Wisdom, like an inheritance, is good, and it benefits those who see the sun.
12 ULB ገንዘብ ጥበቃ ሊሰጥ እንደሚችል ጥበብም ጥበቃን ይሰጣል፥ የዕውቀት ብልጫው ግን ጥበብ ላገኟት ሕይወት መስጠቷ ነው። BSB BSB: For wisdom, like money, is a shelter, and the advantage of knowledge is that wisdom preserves the life of its owner.
13 ULB የእግዚአብሔርን ሥራ ተመልከት፡ እርሱ ያጣመመውን የትኛውንም ነገር ማን ሊያቃናው ይችላል? BSB BSB: Consider the work of God: Who can straighten what He has bent?
14 ULB ጊዜው መልካም ሲሆን በደስታ ኑርበት፥ ቀኑ ሲከፋ ግን ይህን አስብ፡ ሁለቱም አጠገብ ለአጠገብ እንዲኖሩ እግዚአብሔር ፈቅዶላቸዋል። በዚህ ምክንያት ማንም ሰው ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን የትኛውንም ነገር አያውቅም። BSB BSB: In the day of prosperity, be joyful, but in the day of adversity, consider this: God has made one of these along with the other, so that a man cannot discover anything that will come after him.
15 ULB ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመኔ ብዙ ነገሮችን ተመልክቻለሁ። ጻድቃን ቢሆኑም የሚጠፉ ጻድቅ ሰዎች አሉ፥ ክፋትን ቢያደርጉም ረጅም ዘመን የሚኖሩ አመጸኞችም አሉ። BSB BSB: In my futile life I have seen both of these: A righteous man perishing in his righteousness, and a wicked man living long in his wickedness.
16 ULB ራስህን አታጽድቅ፥ በራስህም ግምት ጠቢብ አትሁን። ለምን ራስህን ታጠፋለህ? BSB BSB: Do not be overly righteous, and do not make yourself too wise. Why should you destroy yourself?
17 ULB እጅግ አመጸኛ ወይም ሞኝ አትሁን። ለምን ከቀንህ በፊት ትሞታለህ? BSB BSB: Do not be excessively wicked, and do not be a fool. Why should you die before your time?
18 ULB ይህንን ጥበብ ብትይዝ መልካም ነው፥ ጽድቅንም ከማድረግ እጅህን ባትመልስ። እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ኃላፊነቱን ሁሉ ይወጣልና። BSB BSB: It is good to grasp the one and not let the other slip from your hand. For he who fears God will follow both warnings.
19 ULB በአንድ ከተማ ውስጥ ካሉ አሥር አስተዳዳሪዎች ይልቅ በጥበበኛ ሰው ውስጥ ያለች ጥበብ ተጽዕኖዋ ትልቅ ነው። BSB BSB: Wisdom makes the wise man stronger than ten rulers in a city.
20 ULB መልካምን የሚያደርግና ፈጽሞ ኃጢአትን የማይሠራ አንድም ጻድቅ በምድር ላይ የለም። BSB BSB: Surely there is no righteous man on earth who does good and never sins.
21 ULB የሚነገረውን ቃል ሁሉ አታድምጥ፥ ምናልባት አገልጋይህ ሲረግምህ ትሰማው ይሆናልና። BSB BSB: Do not pay attention to every word that is spoken, or you may hear your servant cursing you.
22 ULB በተመሳሳይ፥ ሌሎችን በልብህ ብዙ ጊዜ እንደረገምካቸው አንተ ራስህ ታውቃለህ። BSB BSB: For you know in your heart that many times you yourself have cursed others.
23 ULB ይህንን ሁሉ በጥበብ አረጋገጥሁ። እኔም፥ "ጠቢብ እሆናለሁ" አልሁ፥ እርሱ ግን መሆን ከምችለው በላይ ነው። BSB BSB: All this I tested by wisdom, saying, “I resolve to be wise.” But it was beyond me.
24 ULB ጥበብ ሩቅና ጥልቅ ናት። ማን ሊያገኛት ይችላል? BSB BSB: What exists is out of reach and very deep. Who can fathom it?
25 ULB ለመማርና ለመፈተን፥ ጥበብንና የእውነታን ማብራሪያ ለመፈለግና ክፋት የማይረባ፥ ሞኝነትም ዕብደት መሆኑን ለመረዳት ልቤን መለስሁ። BSB BSB: I directed my mind to understand, to explore, to search out wisdom and explanations, and to understand the stupidity of wickedness and the folly of madness.
26 ULB ልቧ በወጥመድና በመረብ የተሞላ፥ እጆቿም የእግር ብረት የሆኑ የትኛዋም ሴት ከሞት ይልቅ መራራ ናት። እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ማንም ቢሆን ከእርሷ ያመልጣል፥ ኃጢአተኛው ግን በእርሷ ይወሰዳል። BSB BSB: And I find more bitter than death the woman who is a snare, whose heart is a net, and whose hands are chains. The man who pleases God escapes her, but the sinner is ensnared.
27 ULB "መርምሬ ያገኘሁትን ተመልከቱ" ይላል አስተማሪው። የእውነታን ፍቺ ለማግኘት በአንደኛው ምርምር ላይ ሌላውን እጨምር ነበር። BSB BSB: “Behold,” says the Teacher, “I have discovered this by adding one thing to another to find an explanation.
28 ULB እስካሁን የምፈልገው ይህንን ነው፥ ነገር ግን አላገኘሁትም። በሺህ ሰዎች መካከል አንድ ጻድቅ አገኘሁ፥ በእነዚያ ሁሉ መካከል ግን አንዲት ሴት አላገኘሁም። BSB BSB: While my soul was still searching but not finding, among a thousand I have found one upright man, but among all these I have not found one such woman.
29 ULB እግዚአብሔር ሰዎችን ቅን አድርጎ እንደ ፈጠራቸው፥ እነርሱ ግን ብዙ ችግሮችን እየፈለጉ ርቀው እንደ ሄዱ ይህንን ብቻ አገኘሁ። BSB BSB: Only this have I found: I have discovered that God made mankind upright, but they have sought out many schemes.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.