1 ULB ስለ ጻድቃንና ስለ ጥበበኛ ሰዎች፥ ስለ ሥራቸውም፥ ስለ እነዚህ ሁሉ ለመገንዘብ በልቤ አሰብሁ። ሁሉም በእግዚአብሔር እጅ ውስጥ ናቸው። አንድ ሰው ፍቅር ወይም ጥላቻ ይገጥመው እንደሆነ ማንም አያውቅም። BSB BSB: So I took all this to heart and concluded that the righteous and the wise, as well as their deeds, are in God’s hands. Man does not know what lies ahead, whether love or hate.
2 ULB ሁሉም ሰው ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ አለው። ጻድቃንን እና አመጸኞችን፥ መልካምና ክፉ ሰዎችን፥ ንጹሕ የሆኑትንና ያልሆኑትን፥ መሥዋዕት የሚያቀርበውንና የማያቀርበውን ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ይጠብቃቸዋል። መልካም ሰዎች እንደሚሞቱ ኃጢአተኞችም ደግሞ እንዲሁ ናቸው። የሚምለው ሰው እንደሚሞተው ሁሉ ለመማል የሚፈራው ሰውም ይሞታል። BSB BSB: It is the same for all: There is a common fate for the righteous and the wicked, for the good and the bad, for the clean and the unclean, for the one who sacrifices and the one who does not. As it is for the good, so it is for the sinner; as it is for the one who makes a vow, so it is for the one who refuses to take a vow.
3 ULB ከፀሐይ በታች ለተደረገው ሁሉ ክፉ ዕጣ ፈንታ አለው፥ ለሁሉም አንድ መጨረሻ። የሰዎች ልብ በክፋት የተሞላ ነው፥ በሕይወት እያሉም ዕብደት በልባቸው አለ። ከዚያ በኋላ ወደ ሙታን ይሄዳሉ። BSB BSB: This is an evil in everything that is done under the sun: There is one fate for everyone. Furthermore, the hearts of men are full of evil and madness while they are alive, and afterward they join the dead.
4 ULB ከሞተ አንበሳ በሕይወት ያለ ውሻ እንደሚሻል በሕይወት ላለ ሰውም አሁንም ተስፋ አለው። BSB BSB: There is hope, however, for anyone who is among the living; for even a live dog is better than a dead lion.
5 ULB ሕያዋን ሰዎች እንደሚሞቱ ያውቃሉ፥ ሙታን ግን ምንም አያውቁም። መታሰቢያቸው ተረስቷልና ምንም ብድራት አይኖራቸውም። BSB BSB: For the living know that they will die, but the dead know nothing. They have no further reward, because the memory of them is forgotten.
6 ULB ፍቅራቸው፥ ጥላቻቸውና ቅናታቸው ከብዙ ጊዜ በፊት ጠፍቷል። ከፀሐይ በታች በተደረገ በማንኛውም ነገር ዳግም ስፍራ አይኖራቸውም። BSB BSB: Their love, their hate, and their envy have already vanished, and they will never again have a share in all that is done under the sun.
7 ULB መንገድህን ሂድ፥ ምግብህን በደስታ ተመገብ፥ በደስተኛ ልብ ወይንህን ጠጣ፥ መልካሙን ሥራህን እግዚአብሔር ተቀብሎታልና። BSB BSB: Go, eat your bread with joy, and drink your wine with a cheerful heart, for God has already approved your works:
8 ULB ልብሶችህ ሁልጊዜ ነጭ ይሁኑ፥ ራስህንም በዘይት ተቀባ። BSB BSB: Let your garments always be white, and never spare the oil for your head.
9 ULB ከፀሐይ በታች እግዚአብሔር በሰጠህ በከንቱ ዘመንህ፥ ከንቱ በሆነው የሕይወት ዘመንህ ሁሉ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር በደስታ ኑር። ከፀሐይ በታች ለሆነው ሥራህ ይህ ብድራት ነው። እጅህ ለመሥራት የሚያገኘውን ሁሉ በሙሉ ኃይልህ ሥራ፥ BSB BSB: Enjoy life with your beloved wife all the days of the fleeting life that God has given you under the sun—all your fleeting days. For this is your portion in life and in your labor under the sun.
10 ULB በምትሄድበት በመቃብር ስፍራ ሥራ ወይም ገለጻ ወይም እውቀት ወይም ጥበብ በዚያ የለምና። BSB BSB: Whatever you find to do with your hands, do it with all your might, for in Sheol, where you are going, there is no work or planning or knowledge or wisdom.
11 ULB ከፀሐይ በታች አንዳንድ የሚያስደስቱ ነገሮችን አየሁ፡ ሩጫ ለፈጣኖች አይሆንም። ውጊያ ለብርቱ ሰዎች አይሆንም። እንጀራ ለጥበበኞች ሰዎች አይሆንም። ሀብት ለአስተዋይ ሰዎች አይሆንም። ሞገስ እውቀት ላላቸው ሰዎች አይሆንም። ከዚህ ይልቅ ጊዜና ዕድል በሁሉ ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል። BSB BSB: I saw something else under the sun: The race is not to the swift, nor the battle to the strong; neither is the bread to the wise, nor the wealth to the intelligent, nor the favor to the skillful. For time and chance happen to all.
12 ULB ዓሳ በሚሞትበት መረብ እንደሚጠመድ ወይም ወፎች በወጥመድ እንደሚያዙ ማንም ሰው የሚሞትበትን ጊዜ አያውቅም። የሰው ልጆችም ልክ እንደ እንስሳ ድንገት በሚወድቅባቸው ክፉ ጊዜ ይታሰራሉ። BSB BSB: For surely no man knows his time: Like fish caught in a cruel net or birds trapped in a snare, so men are ensnared in an evil time that suddenly falls upon them.
13 ULB ደግሞም ከፀሐይ በታች ያስገረመኝን ጥበብ አየሁ። BSB BSB: I have also seen this wisdom under the sun, and it was great to me:
14 ULB ጥቂት ሰዎች ብቻ የሚኖሩባት አንዲት ከተማ ነበረች፥ አንድ ታላቅ ንጉሥ መጣባት፥ ከበባት፥ በዙሪያዋም ታላቅ ምሽግ ገነባባት። BSB BSB: There was a small city with few men. A mighty king came against it, surrounded it, and built large siege ramps against it.
15 ULB በከተማው ውስጥ አንድ ድሃ ጠቢብ ሰው ተገኘ፥ በጥበቡም ከተማይቱን አዳነ። በኋላ ላይ ያንን ድሃ ሰው ማንም አላሰበውም። BSB BSB: Now a poor wise man was found in the city, and he saved the city by his wisdom. Yet no one remembered that poor man.
16 ULB እኔም፥ "ጥበብ ከኃይል ይሻላል፥ ነገር ግን የድሃው ጥበብ ተንቋል፥ ቃሎቹም አልተሰሙም" ብዬ ደመደምኩ። BSB BSB: And I said, “Wisdom is better than strength, but the wisdom of the poor man is despised, and his words are not heeded.”
17 ULB በሞኞች መካከል ከሚጮህ ማንኛውም ገዥ ይልቅ በዝግታ የሚነገሩ የጥበበኞች ሰዎች ቃል ይደመጣል። BSB BSB: The calm words of the wise are heeded over the shouts of a ruler among fools.
18 ULB ከጦር መሣሪያዎች ጥበብ ትሻላለች፥ ነገር ግን አንድ ኃጢአተኛ ብዙ መልካም ነገሮችን ሊያበላሽ ይችላል። BSB BSB: Wisdom is better than weapons of war, but one sinner destroys much good.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.