1 ULB ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ BSB BSB: Then the LORD said to Moses,
2 ULB “በዐዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ወር የመጀመሪያ ቀን ማደረያውን፣ የመገናኛውን ድንኳን ትከለው። BSB BSB: “On the first day of the first month you are to set up the tabernacle, the Tent of Meeting.
3 ULB ታቦት በውስጡ አስቀምጠው፤ ታቦቱንም በመጋረጃ ከልለው። BSB BSB: Put the ark of the Testimony in it and screen off the ark with the veil.
4 ULB ጠረጴዛውንም ወደ ውስጥ አምጣና በላዩ የሚቀመጡትን ዕቃዎች በሥርዐት አስቀምጥ። ከዚያም መቅረዙን አስገብተህ መብራቶቹን አስተካክል። BSB BSB: Then bring in the table and set out its arrangement; bring in the lampstand as well, and set up its lamps.
5 ULB የወርቅ የዕጣን መሠዊያውን በምስክሩ ታቦት ፊት አስቀምጥ፤ የመገናኛውን ድንኳን መግቢያ መጋረጃም አድርግ። BSB BSB: Place the gold altar of incense in front of the ark of the Testimony, and hang the curtain at the entrance to the tabernacle.
6 ULB የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያ በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት አስቀምጥ። BSB BSB: Place the altar of burnt offering in front of the entrance to the tabernacle, the Tent of Meeting.
7 ULB ትልቁን የመታጠቢያ ሳሕን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠው፤ ውሀም አድርግበት። BSB BSB: And place the basin between the Tent of Meeting and the altar, and put water in it.
8 ULB በዙሪያውም አደባባይ ሥራለትን በአደባባዩ መግቢያ ላይ መጋረጃውን ስቀል። BSB BSB: Set up the surrounding courtyard and hang the curtain for the entrance to the courtyard.
9 ULB መቅቢያ ዘይቱን ውሰድና መገናኛውን ድንኳንና አውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ቅባ። እርሱንና በውስጡ ያለውን ዕቃ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከዚያም የተቀደሰ ይሆናል። BSB BSB: Take the anointing oil and anoint the tabernacle and everything in it; consecrate it along with all its furnishings, and it shall be holy.
10 ULB የሚቃጠሉ መሥዋዕቶችን መሠዊያና የመሠዊያውን ዕቃዎች ሁሉ ቅባቸው። BSB BSB: Anoint the altar of burnt offering and all its utensils; consecrate the altar, and it shall be most holy.
11 ULB መሠዊያውን ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከዚያም ለእኔ እጅግ የተቀደሰ ይሆንልኛል። BSB BSB: Anoint the basin and its stand and consecrate them.
12 ULB ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ አምጣና በውሀ እጠባቸው። BSB BSB: Then bring Aaron and his sons to the entrance to the Tent of Meeting and wash them with water.
13 ULB ለእኔ የተቀደሱ ልብሶችን ለአሮን አልብሰው፤ ካህኔ ሆኖ እንዲያገለግልም ቅባው፤ ቀድሰውም። BSB BSB: And you are to clothe Aaron with the holy garments, anoint him, and consecrate him, so that he may serve Me as a priest.
14 ULB ልጆቹንም አምጣና ሸሚዞችን አልብሳቸው። BSB BSB: Bring his sons forward and clothe them with tunics.
15 ULB ካህናቴ ሆነው እንዲያገለግሉኝ፣ አባታቸውን እንደ ቀባኸው እነርሱንም ቅጣቸው። የእነርሱ መቀባት በትውልዶች ሁሉ የዘለቄታ ካህንነትን ለእነርሱ ያስገኛል።” BSB BSB: Anoint them just as you anointed their father, so that they may also serve Me as priests. Their anointing will qualify them for a permanent priesthood throughout their generations.”
16 ULB ሙሴ ያደረገው ይህ ነው፦ እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ተከተለ። እነዚህንም ሁሉ አደረገ። BSB BSB: Moses did everything just as the LORD had commanded him.
17 ULB በሁለተኛው ዓመት የመጀመሪያ ወር አንደኛ ቀን ላይ የመገናኛው ድንኳን ተተከለ። BSB BSB: So the tabernacle was set up on the first day of the first month of the second year.
18 ULB ሙሴ መገናኛውን ድንኳን ተከለ፤ መቆሚያዎቹንም በስፍራቸው አስቀመጠ፤ ወጋግራዎቹን አቁሞ አግዳሚዎቹን አያያዘ፤ ምሰሶዎቹንም አቆመ። BSB BSB: When Moses set up the tabernacle, he laid its bases, positioned its frames, inserted its crossbars, and set up its posts.
19 ULB በማደሪያው ላይ መሸፈኛውን ዘረጋ፤ ድንኳኑንም እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው ከበላዩ አስቀመጠው። BSB BSB: Then he spread the tent over the tabernacle and put the covering over the tent, just as the LORD had commanded him.
20 ULB ምስክሩን ወስዶ በታቦቱ ውስጥ አስቀመጠው። BSB BSB: Moses took the Testimony and placed it in the ark, attaching the poles to the ark; and he set the mercy seat atop the ark.
21 ULB ወደ መገናኛው ድንኳን አመጣው። እግዚአብሔር ሙሴን አዝዞት እንደ ነበረው፣ የምስክሩን ታቦት ለመከለል መጋረጃውን አደረገ። BSB BSB: Then he brought the ark into the tabernacle, put up the veil for the screen, and shielded off the ark of the Testimony, just as the LORD had commanded him.
22 ULB ሰሜን ጎን ከመጋረጃው ውጭ ጠረጴዛውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ አስቀመጠ። BSB BSB: Moses placed the table in the Tent of Meeting on the north side of the tabernacle, outside the veil.
23 ULB እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው፣ ኅብስቱን በጠረጴዛው ላይ በሥርዐት በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጠው። BSB BSB: He arranged the bread on it before the LORD, just as the LORD had commanded him.
24 ULB መቅረዙን በመገናኛው ድንኳን ደቡብ ጎን ከጠረጴዛው ትይዩ በማደሪያው ድንኳን ውስጥ አስቀመጠው። BSB BSB: He also placed the lampstand in the Tent of Meeting opposite the table on the south side of the tabernacle
25 ULB መብራቶቹን እግዚአብሔር እንዳዘዘው በእግዚአብሔር ፊት አበራቸው። BSB BSB: and set up the lamps before the LORD, just as the LORD had commanded him.
26 ULB የተሠራውን የዕጣን መሠዊያም በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከመጋረጃው ፊት ለፊት አደረገው። BSB BSB: Moses placed the gold altar in the Tent of Meeting, in front of the veil,
27 ULB ላይም እግዚአብሔር አዝዞት እንደ ነበረው ጣፋጭ መዐዛ ያለውን ዕጣን አቀጣጠለ። BSB BSB: and he burned fragrant incense on it, just as the LORD had commanded him.
28 ULB መጋረጃውን በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሰቀለ። BSB BSB: Then he put up the curtain at the entrance to the tabernacle.
29 ULB የሚቃጠለውን መሥዋዕት መሠዊያም በማደሪያው፣ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ አስቀመጠ። በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን እግዚአብሔር እንዳዘዘው አቀረበ። BSB BSB: He placed the altar of burnt offering near the entrance to the tabernacle, the Tent of Meeting, and offered on it the burnt offering and the grain offering, just as the LORD had commanded him.
30 ULB የመታጠቢያ ሳሕኑን በመገናኛው ድንኳንና በመሠውያው መካከል አኖረው፤ የመታጠቢያ ውሀም በውስጡ አደረገ። BSB BSB: He placed the basin between the Tent of Meeting and the altar and put water in it for washing;
31 ULB ሙሴ፣ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በመታጠቢያው ውሀ ይታጠቡ ነበር፤ BSB BSB: and from it Moses, Aaron, and his sons washed their hands and feet.
32 ULB መገናኛው ድንኳን ውስጥ በሚገቡትና መሠዊያው ወዳለበት ወደ ላይ በሚወጡበት ጊዜ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ታጥበውታል። BSB BSB: They washed whenever they entered the Tent of Meeting or approached the altar, just as the LORD had commanded Moses.
33 ULB ሙሴ በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው ዙሪያ አደባባዩን አቆመ። መጋረጃውንም በአደባባዩ መግቢያ ዘረጋ። ሙሴ በዚህ መንገድ ሥራውን ፈጸመ። BSB BSB: And Moses set up the courtyard around the tabernacle and the altar, and he hung the curtain for the entrance to the courtyard. So Moses finished the work.
34 ULB ደመናውም የመገናኛውን ድንኳን ሸፈነ፤ የእግዚአብሔር ክብርም ማደሪያውን ሞላው። BSB BSB: Then the cloud covered the Tent of Meeting, and the glory of the LORD filled the tabernacle.
35 ULB ደመናው በላዩ ስላረፈና የእግዚአብሔር ክብርም ማደሪያውን ስለ ሞላው፣ ሙሴ መገናኛው ድንኳን ውስጥ መግባት አልቻለም ነበር። BSB BSB: Moses was unable to enter the Tent of Meeting because the cloud had settled on it, and the glory of the LORD filled the tabernacle.
36 ULB ከማደሪያው ድንኳን በተነሣ ጊዜ ሁሉ፣ የእስራኤል ሰዎች ይጓዛሉ። BSB BSB: Whenever the cloud was lifted from above the tabernacle, the Israelites would set out through all the stages of their journey.
37 ULB ግን ደመናው ከማደሪያው ላይ ካልተነሣ፣ ሕዝቡ አይጓዙም። ደመናው እስከሚነሣበት ቀን ድረስ ይቆያሉ። BSB BSB: If the cloud was not lifted, they would not set out until the day it was taken up.
38 ULB በሁሉም የእስራኤል ሕዝብ ፊት በጕዟቸው ሁሉ ቀን የእግዚአብሔር ደመና፣ ማታ ደግሞ እሳቱ በማደሪያው ላይ ነበረ። BSB BSB: For the cloud of the LORD was over the tabernacle by day, and fire was in the cloud by night, in the sight of all the house of Israel through all their journeys.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.