1 ULB አንዳንድ የይሁዳና የብንያም ጠላቶች ከምርኮ የተመለሱት ሰዎች ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በመሥራት ላይ መሆናቸውን ሰሙ። BSB BSB: When the enemies of Judah and Benjamin heard that the exiles were building a temple for the LORD, the God of Israel,
2 ULB እነርሱም ወደ ዘሩባቤልና ወደ አባቶቻቸው የነገድ አለቆች መጡ። እነርሱም፥ "እንደናንተው አምላካችሁን እንፈልገዋለንና የአሶር ንጉሥ አስራዶን ወደዚህ ስፍራ ካመጣን ጊዜ ጀምሮም ስንሠዋለት ነበርና አብረናችሁ እንሥራ"አሏቸው። BSB BSB: they approached Zerubbabel and the heads of the families, saying, “Let us build with you because, like you, we seek your God and have been sacrificing to Him since the time of King Esar-haddon of Assyria, who brought us here.”
3 ULB ዘሩባቤል፥ ኢያሱና የአባቶቻቸው የነገድ አለቆች ግን፥ "የአምላካችንን ቤት መሥራት የሚገባን እኛ እንጂ እናንተ አይደላችሁም፥ የፋርስ ንጉሥ እንዳዘዘው ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር የምንሠራው እኛ ነን" አሏቸው። BSB BSB: But Zerubbabel, Jeshua, and the other heads of the families of Israel replied, “You have no part with us in building a house for our God, since we alone must build it for the LORD, the God of Israel, as Cyrus king of Persia has commanded us.”
4 ULB ስለዚህ የምድሩ ሕዝብ የይሁዳን ሰዎች እጅ አደከሙ፤ እንዳይሠሩም የይሁዳን ሰዎች አስፈራሩ። BSB BSB: Then the people of the land set out to discourage the people of Judah and make them afraid to build.
5 ULB ደግሞም ዕቅዳቸውን ለማጨናገፍ ለአማካሪዎች ጉቦ ሰጡ። ይህንንም በቂሮስ ዘመን ሁሉና እስከ ፋርስ ንጉሥ ዳርዮስ እስከ ነገሠበት ጊዜ ድረስ አደረጉ። BSB BSB: They hired counselors against them to frustrate their plans throughout the reign of Cyrus king of Persia and down to the reign of Darius king of Persia.
6 ULB ከዚያም አርጤክስስ መንገሥ በጀመረበት ዘመን በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ነዋሪዎች ላይ ክስ ጻፉባቸው። BSB BSB: At the beginning of the reign of Xerxes, an accusation was lodged against the people of Judah and Jerusalem.
7 ULB በአርጤክስስ ዘመን ቢሽላም፥ ሚትሪዳጡ፥ ጣብኤልና ተባባሪዎቻቸው ነበር ለአርጤክስስ የጻፉት። ደብዳቤውም በአረማይስጥ ቋንቋ ተጽፎ የተተረጎመ ነበር። BSB BSB: And in the days of Artaxerxes king of Persia, Bishlam, Mithredath, Tabeel, and the rest of his associates wrote a letter to Artaxerxes. It was written in Aramaic and then translated.
8 ULB አዛዡ ሬሁምና ጸሐፊው ሲምሳይ ስለ ኢየሩሳሌም ለአርጤክስስ እንዲህ ብለው ጻፉ፤ BSB BSB: Rehum the commander and Shimshai the scribe wrote the letter against Jerusalem to King Artaxerxes as follows:
9 ULB ከዚያም ዳኞች የነበሩት ሬሁም፥ ሲምሳይና ተባባሪዎቻቸው እንዲሁም በአርክ፥ በባቢሎንና በኤላሙ ሱሳ የነበሩ ሌሎች የመንግሥት ኃላፊዎች ደብዳቤውን ጻፉ- BSB BSB: From Rehum the commander, Shimshai the scribe, and the rest of their associates—the judges and officials over Tripolis, Persia, Erech and Babylon, the Elamites of Susa,
10 ULB እነርሱንም ታላቁና ኃያሉ አሹርባኒጳል በወንዙ ማዶ ባለው አውራጃ ከቀሩት ከሌሎቹ ጋር በሰማርያ እንዲሰፍሩ ያስገደዷቸው ሰዎች ደገፏቸው። BSB BSB: and the rest of the peoples whom the great and honorable Ashurbanipal deported and settled in the cities of Samaria and elsewhere west of the Euphrates.
11 ULB ለአርጤክስስ የላኩት የደብዳቤው ግልባጭ ይህ ነው፤ "ይህንን የሚጽፉት ከወንዙ ማዶ ያሉት ሰዎች፥ አገልጋዮችህ ናቸው፤ BSB BSB: (This is the text of the letter they sent to him.) To King Artaxerxes, From your servants, the men west of the Euphrates:
12 ULB ካንተ ዘንድ የወጡት አይሁድ እኛን በመቃወም አመጸኛይቱን ከተማ በኢየሩሳሌም ውስጥ ለመሥራት መጀመራቸውን ንጉሡ ይወቅ። እነርሱም ቅጥሮቹን ጨርሰው መሠረቶቹን አድሰዋል። BSB BSB: Let it be known to the king that the Jews who came from you to us have returned to Jerusalem and are rebuilding that rebellious and wicked city. They are restoring its walls and repairing its foundations.
13 ULB ይህቺ ከተማ ከተሠራችና ቅጥሯም ከተጠናቀቀ ምንም ዓይነት እጅ መንሻና ቀረጥ እንደማይሰጡና ንጉሡን እንደሚጎዱት ንጉሡ ይወቅ። BSB BSB: Let it now be known to the king that if that city is rebuilt and its walls are restored, they will not pay tribute, duty, or toll, and the royal treasury will suffer.
14 ULB በርግጥ የቤተመንግሥቱን ጨው ስለ በላን በንጉሡ ላይ ማናቸውም ዓይነት ውርደት ሲደርስበት ማየት አይገባንም። BSB BSB: Now because we are in the service of the palace and it is not fitting for us to allow the king to be dishonored, we have sent to inform the king
15 ULB ለዚህም ነው የአባትህን መዛግብት እንድትመረምርና ነገሥታትንና አውራጃዎችን የምትጎዳ አመጸኛ ከተማ መሆኗን እንድታረጋግጥ ለንጉሡ ያስታወቅነው። በነገሥታትና በአውራጃዎች ላይ ብዙ ችግር የፈጠረች ነች። ከብዙ ዘመን ጀምሮም የአመጽ ማዕከል ነች። ከተማይቱ ተደምስሳ የነበረችውም በዚሁ ምክንያት ነበር። BSB BSB: that a search should be made of the record books of your fathers. In these books you will discover and verify that the city is a rebellious city, harmful to kings and provinces, inciting sedition from ancient times. That is why this city was destroyed.
16 ULB ይህቺ ከተማ ከቅጥሯ ጋር ከተሠራች ከዚህ በኋላ ከታላቁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ ምንም የሚቀርልህ ነገር እንደማይኖር ለንጉሡ እናስታውቃለን"። BSB BSB: We advise the king that if this city is rebuilt and its walls are restored, you will have no dominion west of the Euphrates.
17 ULB ስለዚህ ንጉሡ ለሬሁም፥ ሲምሳይ፥ በሰማሪያ ላሉ ተባባሪዎቻቸውና ከወንዙ ማዶ ላሉት ለቀሩት ምላሽ ላከ፤ "ሰላም ይሁንላችሁ። BSB BSB: Then the king sent this reply: To Rehum the commander, Shimshai the scribe, and the rest of your associates living in Samaria and elsewhere in the region west of the Euphrates: Greetings.
18 ULB የላካችሁልኝ ደብዳቤ ተተርጉሞ ተነቦልኛል። BSB BSB: The letter you sent us has been translated and read in my presence.
19 ULB በመሆኑም ምርመራ እንዲደረግ አዘዝኩኝና ባለፉት ዘመናት በነገሥታት ላይ ስታምጽ የኖረች አመጸኛ መሆኗ ታውቋል። BSB BSB: I issued a decree, and a search was conducted. It was discovered that this city has revolted against kings from ancient times, engaging in rebellion and sedition.
20 ULB በኢየሩሳሌም ላይ ኃያላን ነገሥታት ገዝተዋል፥ ከወንዙ ማዶ ባለው ሁሉ ላይም ሥልጣን ነበራቸው። እጅ መንሻና ቀረጥም ይሰጣቸው ነበር። BSB BSB: And mighty kings have ruled over Jerusalem and exercised authority over the whole region west of the Euphrates; and tribute, duty, and toll were paid to them.
21 ULB አሁንም እነዚህ ሰዎች ሥራውን እንዲያቆሙና እኔ እስከማዝዝ ድረስ ይህቺን ከተማ እንዳይሠሩ ትዕዛዝ ስጡ። BSB BSB: Now, therefore, issue an order for these men to stop, so that this city will not be rebuilt until I so order.
22 ULB ይህንን ማድረጉን ቸል እንዳትሉ ተጠንቀቁ። ነገሥታቱን የሚጎዳው ጥፋት ለምን ይጨምራል?" BSB BSB: See that you do not neglect this matter. Why allow this threat to increase and the royal interests to suffer?
23 ULB የንጉሡ የአርጤክስስ ትዕዛዝ በሬሁም፥ በሲምሳይና በተባባሪዎቻቸው ፊት በተነበበ ጊዜ በፍጥነት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱና አይሁድ ሥራውን እንዲያቆሙ አስገደዷቸው። BSB BSB: When the text of the letter from King Artaxerxes was read to Rehum, Shimshai the scribe, and their associates, they went immediately to the Jews in Jerusalem and forcibly stopped them.
24 ULB ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለው የእግዚአብሔር ቤት ሥራ የፋርስ ንጉሥ ዳርዮስ እስከ ነገሠበት እስከ ሁለተኛው ዓመት ድረስ ተቋረጠ። BSB BSB: Thus the construction of the house of God in Jerusalem ceased, and it remained at a standstill until the second year of the reign of Darius king of Persia.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.