1 ULB እስራኤል ሆይ፥ አንተ የታመንክ አይደለህምና፥ አምላክህንም ትተሃልና፤ ሌሎች ሕዝቦች ደስ እንደሚላቸው፥ ደስ አይበልህ። በአውድዎች ሁሉ ላይ ሴተኛ አዳሪ የምትጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል ወድደሃል። BSB BSB: Do not rejoice, O Israel, with exultation like the nations, for you have played the harlot against your God; you have made love for hire on every threshing floor.
2 ULB ነገር ግን አውድማውና የወይን መጭመቂያው አይመግባቸውም፥ አዲሱ የወይን ጠጅም ይጥላታል። BSB BSB: The threshing floor and winepress will not feed them, and the new wine will fail them.
3 ULB በእግዚአብሔር ምድር ላይ አይኖሩም፤ ኤፍሬም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ ደግሞም አንድ ቀን በአሦር የረከሰ ምግብ ይበላሉ። BSB BSB: They will not remain in the land of the LORD; Ephraim will return to Egypt and eat unclean food in Assyria.
4 ULB ለእግዚአብሔር የወይን ጠጅ ቁርባን አያፈሱም፤ ደስም አያሰኙትም። መስዋዕታቸው እንደ ሐዘንተኞች ምግብ ይሆንባቸዋል፦ የሚበሉት ሁሉ ይረክሳሉ። ምግባቸው ለእነርሱ ብቻ የሚሆን ነውና ወደ እግዚአብሔር ቤት ሊመጣ አይችልም። BSB BSB: They will not pour out wine offerings to the LORD, and their sacrifices will not please Him, but will be to them like the bread of mourners; all who eat will be defiled. For their bread will be for themselves; it will not enter the house of the LORD.
5 ULB በእግዚአብሔር በዓል ቀን፥ በዓመት በዓል ቀን ምን ታድርጋላችሁ? BSB BSB: What will you do on the appointed day, on the day of the LORD’s feast?
6 ULB ተመልከቱ፥ ከጥፋት ቢያመልጡ እንኳን ግብጽ ትሰበስባቸዋለች፥ ሜፎስም ትቀብራቸዋለች። የብር ክምችታቸውን ሳማ ይውጠዋል፥ድንኳኖቻቸውንም እሾህ ይሞላዋል። BSB BSB: For even if they flee destruction, Egypt will gather them and Memphis will bury them. Their precious silver will be taken over by thistles, and thorns will overrun their tents.
7 ULB የቅጣት ቀን እየመጣ ነው፥የበቀል ቀን እየመጣ ነው። እስራኤል ሁሉ ይህን ይወቅ። ከክፋትህና ከጠላትነትህ የተነሳ፤ ነቢዩ ሞኝ፥ በመንፈስ የሚነዳውም ሰው እብድ ሆኖእል። BSB BSB: The days of punishment have come; the days of retribution have arrived—let Israel know it. The prophet is called a fool, and the inspired man insane, because of the greatness of your iniquity and hostility.
8 ULB ከአምላኬ ጋር የሆነው ነቢይ የኤፍሬም ጠባቂ ነው፤ ነገር ግን የወፍ ወጥመድ በመንገዱ ሁሉ ነው፥በአምላኩም ቤት ጠላትነት አለበት። BSB BSB: The prophet is Ephraim’s watchman, along with my God, yet the snare of the fowler lies on all his paths. Hostility is in the house of his God!
9 ULB በጊብዓ ዘመን እንደነበረው ራሳቸውን እጅግ አርክሰዋል። እግዚአብሔር ክፋታቸውን ያስባል፥ ኃጢአታቸውንም ይቀጣል። BSB BSB: They have deeply corrupted themselves as in the days of Gibeah; He will remember their guilt; He will punish their sins.
11 ULB የኤፍሬም ክብር እንደ ወፍ በሮ ይሄዳል።መውለድ፥ ማርገዝና መፀነስ የለም። BSB BSB: Ephraim’s glory will fly away like a bird, with no birth, no pregnancy, and no conception.
12 ULB ልጆችን ቢያሳድጉ እንኳን፥ አንዳቸውም እሰከማይቀሩላቸው ድረስ እወስድባቸዋለሁ። ከእነርሱ ዘወር ባልሁ ጊዜ፥ ወዮ ለእነርሱ! BSB BSB: Even if they raise their children, I will bereave them of each one. Yes, woe be to them when I turn away from them!
13 ULB ኤፍሬም እንደ ጢሮስ በለምለም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፥ ነገር ግን ኤፍሬም ልጆቹን ለሚያርዳቸው አሳልፎ ይሰጣል። BSB BSB: I have seen Ephraim, like Tyre, planted in a meadow. But Ephraim will bring out his children for slaughter.
14 ULB እግዚአብሔር ሆይ ስጣቸው፤ ምን ትሰጣቸዋለህ? የሚጨነግፍ ማኅፀንና ወተት የማይሰጡ ጡቶች ስጣቸው። BSB BSB: Give them, O LORD—what will You give? Give them wombs that miscarry and breasts that dry up!
15 ULB በጌልጌላ ካደረጉት ክፋታቸው ሁሉ የተነሳ፥ በዚያ እነርሱን መጥላት ጀመርኩ። ከክፉ ሥራቸው የተነሣ፥ ከቤቴ አስወጣቸዋለሁ። ከእንግዲህ ወዲያ አልወዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዓመጸኞች ናቸው። BSB BSB: All their evil appears at Gilgal, for there I hated them. I will drive them from My house for the wickedness of their deeds. I will no longer love them; all their leaders are rebellious.
16 ULB ኤፍሬም በበሽታ ተመታ፤ሥራቸውም ደረቀ፥ ፍሬም አይሰጡም። ልጆች ቢወልዱም እንኳን፥ የተወደዱ ልጆቻቸውን እገድላለሁ።» BSB BSB: Ephraim is struck down; their root is withered; they cannot bear fruit. Even if they bear children, I will slay the darlings of their wombs.
17 ULB አልታዘዙትምና አምላኬ ይጥላቸዋል። በሕዝቦች መካከል ተንከራታች ይሆናሉ። BSB BSB: My God will reject them because they have not obeyed Him; and they shall be wanderers among the nations.