3 ULB ሕግ ከጽዮን የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፣ "ኑ፣ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፥ በጎዳናውም እንሄዳለን ይላሉ።" BSB BSB: And many peoples will come and say: “Come, let us go up to the mountain of the LORD, to the house of the God of Jacob. He will teach us His ways so that we may walk in His paths.” For the law will go forth from Zion, and the word of the LORD from Jerusalem.
4 ULB በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፣ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፣ ጦርነትንም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም። BSB BSB: Then He will judge between the nations and arbitrate for many peoples. They will beat their swords into plowshares and their spears into pruning hooks. Nation will no longer take up the sword against nation, nor train anymore for war.
5 ULB እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፣ ኑ፣ በእግዚአብሔር ብርሃን እንሂድ። BSB BSB: Come, O house of Jacob, let us walk in the light of the LORD.
6 ULB የምሥራቅን ሰዎች አመል ስለ ተሞሉ፣ እንደ ፍልስጥኤማውያንም ምዋርተኞች ስለ ሆኑ፣ ከባዕድ ልጆችም ጋር ስለ ተባበሩ፣ የሕዝብህን የያዕቆብን ቤት ትተሃል። BSB BSB: For You have abandoned Your people, the house of Jacob, because they are filled with influences from the east; they are soothsayers like the Philistines; they strike hands with the children of foreigners.
7 ULB ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፣ ለመዛግብቶቻቸውም ፍጻሜ የለውም፤ ምድራቸውም ደግሞ በፈረሶች ተሞልታለች፣ ለሠረገሎቻቸውም ፍጻሜ የለውም። BSB BSB: Their land is full of silver and gold, with no limit to their treasures; their land is full of horses, with no limit to their chariots.
8 ULB ምድራቸው ደግሞ በጣዖታት ተሞልታለች፤ ጣቶቻቸውም ላደረጉት ለእጃቸው ሥራ ይሰግዳሉ። BSB BSB: Their land is full of idols; they bow down to the work of their hands, to what their fingers have made.
9 ULB ታናሹም ሰው ዝቅ ብሎአል፣ ግለሰቦችም ይዋረዳሉ፤ ስለዚህ አትቀበላቸው። BSB BSB: So mankind is brought low, and man is humbled—do not forgive them!
10 ULB ከእግዚአብሔር ማሸበርና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻ ግቡ፣ በመሬትም ውስጥ ተሸሸጉ። BSB BSB: Go into the rocks and hide in the dust from the terror of the LORD and the splendor of His majesty.
11 ULB ከፍ ያለችውም የሰው ዓይን ትዋረዳለች፣ የሰዎችም ኵራት ተጎትታ ትወድቃለች፣ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻውን ከፍ ይላል። BSB BSB: The proud look of man will be humbled, and the loftiness of men brought low; the LORD alone will be exalted in that day.
12 ULB የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ፣ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፣ እርሱም ይዋረዳል፤ BSB BSB: For the Day of the LORD of Hosts will come against all the proud and lofty, against all that is exalted—it will be humbled—
13 ULB ደግሞም በረጅሙ ከፍ ባለው በሊባኖስ ዝግባ ሁሉ ላይ፣ በባሳንም ዛፍ ሁሉ ላይ ይሆናል፣ BSB BSB: against all the cedars of Lebanon, lofty and lifted up, against all the oaks of Bashan,
14 ULB በረጅሞቹም ተራራዎች ሁሉ ላይ፣ ከፍ ባለውም ኮረብቶች ሁሉ ላይ፣ BSB BSB: against all the tall mountains, against all the high hills,
15 ULB በረጅሙም ግንብ ሁሉ ላይ፣ በተመሸገውም ቅጥር ሁሉ ላይ፣ BSB BSB: against every high tower, against every fortified wall,
16 ULB በተርሴስም መርከቦች ሁሉ ላይ፣ በሚያማምሩ ጣዖታትም ሁሉ ላይ ይሆናል። BSB BSB: against every ship of Tarshish, and against every stately vessel.
17 ULB የሰው ሁሉ ክብር ይዋረዳል፣ የሰውም ኵራት ይወድቃል፤ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል። BSB BSB: So the pride of man will be brought low, and the loftiness of men will be humbled; the LORD alone will be exalted in that day,
18 ULB ጣዖቶቻቸውም ሁሉ ፈጽመው ይጠፋሉ። BSB BSB: and the idols will vanish completely.
19 ULB እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ፣ ሰዎችን ከማስደንገጡና ከግርማው ክብሩ የተነሣ፣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ምድር ንቃቃት ውስጥ ይገባሉ። BSB BSB: Men will flee to caves in the rocks and holes in the ground, away from the terror of the LORD and from the splendor of His majesty, when He rises to shake the earth.
20 ULB በዚያን ቀን ሰው ይሰግድላቸው ዘንድ ያበጁአቸውን የብሩንና የወርቁን ጣዖቶቻቸውን ለፍልፈልና ለሌሊት ወፍ ይጥላሉ። BSB BSB: In that day men will cast away to the moles and bats their idols of silver and gold—the idols they made to worship.
21 ULB እግዚአብሔርም ምድርን ያናውጥ ዘንድ በተነሣ ጊዜ ከማስደንገጡና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ ዋሻና ወደ ተሰነጠቁ ዓለቶች ውስጥ ይገባሉ። BSB BSB: They will flee to caverns in the rocks and crevices in the cliffs, away from the terror of the LORD and from the splendor of His majesty, when He rises to shake the earth.
22 ULB እስትንፋሱ በአፍንጫው ውስጥ ያለበትን ሰው ተዉት፣ እርሱ ስለ ምን ይቈጠራል? BSB BSB: Put no more trust in man, who has only the breath in his nostrils. Of what account is he?
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.