1 ULB ተመልከቱ፣ እግዚአብሔር ምድርን ባዶ ያደርጋታል፣ ባድማም ያደርጋታል፣ ይገለብጣትማል፣ በእርስዋም የሚኖሩትን ይበትናል። BSB BSB: Behold, the LORD lays waste the earth and leaves it in ruins. He will twist its surface and scatter its inhabitants—
2 ULB እንደ ሕዝቡም እንዲሁ ካህኑ፣ እንደ ባሪያውም እንዲሁ ጌታው፣ እንደ ባሪያይቱም እንዲሁ እመቤትዋ፣ እንደሚገዛም እንዲሁ የሚሸጠው፣ እንደ አበዳሪውም እንዲሁ ተበዳሪው፣ እንደ ዕዳ አስከፋዩም እንዲሁ ዕዳ ከፋዩ ይሆናል። BSB BSB: people and priest alike, servant and master, maid and mistress, buyer and seller, lender and borrower, creditor and debtor.
3 ULB ምድር ፈጽሞ ትጠፋለች፣ ፈጽማም ትበላሻላች፤ እግዚአብሔር ይህን ቃል ተናግሮአልና። BSB BSB: The earth will be utterly laid waste and thoroughly plundered. For the LORD has spoken this word.
4 ULB ምድር ደረቀች ረገፈችም፤ ዓለም ተናወጠች ረገፈችም፤ የምድርም ስመ-ጥር ሕዝብ ደከሙ። BSB BSB: The earth mourns and withers; the world languishes and fades; the exalted of the earth waste away.
5 ULB ሕጉን ተላልፈዋልና፣ ሥርዓቱንም ለውጠዋልና፣ የዘላለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋልና፣ ምድርም ከሚቀመጡባት በታች ረክሳለች። BSB BSB: The earth is defiled by its people; they have transgressed the laws; they have overstepped the decrees and broken the everlasting covenant.
6 ULB ስለዚህ መርገም ምድርን ትበላለች፣ የሚኖሩባትም ጥፋተኞች ይሆናሉ። ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይቃጠላሉ፣ ጥቂት ሰዎችም ይቀራሉ። BSB BSB: Therefore a curse has consumed the earth, and its inhabitants must bear the guilt; the earth’s dwellers have been burned, and only a few survive.
7 ULB አዲስ የወይን ጠጅ ይደርቃል፣ የወይን ንግድ ደከመች፣ ልባቸው ደስ ያለው ሁሉ ተከዙ። BSB BSB: The new wine dries up, the vine withers. All the merrymakers now groan.
8 ULB የከበሮው ደስታ ቆሟል፣ የደስተኞች ድምፅ ዝም ብሎአል፣ የመሰንቆ ደስታ ቀርቶአል። BSB BSB: The joyful tambourines have ceased; the noise of revelers has stopped; the joyful harp is silent.
9 ULB እየዘፈኑም የወይን ጠጅን አይጠጡትም፣ የሚያሰክርም መጠጥ ለሚጠጡት መራራ ይሆናል። BSB BSB: They no longer sing and drink wine; strong drink is bitter to those who consume it.
10 ULB የተቃወሰችው ከተማ ፈረሰች፤ ቤት ሁሉ ተዘግቶ ባዶ ሆነ። BSB BSB: The city of chaos is shattered; every house is closed to entry.
11 ULB ስለ ወይኑም ጠጅ በአደባባይ ለቅሶ ይሆናል፤ ደስታ ሁሉ ጨልሞአል፥ የምድርም ደስታ ጠፍቷል። BSB BSB: In the streets they cry out for wine. All joy turns to gloom; rejoicing is exiled from the land.
12 ULB ከተማይቱም ባድማ ሆናለች፣ በርዋም በጥፋት ተመትቶአል። BSB BSB: The city is left in ruins; its gate is reduced to rubble.
13 ULB የወይራን ዛፍ እንደ መምታት፣ ከወይንም መከር በኋላ ቃርሚያውን እንደ መልቀም፣ እንዲሁ በምድር መካከል በአሕዛብም መካከል ይሆናል። BSB BSB: So will it be on the earth and among the nations, like a harvested olive tree, like a gleaning after a grape harvest.
14 ULB እነዚህ ድምፃቸውን አሰምተው እልል ይላሉ፣ ስለ እግዚአብሔር ክብርም ከባሕር በደስታ ይጮኻሉ። BSB BSB: They raise their voices, they shout for joy; from the west they proclaim the majesty of the LORD.
15 ULB ስለዚህ እግዚአብሔርን በምሥራቅ፣ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሔርንም ስም በባሕር ደሴቶች አክብሩ። BSB BSB: Therefore glorify the LORD in the east. Extol the name of the LORD, the God of Israel in the islands of the sea.
16 ULB "ለጻድቁ ክብር ይሁን!" የሚለውን ዝማሬ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እኔ ግን፣ "ባከንሁ፣ ባከንሁ፣ ወዮልኝ! ወንጀለኞች ወንጅለዋል፤ አዎን፣ ወንጀለኞች እጅግ ወንጅለዋል" አልሁ። BSB BSB: From the ends of the earth we hear singing: “Glory to the Righteous One.” But I said, “I am wasting away! I am wasting away! Woe is me.” The treacherous betray; the treacherous deal in treachery.
17 ULB በምድር ላይ የምትኖር ሆይ፣ ፍርሃትና ገደል ወጥመድም በአንተ ላይ አሉ። BSB BSB: Terror and pit and snare await you, O dweller of the earth.
18 ULB ከፍርሃት ድምፅ የሸሸ፣ በገደል ይወድቃል፤ ከገደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል። የሰማይ መስኮቶች ተከፍተዋል፣ የምድርም መሠረት ተናውጣለች። BSB BSB: Whoever flees the sound of panic will fall into the pit, and whoever climbs from the pit will be caught in the snare. For the windows of heaven are open, and the foundations of the earth are shaken.
19 ULB ምድር ፈጽሞ ትሰባበራለች፣ ምድር ፈጽማ ደቀቀች፤ ምድር በኃይል ትነዋወጣለች። BSB BSB: The earth is utterly broken apart, the earth is split open, the earth is shaken violently.
20 ULB ምድር እንደ ሰካራም ሰው ትንገዳገዳለች፣ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች። መተላለፍዋ ይከብድባታል፣ ትወድቃለች ደግማም አትነሣም። BSB BSB: The earth staggers like a drunkard and sways like a shack. Earth’s rebellion weighs it down, and it falls, never to rise again.
21 ULB በዚያም ቀን እንደዚህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በከፍታ ያለውን ሠራዊት በከፍታ ላይ፣ በምድርም ያሉትን ነገሥታት በምድር ላይ ይቀጣቸዋል። BSB BSB: In that day the LORD will punish the host of heaven above and the kings of the earth below.
22 ULB ግዞተኞች በጕድጓድ እንደሚከማቹ በአንድነት ይከማቻሉ፣ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ፣ ከብዙ ቀንም በኋላ ይፈረድባቸዋል። BSB BSB: They will be gathered together like prisoners in a pit. They will be confined to a dungeon and punished after many days.
23 ULB ከዚያም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ ይነግሣልና፣ በሽማግሌዎቹም ፊት ክብር ይሆናልና ጨረቃ ያፍራል፣ ፀሐይም ይዋረዳል። BSB BSB: The moon will be confounded and the sun will be ashamed; for the LORD of Hosts will reign on Mount Zion and in Jerusalem, and before His elders with great glory.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.