1 ULB ተመልከቱ፣ ንጉሥ በጽድቅ ይነግሣል፣ መሳፍንትም በፍርድ ይገዛሉ። BSB BSB: Behold, a king will reign in righteousness, and princes will rule with justice.
2 ULB ሰውም ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ፣ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፣ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፣ በበረሃም አገር እንደ ትልቅ ድንጋይ ጥላ ይሆናል። BSB BSB: Each will be like a shelter from the wind, a refuge from the storm, like streams of water in a dry land, like the shadow of a great rock in an arid land.
3 ULB ከዚያም፣ የሚያዩትም ሰዎች ዓይኖች አይደበዝዙም፣ የሚሰሙትም ጆሮች በትኩረት ያደምጣሉ። BSB BSB: Then the eyes of those who see will no longer be closed, and the ears of those who hear will listen.
4 ULB ጥንቃቄ የሌላቸው ሰዎች ልብ እውቀትን ታስተውላለች፣ የተብታቦችም ምላስ በቀላሉ አድርጋ ትናገራለች። BSB BSB: The mind of the rash will know and understand, and the stammering tongue will speak clearly and fluently.
5 ULB ከእንግዲህ ወዲህ ሰነፍ ከበርቴ ተብሎ አይጠራም፣ አታላዩም የተገራ አይባልም። BSB BSB: No longer will a fool be called noble, nor a scoundrel be respected.
6 ULB ሰነፍ ግን ስንፍናን ይናገራል፣ ልቡም ዝንጉነትን ይፈጽም ዘንድ በእግዚአብሔርም ላይ ስሕተትን ይናገር ዘንድ፣ የተራበችውንም ሰውነት ባዶ ያደርግ ዘንድ፣ ከተጠማም ሰው መጠጥን ይቈርጥ ዘንድ በደልን ይሠራል። BSB BSB: For a fool speaks foolishness; his mind plots iniquity. He practices ungodliness and speaks falsely about the LORD; he leaves the hungry empty and deprives the thirsty of drink.
7 ULB የንፉግም ዕቃ ክፉ ናት። ችግረኛ ትክክል ነገርን በተናገረ ጊዜ እንኳ እርሱ በሐሰት ቃል ድሀውን ያጠፋ ዘንድ ክፉን አሳብ ያስባል። BSB BSB: The weapons of the scoundrel are destructive; he hatches plots to destroy the poor with lies, even when the plea of the needy is just.
8 ULB ነገር ግን፣ ከበርቴው ሰው ለመከበር ያስባል፤ በመከበርም ጸንቶ ይኖራል። BSB BSB: But a noble man makes honorable plans; he stands up for worthy causes.
9 ULB እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፣ ተነሡ፣ ድምፄንም ስሙ፤ እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ልጆች ሆይ፣ ንግግሬን አድምጡ። BSB BSB: Stand up, you complacent women; listen to me. Give ear to my word, you overconfident daughters.
10 ULB እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ሆይ፣ ወይንን መሰብሰብ ይቀራልና፣ ፍሬም ማከማቸት አይመጣምና ከዓመትና ከጥቂት ቀን በኋላ ትንቀጠቀጣላችሁ። BSB BSB: In a little more than a year you will tremble, O secure ones. For the grape harvest will fail and the fruit harvest will not arrive.
11 ULB እናንተ ዓለመኞች ሴቶች ሆይ፣ ተጠንቀቁ፤ ተማምናችሁም የምትቀመጡ ሆይ፣ ተንቀጥቀጡ፤ የቅምጥል ልብሳችሁን አውልቁ፣ ዕራቁታችሁን ሁኑ፣ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ። BSB BSB: Shudder, you ladies of leisure; tremble, you daughters of complacency. Strip yourselves bare and put sackcloth around your waists.
12 ULB ስለ ተወደደችውም እርሻ፣ ስለሚያፈራውም ወይን ደረታችሁን ድቁ። BSB BSB: Beat your breasts for the pleasant fields, for the fruitful vines,
13 ULB በሕዝቤ ምድር ላይ፣ በደስታ ከተማ ባሉት በደስታ ቤቶች ሁሉ ላይ እሾህና ኵርንችት ይወጣባቸዋል፤ BSB BSB: and for the land of my people, overgrown with thorns and briers—even for every house of merriment in this city of revelry.
14 ULB አዳራሹ ወና ትሆናለችና፣ የብዙ ሰውም ከተማ ትለቅቃለችና፣ አምባውና ግንቡም ለዘላለም ዋሻ፣ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፣ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናልና፤ BSB BSB: For the palace will be forsaken, the busy city abandoned. The hill and the watchtower will become caves forever—the delight of wild donkeys and a pasture for flocks—
15 ULB ይህም፣ መንፈስ ከላይ እስኪፈስስልን፣ ምድረ በዳውም ፍሬያማ እርሻ እስኪሆን፣ ፍሬያማውም እርሻ ጫካ ተብሎ እስኪቈጠር ድረስ ይሆናል። BSB BSB: until the Spirit is poured out upon us from on high. Then the desert will be an orchard, and the orchard will seem like a forest.
16 ULB ከዚያ በኋላ ፍርድ በምድረ በዳ ይኖራል፤ ጽድቅም በፍሬያማው እርሻ ያድራል። BSB BSB: Then justice will inhabit the wilderness, and righteousness will dwell in the fertile field.
17 ULB የጽድቅም ሥራ ሰላም፣ የጽድቅም ፍሬ ለዘላለም ጸጥታና መታመን ይሆናል። BSB BSB: The work of righteousness will be peace; the service of righteousness will be quiet confidence forever.
18 ULB ሕዝቤም በሰላም ማደሪያ፣ በታመነም ቤት በጸጥተኛ ማረፊያ ይቀመጣል። BSB BSB: Then my people will dwell in a peaceful place, in safe and secure places of rest.
19 ULB በረዶ ግን በዱር ላይ ይወርዳል፣ ከተማም ፈጽማ ትዋረዳለች፣ BSB BSB: But hail will level the forest, and the city will sink to the depths.
20 ULB እናንተ የበሬና የአህያ እግር እየነዳችሁ በውኃ ሁሉ አጠገብ የምትዘሩ ትባረካላችሁ። BSB BSB: Blessed are those who sow beside abundant waters, who let the ox and donkey range freely.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.