1 ULB "አጽናኑ፣ ሕዝቤን አጽናኑ" ይላል አምላካችሁ። BSB BSB: “Comfort, comfort My people,” says your God.
2 ULB ለኢየሩሳሌም ልብ ተናገሩ የተቀጠረችበት ወራት እንደ ተፈጸመ፣ ኃጢአትዋም እንደ ተሰረየ፣ ከእግዚአብሔርም እጅ ስለ ኃጢአትዋ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀበለች ወደ እርስዋ ጩኹ። BSB BSB: “Speak tenderly to Jerusalem, and proclaim to her that her forced labor has been completed; her iniquity has been pardoned. For she has received from the hand of the LORD double for all her sins.”
3 ULB የሚጮኽ የአዋጅ ነጋሪ ቃል፣ "የእግዚአብሔርን መንገድ በምድረ በዳ አዘጋጁ፤ ለአምላካችንም ጐዳና በበረሀ አስተካክሉ።" BSB BSB: A voice of one calling: “Prepare the way for the LORD in the wilderness; make a straight highway for our God in the desert.
4 ULB ሸለቆው ሁሉ ከፍ ይላል፣ ተራራውና ኮረብታውም ሁሉ ዝቅ ይላል፤ ጠማማውም ይቃናል፣ ስርጓጕጡም ሜዳ ይሆናል፤ BSB BSB: Every valley shall be lifted up, and every mountain and hill made low; the uneven ground will become smooth, and the rugged land a plain.
5 ULB የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጣል፣ ሥጋ ለባሹም ሁሉ በአንድነት ያየዋል፣ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና። BSB BSB: And the glory of the LORD will be revealed, and all humanity together will see it.” For the mouth of the LORD has spoken.
7 ULB የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው። BSB BSB: The grass withers and the flowers fall when the breath of the LORD blows on them; indeed, the people are grass.
9 ULB የምስራች የምትነግሪ ጽዮን ሆይ፣ ከፍ ወዳለው ተራራ ውጪ፣ የምስራች የምትነግሪ ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ድምፅሽን በኃይል አንሺ፣ አንሺ፣ አትፍሪ፤ ለይሁዳም ከተሞች፣ "እነሆ፣ አምላካችሁ!" ብለሽ ንገሪ። BSB BSB: Go up on a high mountain, O Zion, herald of good news. Raise your voice loudly, O Jerusalem, herald of good news. Lift it up, do not be afraid! Say to the cities of Judah, “Here is your God!”
10 ULB ተመልከቱ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይመጣል። ክንዱም ስለ እርሱ ይገዛል፤ እነሆ፣ ዋጋው ከእርሱ ጋር ደመወዙም በፊቱ ነው። BSB BSB: Behold, the Lord GOD comes with might, and His arm establishes His rule. His reward is with Him, and His recompense accompanies Him.
11 ULB መንጋውን እንደ እረኛ ያሰማራል፣ ጠቦቶቹን በክንዱ ሰብስቦ በብብቱ ይሸከማል፣ የሚያጠቡትንም በቀስታ ይመራል። BSB BSB: He tends His flock like a shepherd; He gathers the lambs in His arms and carries them close to His heart. He gently leads the nursing ewes.
13 ULB የእግዚአብሔርን መንፈስ ያዘዘ፣ ወይስ አማካሪ ሆኖ ያስተማረው ማን ነው? BSB BSB: Who has directed the Spirit of the LORD, or informed Him as His counselor?
14 ULB ወይስ ከማን ጋር ተመካከረ? ወይስ ማን መከረው? የፍርድንም መንገድ ማን አስተማረው? እውቀትንስ ማን አስተማረው? የማስተዋልንስ መንገድ ማን አሳየው? BSB BSB: Whom did He consult to enlighten Him, and who taught Him the paths of justice? Who imparted knowledge to Him and showed Him the way of understanding?
15 ULB ተመልከቱ፣ አሕዛብ በገንቦ እንዳለች ጠብታ ናቸው፣ በሚዛንም እንዳለ ትንሽ ትቢያ ተቈጥረዋል፤ ተመልከቱ፣ ደሴቶችን እንደ ቀላል ነገር ያነሣል። BSB BSB: Surely the nations are like a drop in a bucket; they are considered a speck of dust on the scales; He lifts up the islands like fine dust.
16 ULB ሊባኖስ ለማንደጃ፣ እንስሶችዋም ለሚቃጠል መሥዋዕት አይበቁም። BSB BSB: Lebanon is not sufficient for fuel, nor its animals enough for a burnt offering.
17 ULB አሕዛብ ሁሉ በፊቱ እንዳልነበሩ ናቸው፤ ከምናምን እንደሚያንሱ፣ እንደ ከንቱ ነገርም ይቈጥራቸዋል። BSB BSB: All the nations are as nothing before Him; He regards them as nothingness and emptiness.
18 ULB እንግዲህ እግዚአብሔርን በማን ትመስሉታላችሁ? ወይስ በምን ምሳሌ ታስተያዩታላችሁ? BSB BSB: To whom will you liken God? To what image will you compare Him?
19 ULB የተቀረጸውንስ ምስል! ሠራተኛ ሠርቶታል፤ አንጥረኛም በወርቅ ለብጦታል፣ የብሩንም ሰንሠለት አፍስሶለታል። BSB BSB: To an idol that a craftsman casts and a metalworker overlays with gold and fits with silver chains?
20 ULB ለዚህ መባዕ ገንዘቡ ያልበቃው ድሀ የማይነቅዘውን እንጨት ይመርጣል፤ ምስሉም እንዳይናወጥ ያቆመው ዘንድ ብልህ ሠራተኛን ይፈልጋል። BSB BSB: One lacking such an offering chooses wood that will not rot. He seeks a skilled craftsman to set up an idol that will not topple.
21 ULB አላወቃችሁምን? ወይስ አልሰማችሁምን? ከጥንትስ አልተወራላችሁምን? ወይስ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን? BSB BSB: Do you not know? Have you not heard? Has it not been declared to you from the beginning? Have you not understood since the foundation of the earth?
22 ULB እርሱ በምድር ክበብ ላይ ይቀምጣል፣ በእርስዋም የሚኖሩት እንደ አንበጣ ናቸው፤ ሰማያትን እንደ መጋረጃ የሚዘረጋቸው እንደ ድንኳንም ለመኖርያ የሚዘረጋቸው፥ BSB BSB: He sits enthroned above the circle of the earth; its dwellers are like grasshoppers. He stretches out the heavens like a curtain, and spreads them out like a tent to dwell in.
23 ULB አለቆችንም እንዳልነበሩ፣ የምድርንም ፈራጆች እንደ ከንቱ ነገር የሚያሳንሳቸው እርሱ ነው። BSB BSB: He brings the princes to nothing and makes the rulers of the earth meaningless.
24 ULB ተመልከቱ፣ ገና እንደ ተተከሉና እንደ ተዘሩ፣ በምድርም ሥር ገና እንደ ሰደዱ ወዲያውኑ ነፈሰባቸው፣ እነርሱም ደረቁ፣ ዐውሎ ነፋስም እንደ እብቅ ጠረጋቸው። BSB BSB: No sooner are they planted, no sooner are they sown, no sooner have their stems taken root in the ground, than He blows on them and they wither, and a whirlwind sweeps them away like stubble.
25 ULB "እንግዲህ እተካከለው ዘንድ በማን መሰላችሁኝ?" ይላል ቅዱሱ። BSB BSB: “To whom will you liken Me, or who is My equal?” asks the Holy One.
26 ULB ዓይናችሁን ወደ ላይ አንሥታችሁ ተመልከቱ፤ እነዚህን የፈጠረ ማን ነው? ሠራዊታቸውን በቍጥር የሚያወጣ እርሱ ነው፣ ሁሉንም በየስማቸው ይጠራቸዋል፤ በኃይሉ ብዛትና በችሎቱ ብርታት አንድስ እንኳ አይታጣውም። BSB BSB: Lift up your eyes on high: Who created all these? He leads forth the starry host by number; He calls each one by name. Because of His great power and mighty strength, not one of them is missing.
27 ULB ያዕቆብ ሆይ፣ እስራኤልም ሆይ፣ "መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች፣ ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች" ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? BSB BSB: Why do you say, O Jacob, and why do you assert, O Israel, “My way is hidden from the LORD, and my claim is ignored by my God”?
29 ULB ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፤ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። BSB BSB: He gives power to the faint and increases the strength of the weak.
30 ULB ብላቴኖች ይደክማሉ፣ ይታክቱማል፣ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ፤ BSB BSB: Even youths grow tired and weary, and young men stumble and fall.
31 ULB እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፣ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፣ አይደክሙም። BSB BSB: But those who wait upon the LORD will renew their strength; they will mount up with wings like eagles; they will run and not grow weary, they will walk and not faint.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.