2 ULB አይጮኽም ቃሉንም አያነሣም፣ ድምፁንም በጎዳናዎች አያሰማም። BSB BSB: He will not cry out or raise His voice, nor make His voice heard in the streets.
3 ULB የተቀጠቀጠን ሸምበቆ አይሰብርም፣ የሚጤስንም ክር አያጠፋም፤ በእውነት ፍርድን ያወጣል። BSB BSB: A bruised reed He will not break and a smoldering wick He will not extinguish; He will faithfully bring forth justice.
4 ULB በምድርም ፍትሕን እስኪያደርግ ድረስ ይበራል እንጂ አይጠፋም፤ አሕዛብም ሕጉን ይጠብቃሉ። BSB BSB: He will not grow weak or discouraged before He has established justice on the earth. In His law the islands will put their hope.”
5 ULB ሰማያትን የፈጠረ የዘረጋቸውም፣ ምድርንና በውስጥዋ ያለውን ያጸና፣ በእርስዋ ላይ ለሚኖሩ ሕዝብ እስትንፋስን፣ ለሚሄዱባትም መንፈስን የሚሰጥ አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ BSB BSB: This is what God the LORD says—He who created the heavens and stretched them out, who spread out the earth and its offspring, who gives breath to the people on it and life to those who walk in it:
7 ULB የዕውሩንም ዓይን ትከፍት ዘንድ፣ የተጋዘውንም ከግዞት ቤት በጨለማም የተቀመጡትን ከወህኒ ቤት ታወጣ ዘንድ ለሕዝብ ቃል ኪዳን ለአሕዛብም ብርሃን አድርጌ እሰጥሃለሁ። BSB BSB: to open the eyes of the blind, to bring prisoners out of the dungeon and those sitting in darkness out from the prison house.
9 ULB ተመልከቱ፣ የቀድሞው ነገር ተፈጸመ፣ አዲስ ክስተቶችንም እናገራለሁ። አስቀድሞም ሳይከሰት ስለ እነርሱ አስታውቃችኋለሁ።" BSB BSB: Behold, the former things have happened, and now I declare new things. Before they spring forth I proclaim them to you.”
10 ULB ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርስዋም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፣ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ ሆይ፣ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፣ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ። BSB BSB: Sing to the LORD a new song—His praise from the ends of the earth—you who go down to the sea, and all that is in it, you islands, and all who dwell in them.
12 ULB ለእግዚአብሔር ክብርን ይስጡ፣ ምስጋናውንም በደሴቶች ይናገሩ። BSB BSB: Let them give glory to the LORD and declare His praise in the islands.
13 ULB እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይወጣል፤ እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፤ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል፣ በጠላቶቹም ላይ ኃይሉን ያሳያል። BSB BSB: The LORD goes forth like a mighty one; He stirs up His zeal like a warrior. He shouts; yes, He roars in triumph over His enemies:
14 ULB ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፤ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፤ አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እጮኻለሁ፤ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ። BSB BSB: “I have kept silent from ages past; I have remained quiet and restrained. But now I will groan like a woman in labor; I will at once gasp and pant.
15 ULB ተራሮችንና ኮረብቶችን አፈርሳለሁ፣ ቡቃያዎቻቸውንም ሁሉ አደርቃለሁ፤ ወንዞችንም ደሴቶች አደርጋለሁ፣ ኵሬዎችንም አደርቃለሁ። BSB BSB: I will lay waste the mountains and hills and dry up all their vegetation. I will turn the rivers into dry land and drain the marshes.
16 ULB ዕውሮችንም በማያውቋት መንገድ አመጣቸዋለሁ፤ በማያውቋትም ጎዳና እመራቸዋለሁ፤ በፊታቸውም ጨለማውን ብርሃን አደርጋለሁ፣ ጠማማውንም አቀናለሁ። ይህን አደርግላቸዋለሁ፣ አልተዋቸውምም። BSB BSB: I will lead the blind by a way they did not know; I will guide them on unfamiliar paths. I will turn darkness into light before them and rough places into level ground. These things I will do for them, and I will not forsake them.
17 ULB በተቀረጹትም ምስሎች የሚታመኑ፣ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎች፣ "አምላኮቻችን ናችሁ" የሚሉ ወደ ኋላቸው ይመለሳሉ ፈጽመውም ያፍራሉ። BSB BSB: But those who trust in idols and say to molten images, ‘You are our gods!’ will be turned back in utter shame.
18 ULB እናንተ ደንቆሮች፣ ስሙ፤ እናንተም ዕውሮች፣ ታዩ ዘንድ ተመልከቱ። BSB BSB: Listen, you deaf ones; look, you blind ones, that you may see!
19 ULB ከባሪያዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ በቀር ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹሙ ወይስ እንደ እግዚአብሔር ባሪያ ዕውር የሆነ ማን ነው? BSB BSB: Who is blind but My servant, or deaf like the messenger I am sending? Who is blind like My covenant partner, or blind like the servant of the LORD?
20 ULB ብዙ ነገርን ታያላችሁ ነገር ግን አትገነዘቡትም፤ ጆሮአችሁም ተከፍተዋል፣ ነገር ግን አትሰሙም። BSB BSB: Though seeing many things, you do not keep watch. Though your ears are open, you do not hear.”
21 ULB እግዚአብሔር ስለ ጽድቁ ሕጉን ታላቅ ያደርግና ያከብር ዘንድ ወደደ። BSB BSB: The LORD was pleased, for the sake of His righteousness, to magnify His law and make it glorious.
22 ULB ይህ ግን የተበዘበዘና የተዘረፈ ሕዝብ ነው፤ ሁላቸው በዋሻ ውስጥ ተጠምደዋል፣ በግዞት ቤትም ተሸሽገዋል፤ ብዝበዛ ሆነዋል የሚያድንም የለም፣ ምርኮም ሆነዋል፣ ማንም፣ "መልሷቸው!" የሚል የለም። BSB BSB: But this is a people plundered and looted, all trapped in caves or imprisoned in dungeons. They have become plunder with no one to rescue them, and loot with no one to say, “Send them back!”
23 ULB ከመካከላችሁ ይህን የሚያደምጥ፣ ለሚመጣውም ጊዜ የሚያደምጥና የሚሰማ ማን ነው? BSB BSB: Who among you will pay attention to this? Who will listen and obey hereafter?
24 ULB ያዕቆብን ለማረኩ እስራኤልንም ለበዘበዙ ሰዎች የሰጠ ማን ነው? እኛ የበደልነው፥ እነርሱም በመንገዱ ይሄዱ ዘንድ ያልወደዱት ለሕጉም ያልታዘዙለት እግዚአብሔር እርሱ አይደለምን? BSB BSB: Who gave Jacob up for spoil, and Israel to the plunderers? Was it not the LORD, against whom we have sinned? They were unwilling to walk in His ways, and they would not obey His law.
25 ULB ስለዚህ፣ የቍጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አፈሰሰበት። በዙሪያም አነደደው እርሱ ግን አላወቀም፣ አቃጠለውም እርሱ ግን ልብ አላደረገም። BSB BSB: So He poured out on them His furious anger and the fierceness of battle. It enveloped them in flames, but they did not understand; it consumed them, but they did not take it to heart.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.