1 ULB ብርሃንሽ መጥቶአልና፣ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፣ አብሪ። BSB BSB: Arise, shine, for your light has come, and the glory of the LORD rises upon you.
2 ULB እነሆ፣ ጨለማ ምድርን ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይወጣል፣ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤ BSB BSB: For behold, darkness covers the earth, and thick darkness is over the peoples; but the LORD will rise upon you, and His glory will appear over you.
3 ULB አሕዛብም ወደ ብርሃንሽ ነገሥታትም ወደ መውጫሽ ጸዳል ይመጣሉ። BSB BSB: Nations will come to your light, and kings to the brightness of your dawn.
4 ULB ዓይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ። እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፣ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል። BSB BSB: Lift up your eyes and look around: They all gather and come to you; your sons will come from afar, and your daughters will be carried on the arm.
5 ULB በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፣ የአሕዛብም ብልጥግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፣ አይተሽ ደስ ይልሻል፣ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል። BSB BSB: Then you will look and be radiant, and your heart will tremble and swell with joy, because the riches of the sea will be brought to you, and the wealth of the nations will come to you.
6 ULB የግመሎች ብዛት፣ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፣ ይሸፍኑሻል፤ ሁሉ ከሳባ ይመጣሉ፣ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ የእግዚአብሔርንም ምስጋና ያወራሉ። BSB BSB: Caravans of camels will cover your land, young camels of Midian and Ephah, and all from Sheba will come, bearing gold and frankincense and proclaiming the praises of the LORD.
7 ULB የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፣ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፣ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ። BSB BSB: All the flocks of Kedar will be gathered to you; the rams of Nebaioth will serve you and go up on My altar with acceptance; I will adorn My glorious house.
8 ULB ርግቦች ወደ ቤታቸው እንደሚበርሩ፣ እነዚህ እንደ ደመና የሚበርሩ እነማን ናቸው? BSB BSB: Who are these who fly like clouds, like doves to their shelters?
9 ULB እርሱ አክብሮሻልና ለአምላክሽ ለእግዚአብሔር ስምና ለእስራኤል ቅዱስ ልጆችሽን ከሩቅ ከእነርሱ ጋርም ብራቸውንና ወርቃቸውን ያመጡ ዘንድ ደሴቶች የተርሴስ መርከቦችም አስቀድመው ይጠባበቁኛል። BSB BSB: Surely the islands will wait for Me, with the ships of Tarshish in the lead, to bring your children from afar, with their silver and gold, to the honor of the LORD your God, the Holy One of Israel, for He has glorified you.
10 ULB በቍጣዬ ቀሥፌ በፍቅሬ ምሬሻለሁና መጻተኞች ቅጥርሽን ይሠራሉ፣ ነገሥታቶቻቸውም ያገለግሉሻል። BSB BSB: Foreigners will rebuild your walls, and their kings will serve you. Although I struck you in anger, yet in favor I will show you mercy.
11 ULB በሮችሽም ሁልጊዜ ይከፈታሉ፤ ሰዎች የአሕዛብን ብልጥግና የተማረኩትንም ነገሥታቶቻቸውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊትና ቀን አይዘጉም። BSB BSB: Your gates will always stand open; they will never be shut, day or night, so that the wealth of the nations may be brought into you, with their kings being led in procession.
12 ULB ለአንቺም የማይገዛ ሕዝብና መንግሥት ይጠፋል፣ እነዚያ አሕዛብም ፈጽመው ይጠፋሉ። BSB BSB: For the nation or kingdom that will not serve you will perish; it will be utterly destroyed.
13 ULB የመቅደሴንም ስፍራ ያስጌጡ ዘንድ የሊባኖስ ክብር፣ ጥዱና አስታው ባርሰነቱም፣ ወደ አንቺ ይመጣሉ፣ የእግሬንም ስፍራ አከብራለሁ። BSB BSB: The glory of Lebanon will come to you—its cypress, elm, and boxwood together—to adorn the place of My sanctuary, and I will glorify the place of My feet.
14 ULB የአስጨናቂዎችሽም ልጆች አንገታቸውን ደፍተው ወደ አንቺ ይመጣሉ፣ የናቁሽም ሁሉ ወደ እግርሽ ጫማ ይሰግዳሉ፤ የእግዚአብሔርም ከተማ፣ የእስራኤል ቅዱስ የሆንሽ ጽዮን ይሉሻል። BSB BSB: The sons of your oppressors will come and bow down to you; all who reviled you will fall facedown at your feet and call you the City of the LORD, Zion of the Holy One of Israel.
15 ULB ከሰውም ማንም እስከማያልፍብሽ ድረስ የተተውሽና የተጠላሽ ነበርሽ፤ ነገር ግን የዘላለም ትምክሕትና የልጅ ልጅ ደስታ አደርግሻለሁ። BSB BSB: Whereas you have been forsaken and despised, with no one passing through, I will make you an everlasting pride, a joy from age to age.
16 ULB የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ፣ የነገሥታትንም ጡት ትጠቢያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የያዕቆብ ኃይል፣ መድኃኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ። BSB BSB: You will drink the milk of nations and nurse at the breasts of royalty; you will know that I, the LORD, am your Savior and your Redeemer, the Mighty One of Jacob.
17 ULB በናስ ፋንታ ወርቅን፣ በብረትም ፋንታ ብርን፣ በእንጨትም ፋንታ ናስን፣ በድንጋይም ፋንታ ብረትን አመጣለሁ። አለቆችሽንም ሰላም፣ የበላይ ገዢዎችሽንም ጽድቅ አደርጋለሁ፤ BSB BSB: Instead of bronze I will bring you gold; I will bring silver in place of iron, bronze instead of wood, and iron instead of stones. I will appoint peace as your governor and righteousness as your ruler.
18 ULB ከዚያ በኋላ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፣ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥርሽን መዳን በሮችሽንም ምስጋና ብለሽ ትጠሪያለሽ BSB BSB: No longer will violence be heard in your land, nor ruin or destruction within your borders. But you will name your walls Salvation and your gates Praise.
19 ULB ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፣ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አይበራልሽም። BSB BSB: No longer will the sun be your light by day, nor the brightness of the moon shine on your night; for the LORD will be your everlasting light, and your God will be your splendor.
20 ULB እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ ይሆናልና፣ የልቅሶሽም ወራት ታልቃለችና ፀሐይሽ ከዚያ በኋላ አትጠልቅም ጨረቃሽም አይቋረጥም። BSB BSB: Your sun will no longer set, and your moon will not wane; for the LORD will be your everlasting light, and the days of your sorrow will cease.
21 ULB ሕዝብሽም ሁሉ ጻድቃን ይሆናሉ፤ እኔም እከብር ዘንድ የአታክልቴን ቡቃያ፣ የእጄ ሥራ የምትሆን ምድሪቱንም ለዘላለም ይወርሳሉ። BSB BSB: Then all your people will be righteous; they will possess the land forever; they are the branch of My planting, the work of My hands, so that I may be glorified.
22 ULB ታናሹ ለሺህ የሁሉም ታናሹ ለብርቱ ሕዝብ ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር በዘመኑ ይህን አፋጥነዋለሁ። BSB BSB: The least of you will become a thousand, and the smallest a mighty nation. I am the LORD; in its time I will accomplish it quickly.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.