1 ULB በእናንተ መከከል ያለው ፀብና ጭቅጭቅ ከየት የመጣ ነው? በውስጣችሁ ውጊያ ከገጠሙት ክፉ ምኞቶቻችሁ የመጣ አይደለምን? BSB BSB: What causes conflicts and quarrels among you? Don’t they come from the passions at war within you?
2 ULB የሌላችሁን ትመኛላችሁ። ትገድላላችሁ፤ ማግኘት ያልቻላችሁትን በብርቱ ታሳድዳላችሁ። ትጣላላችሁ፤ ትዋጋላችሁ፤ ይሁን እንጂ፣ ከእግዚአብሔር ስለማትለምኑ አታገኙም። BSB BSB: You crave what you do not have; you kill and covet, but are unable to obtain it. You quarrel and fight. You do not have, because you do not ask.
3 ULB ትለምናላችሁ ግን አትቀበሉም፤ ምክንያቱም ክፉ ምኞቶቻችሁን ለማሳካት ክፉ ነገሮችን ስለምትለምኑ ነው። BSB BSB: And when you do ask, you do not receive, because you ask with wrong motives, that you may squander it on your pleasures.
4 ULB እናንት አመንዝሮች! የዓለም ወዳጅ መሆን፣ የእግዚአብሔር ጠላት መሆን እንደ ሆነ አታውቁም? ስለዚህ ማንም የዓለም ወዳጅ መሆን ቢፈልግ፣ የእግዚአብሔር ጠላት ይሆናል። BSB BSB: You adulteresses! Do you not know that friendship with the world is hostility toward God? Therefore, whoever chooses to be a friend of the world renders himself an enemy of God.
5 ULB ወይስ እግዚአብሔር እኛ ውስጥ ያኖረው መንፈስ ለእርሱ ብቻ እንድንሆን አብዝቶ ይቀናል የሚለው የመጽሐፍ ቃል በከንቱ የተነገረ ይመስላችኋል? BSB BSB: Or do you think the Scripture says without reason that the Spirit He caused to dwell in us yearns with envy?
6 ULB እግዚአብሔር ግን አብዝቶ ጸጋውን ይሰጣል፤ መጽሐፍ፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል” የሚለው በዚህ ምክንያት ነው። BSB BSB: But He gives us more grace. This is why it says: “God opposes the proud, but gives grace to the humble.”
7 ULB ስለዚህ፣ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙት፤ እርሱም ከእናንተ ይሸሻል። BSB BSB: Submit yourselves, then, to God. Resist the devil, and he will flee from you.
8 ULB ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፣ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች እጆቻችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ። BSB BSB: Draw near to God, and He will draw near to you. Cleanse your hands, you sinners, and purify your hearts, you double-minded.
9 ULB እዘኑ፤ አልቅሱ፤ ጩኹ! ሳቃችሁን ወደ ሐዘን፣ ደስታችሁን ወደ ትካዜ ለውጡ። BSB BSB: Grieve, mourn, and weep. Turn your laughter to mourning, and your joy to gloom.
10 ULB በጌታ ፊት ራሳችሁን ዝቅ አድርጉ፤ እርሱም ከፍ ያደርጋችኋል። BSB BSB: Humble yourselves before the Lord, and He will exalt you.
11 ULB ወንድሞች ሆይ፣ እርስ በርስ አትወነጃጀሉ። ወንድሙን የሚወነጅልና በወንድሙ ላይ የሚፈርድ ሕጉ ላይ ክፉ ይናገራል፤ በእግዚአብሔርም ሕግ ላይ ይፈርዳል። ሕጉ ላይ የምትፈርዱ ከሆነ፣ ፈራጆች እንጂ፣ ሕጉን አድራጊዎች አይደላችሁም። BSB BSB: Brothers, do not slander one another. Anyone who speaks against his brother or judges him speaks against the law and judges it. And if you judge the law, you are not a practitioner of the law, but a judge of it.
12 ULB ሕጉን የሰጠና በሕጉም የሚፈርድ፣ ማዳንም መግደልም የሚቻለው አንዱ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ታዲያ፣ በባልንጀራህ ላይ የምትፈርድ አንተ ማን ነህ? BSB BSB: There is only one Lawgiver and Judge, the One who is able to save and destroy. But who are you to judge your neighbor?
14 ULB ነገ የሚሆነውን የሚያውቅ ማን ነው? ሕይወታችሁስ ምንድን ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ ጭጋግ አይደላችሁምን? BSB BSB: You do not even know what will happen tomorrow! What is your life? You are a mist that appears for a little while and then vanishes.
15 ULB ይልቁንም፣ “ጌታ ቢፈቅድ እንኖራለን፤ ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን” ማለት ይኖርባችኋል። BSB BSB: Instead, you ought to say, “If the Lord is willing, we will live and do this or that.”
16 ULB አሁን ግን በዕቅዶቻችሁ ትመካላችሁ። እንዲህ ያለው ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው። BSB BSB: As it is, you boast in your proud intentions. All such boasting is evil.
17 ULB ስለዚህ መልካም የሆነውን ማድረግ እንዳለበት እያወቀ ለማያደርግ ለዚያ ሰው ኃጢአት ይሆንበታል። BSB BSB: Anyone, then, who knows the right thing to do, yet fails to do it, is guilty of sin.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.