1 ULB የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ መጣ፣ እንዲህም አለኝ፣ BSB BSB: Now the word of the LORD came to me, saying,
2 ULB "ሂድና በኢየሩሳሌም ጆሮ ጩኽ። እንዲህም በል 'እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወጣትነትሽ የነበረሽን የኪዳን ታማኝነት፣ በታጨሽበት ጊዜ የነበረሽን ፍቅር፣ ዘር ባልተዘራበት ምድረ በዳ እንደ ተከተልሽኝ ስለአንቺ አስታውሳለሁ። BSB BSB: “Go and proclaim in the hearing of Jerusalem that this is what the LORD says: ‘I remember the devotion of your youth, your love as a bride, how you followed Me in the wilderness, in a land not sown.
3 ULB እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረ፣ የእርሻው መከር በኩራትም ነበረ! ከበኩራቱ የበሉት ሁሉ ኃጢአት አድርገዋል! ክፉም ነገር ይመጣባቸዋል ይላል እግዚአብሔር።'" BSB BSB: Israel was holy to the LORD, the firstfruits of His harvest. All who devoured her were found guilty; disaster came upon them,’” declares the LORD.
4 ULB የያዕቆብ ቤትና የእስራኤልም ቤት ቤተሰቦች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። BSB BSB: Hear the word of the LORD, O house of Jacob, and all you families of the house of Israel.
5 ULB እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "አባቶቻችሁ ምን ክፋት አግኝተውብኝ ነው እኔን ከመከተል የራቁት፣ ከንቱ ጣዖታትንም የተከተሉት፣ እና ራሳቸውም ከንቱ የሆኑት? BSB BSB: This is what the LORD says: “What fault did your fathers find in Me that they strayed so far from Me? They followed worthless idols, and became worthless themselves.
6 ULB እነርሱም 'ከግብጽ ምድር ያወጣን እግዚአብሔር፣ በምድረ በዳ ጉድጓድ ወዳለበት የአረባህ ምድር፣ በውኃ ጥምና በሞት ጥላ ምድር፥ ማንም በማያልፍበትና ማንም በማይቀመጥበት ምድር የመራን እግዚአብሔር ወዴት አለ?' አላሉም። BSB BSB: They did not ask, ‘Where is the LORD who brought us up from the land of Egypt, who led us through the wilderness, through a land of deserts and pits, a land of drought and darkness, a land where no one travels and no one lives?’
7 ULB ነገር ግን ፍሬዋንና ሌሎች መልካም ነገሮቿን እንድትበሉ ወደ ቀርሜሎስ ምድር አገባኋችሁ! ይሁን እንጂ በመጣችሁ ጊዜ፣ ምድሬን አረከሳችሁ፣ ርስቴንም አጐሳቈላችሁ! BSB BSB: I brought you into a fertile land to eat its fruit and bounty, but you came and defiled My land and made My inheritance detestable.
8 ULB ካህናቱም 'እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፥ ባለ የኦሪቶች ሊቅ የሆኑትም ስለ እኔ ግድ አላላቸውም! እረኞችም በደሉኝ፥ ነቢያትም ለበኣል ትንቢት ተናገሩ፣ ትርፍ የሌለውንም ነገር ተከተሉ። BSB BSB: The priests did not ask, ‘Where is the LORD?’ The experts in the law no longer knew Me, and the leaders rebelled against Me. The prophets prophesied by Baal and followed useless idols.
9 ULB ስለዚህ እከስሳችኋለሁ- የልጆቻችሁንም ልጆች እከስሳለሁ። BSB BSB: Therefore, I will contend with you again, declares the LORD, and I will bring a case against your children’s children.
10 ULB ወደ ኪቲም ደሴቶች እለፉና ተመልከቱ። ወደ ቄዳርም መልእክተኞችን ላኩና እንደዚህ ያለ ነገር ህኖ እንደ ሆነ መርምራችሁ እዩ። BSB BSB: Cross over to the coasts of Cyprus and take a look; send to Kedar and consider carefully; see if there has ever been anything like this:
11 ULB አማልክት ባይሆኑ እንኳን አማልክት ያልሆኑትን አማልክቱን የለወጣቸው አንድ ሕዝብ አለን? ነገር ግን ሕዝቤ ሊረዳቸው ለማይችለው ነገር ክብሩን ለወጠ። BSB BSB: Has a nation ever changed its gods? (Yet they are not gods at all.) But My people have exchanged their Glory for useless idols.
12 ULB ሰማያት ከዚህ የተነሣ ተደነቁ! ተንቀጥቀጡ እና ደንግጡ ይላል እግዚአብሔር። BSB BSB: Be stunned by this, O heavens; be shocked and utterly appalled,” declares the LORD.
14 ULB እስራኤል ባርያ ነውን? ወይስ በቤት የተወለደ አይደለምን? እናስ ብዝበዛ የሆነው ለምንድነው? BSB BSB: Is Israel a slave? Was he born into slavery? Why then has he become prey?
15 ULB የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ። ብዙ ድምጽ በማሰማት ምድሩን አስፈሪ አደረጉት! ከተሞቹም የሚኖርባቸው እንዳይኖር ሆኖ ተደመሰሰ። BSB BSB: The young lions have roared at him; they have sounded their voices. They have laid waste his land; his cities lie in ruins, without inhabitant.
16 ULB የሜምፎስና የጣፍናስ ልጆች የራስ ቅልሽን ላጭተው ባርያዎችን ከአንቺ ወሰዱ! BSB BSB: The men of Memphis and Tahpanhes have shaved the crown of your head.
17 ULB ይህን ሁሉ በራስሽ ላይ ያደረግሽው በመንገድ ላይ ሲመራሽ አምላክሽን እግዚአብሔርን ስለተውሽ አይደለምን? ይላል እግዚአብሔር አምላክሽ። BSB BSB: Have you not brought this on yourself by forsaking the LORD your God when He led you in the way?
18 ULB አሁንስ በግብጽ መንገድ ሄደሽ የሺሖርን ውኃ የምትጠጪው ለምንድነው? በአሦርስ መንገድ ሄደሽ የኤፍራጥስንም ውኃ የምትጠጪው ለምንድነው? BSB BSB: Now what will you gain on your way to Egypt to drink the waters of the Nile? What will you gain on your way to Assyria to drink the waters of the Euphrates?
19 ULB ክፋትሽ ይገሥጽሻል፣ ክዳትሽም ይቀጣሻል፤ አምላክሽንም እግዚአብሔርን መተውሽ እኔንም መፍራት ማቆምሽ ክፉና መራራ ነገር እንደ ሆነ እወቂ፥ ተመልከቺ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። BSB BSB: Your own evil will discipline you; your own apostasies will reprimand you. Consider and realize how evil and bitter it is for you to forsake the LORD your God and to have no fear of Me,” declares the Lord GOD of Hosts.
20 ULB ከጥንት ጀምሮ የነበረብሽን ቀንበር ሰብሬአለሁና፣ እስራትሽንም ቈርጫለሁ። እንዲህም ሆኖ አንቺ 'አላገለግልም!' አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ተጋደምሽ፣ አንቺ አመንዝራ። BSB BSB: “For long ago you broke your yoke and tore off your chains, saying, ‘I will not serve!’ Indeed, on every high hill and under every green tree you lay down as a prostitute.
21 ULB እኔ ራሴ ግን የተመረጠች ወይን፣ ፈጽሞ እውነተኛ የሆነ ዘር አድርጌ ተክዬሽ ነበር። አንቺ ግን ክፉ የእንግዳ ወይን ግንድ ሆነሽ እንዴት ተለወጥሽብኝ? BSB BSB: I had planted you like a choice vine from the very best seed. How could you turn yourself before Me into a rotten, wild vine?
22 ULB በወንዝ ብትታጠቢ ወይም በብርቱ ሳሙና ብትታጠቢ፣ በእኔ ፊት በኃጢአትሽ ረክሰሻል ይላል ጌታ እግዚአብሔር። BSB BSB: Although you wash with lye and use an abundance of soap, the stain of your guilt is still before Me,” declares the Lord GOD.
23 ULB 'አልረከስሁም! በአሊምንም አልተከተልሁም' እንዴት ትያለሽ? በሸለቆዎች ያለውን ባህርይሽን ተመልከቺ! ያደረግሽውንም ተገንዘቢ፣ በመንገዷ ላይ እንደ ተለቀቀች ፈጣን ግመል ሆነሻል፤ BSB BSB: “How can you say, ‘I am not defiled; I have not run after the Baals’? Look at your behavior in the valley; acknowledge what you have done. You are a swift young she-camel galloping here and there,
24 ULB በምኞትዋ ከንቱ ነፋስን እንደምታሸትት፣ ምድረ በዳ እንደ ለመደች እንደ ሜዳ አህያ ነሽ! ከምኞትዋ የሚመልሳት ማን ነው? የሚፈልጋት ሁሉ ራሱን አያደክምም። ወደ እርሷ ሄደው በትኩሳቷ ወራት ያገኟታል። BSB BSB: a wild donkey at home in the wilderness, sniffing the wind in the heat of her desire. Who can restrain her passion? All who seek her need not weary themselves; in mating season they will find her.
25 ULB እግርሽን ባዶ ከመሆን፣ ጉሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ! አንቺ ግን 'ተስፋ-ቢስ ነው! አይሆንም፣ እንግዶችን ወድጄአለሁና እከተላቸዋለሁ!' አልሽ። BSB BSB: You should have kept your feet from going bare and your throat from being thirsty. But you said, ‘It is hopeless! For I love foreign gods, and I must go after them.’
26 ULB ሌባ ሲያዝ እንደሚያፍረው ሁሉ፣ እንዲሁ የእስራኤል ቤት፣ እነርሱ፣ ንጉሦቻቸው፣ አለቆቻቸው፣ ካህናቶቻቸውና ነብያቶቻቸውም ያፍራሉ። BSB BSB: As the thief is ashamed when he is caught, so the house of Israel is disgraced. They, their kings, their officials, their priests, and their prophets
27 ULB ለዛፉ፣ 'አንተ አባቴ ነህ፣' ድንጋዮንም 'አንተ ወለድከኝ' ይላሉ። ፊታቸውንም ሳይሆን ጀርባቸውን ሰጡኝ። በመከራቸው ጊዜ ግን 'ተነሥና አድነን!' ይላሉ። BSB BSB: say to a tree, ‘You are my father,’ and to a stone, ‘You gave me birth.’ They have turned their backs to Me and not their faces. Yet in the time of trouble, they say, ‘Rise up and save us!’
28 ULB ለአንተ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ፥ አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቊጥር እንዲሁ ናቸውና ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ! BSB BSB: But where are the gods you made for yourselves? Let them rise up in your time of trouble and save you if they can; for your gods are as numerous as your cities, O Judah.
29 ULB ስለዚህ እኔ እንዳጠፋሁ አድርጋችሁ የምትከስሱኝ ለምንድር ነው? ሁላችሁ በእኔ ላይ ኃጢአት ሠርታችሁብኛል ይላል እግዚአብሔር። BSB BSB: Why do you bring a case against Me? You have all rebelled against Me,” declares the LORD.
30 ULB ሕዝባችሁን በከንቱ ቀጥቼአቸዋለሁ፤ ተግሣጽን አልተቀበሉም፤ እንደሚሰብር አንበሳ ሰይፋችሁ ነቢያቶቻችሁን በልቶአል! BSB BSB: “I have struck your sons in vain; they accepted no discipline. Your own sword has devoured your prophets like a voracious lion.”
31 ULB ከዚህ ትውልድ የሆናችሁ እናንተ! የእግዚአብሔር ቃል ለሆነው ለቃሌ ትኩረት ስጡ! በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ፣ ወይስ የጥልቅ ጨለማ ምድር ሆንሁባትን? ሕዝቤስ ስለ ምን 'እኛ እንቅበዝበዝ፣ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንተ አንመለስም' ይላል? BSB BSB: You people of this generation, consider the word of the LORD: “Have I been a wilderness to Israel or a land of dense darkness? Why do My people say, ‘We are free to roam; we will come to You no more’?
32 ULB ደናግሏ ጌጥዋን፣ ወይስ ሙሽራ ዝርግፍ ጌጥዋን ትረሳለችን? ሕዝቤ ግን ለማይቈጠሩ ቀናት ረስቶኛል። BSB BSB: Does a maiden forget her jewelry or a bride her wedding sash? Yet My people have forgotten Me for days without number.
33 ULB ፍቅርን ለመሻት መንገድሽን እንዴት በደህና ታቀኛለሽ። እንደውም መንገድሽን ለክፉዎች ሴቶች እንኳ አስተምረሻል። BSB BSB: How skillfully you pursue love! Even the most immoral of women could learn from your ways.
34 ULB የንፁሐን ሕይወት የሆነው ደም፣ የድሆችም ደም በልብሶችሽ ላይ ተገኝቷል። እነዚህ ሰዎች በስርቆሽ ተግባር የተያዙ አልነበሩም። BSB BSB: Moreover, your skirts are stained with the blood of the innocent poor, though you did not find them breaking in. But in spite of all these things
35 ULB ይልቊን፣ ይህ ሁሉ ሆኖ ሳለ፣ 'ወቀሳ የለብኝም፤ በእውነት የእግዚአብሔር ቊጣ ከእኔ ተመልሶአል' አልሽ። ነገር ግን ተመልከቺ! 'ኃጢአት አልሠራሁም' ብለሻልና ይፈረድብሻል። BSB BSB: you say, ‘I am innocent. Surely His anger will turn from me.’ Behold, I will judge you, because you say, ‘I have not sinned.’
36 ULB መንገድሽን ትለዋውጪ ዘንድ ነገሩን ለምን ታቀልያለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ ያሳፍርሻል። BSB BSB: How impulsive you are, constantly changing your ways! You will be disappointed by Egypt just as you were by Assyria.
37 ULB እግዚአብሔር የታመንሽባቸውን ጥሎአልና፥ በእነርሱም አይከናወንልሽምና እጅሽን በራስሽ ላይ አድርገሽ ከዚያ ደግሞ ትወጫለሽ። BSB BSB: Moreover, you will leave that place with your hands on your head, for the LORD has rejected those you trust; you will not prosper by their help.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.