1 ULB ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው፣ እንዲህም አለ፣ BSB BSB: This is the word that came to Jeremiah from the LORD:
2 ULB "የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'የነገርኩህን ቃል ሁሉ በጥቅልል ላይ ጻፈው። BSB BSB: “This is what the LORD, the God of Israel, says: ‘Write in a book all the words that I have spoken to you.
3 ULB ተመልከት፣ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስባት ዘመን ይመጣልና፣ ይላል እግዚአብሔር። ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፣ እነርሱም ይገዙአታል። BSB BSB: For behold, the days are coming, declares the LORD, when I will restore from captivity My people Israel and Judah, declares the LORD. I will restore them to the land that I gave to their fathers, and they will possess it.’”
4 ULB እግዚአብሔር ስለ እስራኤልና ስለ ይሁዳ የተናገረው ቃል ይህ ነው፣ BSB BSB: These are the words that the LORD spoke concerning Israel and Judah.
5 ULB "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'የሚያስፈራ ድምፅ ሰምተናል፤ የፍርሃት ነው እንጂ የሰላም አይደለም። BSB BSB: Yes, this is what the LORD says: “A cry of panic is heard—a cry of terror, not of peace.
6 ULB ጠይቁ፣ ወንድ ይወልድ እንደ ሆነ ተመልከቱ። እያንዳንዱ ወጣት ሰው እጁን በወገቡ ላይ ያደረገው ለምንድነው? እንደ ወላድ ሴት፣ ፊታቸው ሁሉ ወደ ጥቁረት የተለወጠው ለምንድነው? BSB BSB: Ask now, and see: Can a male give birth? Why then do I see every man with his hands on his stomach like a woman in labor and every face turned pale?
7 ULB ወዮ! ያ ቀን ታላቅ ይሆናልና፣ እርሱንም የሚመስል የለምና። ያ የያዕቆብ የመከራ ዘመን ነው፣ ነገር ግን ከእርሱ ይድናል። BSB BSB: How awful that day will be! None will be like it! It is the time of Jacob’s distress, but he will be saved out of it.
8 ULB በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ቀንበርን ከአንገትህ እሰብራለሁ፣ እስራትህንም እበጥሳለሁ፣ ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ ለሌላ አትገዛም። BSB BSB: On that day, declares the LORD of Hosts, I will break the yoke off their necks and tear off their bonds, and no longer will strangers enslave them.
9 ULB ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር፣ በእነርሱ ላይ ንጉሥ ለማደርግላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ያገለግላሉ። BSB BSB: Instead, they will serve the LORD their God and David their king, whom I will raise up for them.
10 ULB ስለዚህ፣ ባሪያዬ ያዕቆብ ሆይ፣ አትፍራ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተም እስራኤል ሆይ፣ አትደንግጥ። ተመልከቱ፣ አንተን ከሩቅ፣ ዘርህንም ከምርኮ አገር አድናለሁና። ያዕቆብም ይመለሳል ሰላምም ይሆናል፤ ደህንነቱም ይጠበቃል፣ ከዚያም በኋላ ማንም አያስፈራውም። BSB BSB: As for you, O Jacob My servant, do not be afraid, declares the LORD, and do not be dismayed, O Israel. For I will surely save you out of a distant place, your descendants from the land of their captivity! Jacob will return to quiet and ease, with no one to make him afraid.
11 ULB አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና፣ ይላል እግዚአብሔር። አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብ ፍጹም ማብቂያቸው እንዲመጣ አደርጋለሁ። አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፣ በፍትህ እቀጣሃለሁ፣ ያለ ቅጣትም ከቶ አልተውህም።' BSB BSB: For I am with you to save you, declares the LORD. Though I will completely destroy all the nations to which I have scattered you, I will not completely destroy you. Yet I will discipline you justly, and will by no means leave you unpunished.”
12 ULB እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'ስብራትህ የማይፈወስ፣ ቍስልህም ያመረቀዘ ነው። BSB BSB: For this is what the LORD says: “Your injury is incurable; your wound is grievous.
13 ULB ጉዳይህን የሚሟገትልህ የለም፣ ቍስልህንም የሚፈውስ መድኃኒት የለህም። BSB BSB: There is no one to plead your cause, no remedy for your sores, no recovery for you.
14 ULB አፍቃሪዎችሽ ሁሉ ረስተውሻል። አይፈልጉሽምም፣ በደልሽ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትሽም ስለ በዛ፣ በጠላት ማቍሰልና በጨካኝ አሠሪ ቅጣት አቍስዬሻለሁና። BSB BSB: All your lovers have forgotten you; they no longer seek you, for I have struck you as an enemy would, with the discipline of someone cruel, because of your great iniquity and your numerous sins.
15 ULB ሕመምሽ የማይፈወስ ሆኖአልና ስለ ስብራትሽ ለምን ትጮያለሽ? በደልሽ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትሽም ስለ በዛ፣ ይህን አድርጌብሻለሁ። BSB BSB: Why do you cry out over your wound? Your pain has no cure! Because of your great iniquity and your numerous sins I have done these things to you.
16 ULB ስለዚህ የሚበሉሽ ሁሉ ይበላሉ፣ ጠላቶችሽም ሁሉ ወደ ምርኮ ይወሰዳሉ። የዘረፉሽም ይዘረፋሉ፣ የበዘበዙሽንም ሁሉ ለመበዝበዝ አሳልፌ እሰጣለሁ። BSB BSB: Nevertheless, all who devour you will be devoured, and all your adversaries—every one of them—will go off into exile. Those who plundered you will be plundered, and all who raided you will be raided.
17 ULB እኔ ጤናሽን እመልስልሻለሁ ቍስልሽንም እፈውሳለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ይህንንም የማደርገው፦ ማንም የማይሻት፤ የተጣለች ጽዮን" ብለው ጠርተውሻልና። BSB BSB: But I will restore your health and heal your wounds, declares the LORD, because they call you an outcast, Zion, for whom no one cares.”
18 ULB እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቺ፣ የያዕቆብን ድንኳን ምርኮ እመልሳለሁ፣ ለቤቱም እራራለሁ። ከተማይቱም በፍርስራሽ ጉብታዋ ላይ ትሠራለች፣ ምሽጉም እንደ ዱሮው ይሆናል። BSB BSB: This is what the LORD says: “I will restore the fortunes of Jacob’s tents and have compassion on his dwellings. And the city will be rebuilt on her own ruins, and the palace will stand in its rightful place.
19 ULB ከዚያም ከእርሱ ዘንድ የምስጋናና የዘፋኞች ድምፅ ይወጣል፣ እኔም አበዛቸዋለሁ አላሳንሳቸውም፤ እንዳይዋረዱ እኔ አከብራቸዋለሁ። BSB BSB: Thanksgiving will proceed from them, a sound of celebration. I will multiply them, and they will not be decreased; I will honor them, and they will not be belittled.
20 ULB ከዚያም ሕዝቦቻቸው እንደ ቀድሞ ይሆናሉ፣ ማኅበራቸውም በፊቴ ጸንቶ ይኖራል፤ የሚያስጨንቋቸውንም ሁሉ እቀጣለሁ። BSB BSB: Their children will be as in days of old, and their congregation will be established before Me; and I will punish all their oppressors.
21 ULB መሪያቸው ከእነርሱ ውስጥ ይወጣል። እኔ ሳቀርበውና እርሱም ሲቀርበኝ ከመካከላቸው ይወጣል። ይህንን ባላደርግ፣ ወደ እኔ ለመቅረብ የሚደፍር ማን ነው? ይላል እግዚአብሔር። BSB BSB: Their leader will be one of their own, and their ruler will arise from their midst. And I will bring him near, and he will approach Me, for who would dare on his own to approach Me?” declares the LORD.
22 ULB እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፣ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ። BSB BSB: “And you will be My people, and I will be your God.”
23 ULB ተመልከቱ፣ የእግዚአብሔር ዐውሎ ነፋስ፣ ቍጣው ወጥቷል። ሳይቋረጥ የሚያገለባብጥ ዐውሎ ነፋስ ወጥቶአል። የክፉዎችንም ራስ ይገለባብጣል። BSB BSB: Behold, the storm of the LORD has gone out with fury, a whirlwind swirling down upon the heads of the wicked.
24 ULB የእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የልቡን አሳብ ሠርቶ እስኪፈጽም ድረስ አይመለስም። በመጨረሻው ዘመን ታስተውሉታላችሁ።" BSB BSB: The fierce anger of the LORD will not turn back until He has fully accomplished the purposes of His heart. In the days to come you will understand this.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.