1 ULB ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣ ቃል ይህ ነው። ይህ ቃል የመጣው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርና ሠራዊቱ ሁሉ፣ ከእጁም ግዛት በታች ያሉ የምድር መንግሥታት ሁሉ አሕዛብም ሁሉ ኢየሩሳሌምንና ከተሞችዋን ሁሉ ይወጉ በነበረ ጊዜ ነበር። BSB BSB: This is the word that came to Jeremiah from the LORD when Nebuchadnezzar king of Babylon, all his army, all the earthly kingdoms under his control, and all the other nations were fighting against Jerusalem and all its surrounding cities.
2 ULB 'የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሂድ ለይሁዳም ንጉሥ ለሴዴቅያስ ተናገር እንዲህም በለው፣ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተመልከት፣ ይህችን ከተማ በባቢሎን ንጉሥ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። በእሳትም ያቃጥላታል። BSB BSB: The LORD, the God of Israel, told Jeremiah to go and speak to Zedekiah king of Judah and tell him that this is what the LORD says: “Behold, I am about to deliver this city into the hand of the king of Babylon, and he will burn it down.
3 ULB አንተም በእርግጥ ትያዛለህ፣ በእጁም ተላልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም። ዐይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዐይን ታያለች፤ ወደ ባቢሎን ስትሄድ፣ እርሱ ከአንተ ጋር አፍ ለአፍ ይነጋገራል።' BSB BSB: And you yourself will not escape his grasp, but will surely be captured and delivered into his hand. You will see the king of Babylon eye to eye and speak with him face to face; and you will go to Babylon.
4 ULB የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ! ስለ አንተ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'በሰይፍ አትሞትም። BSB BSB: Yet hear the word of the LORD, O Zedekiah king of Judah. This is what the LORD says concerning you: You will not die by the sword;
5 ULB በሰላም ትሞታለህ። እንደ አባቶችህ የቀብር መቃጠል፣ ከአንተ በፊት እንደነበሩት ነገሥታት፣ እንዲሁ አካልህን ያቃጥላሉና። "ወየው፣ ጌታ ሆይ!" እያሉ ያለቅሱልሃል። አሁን እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና፣ ይላል እግዚአብሔር።" BSB BSB: you will die in peace. As spices were burned for your fathers, the former kings who preceded you, so people will burn spices for you and lament, ‘Alas, O master!’ For I Myself have spoken this word, declares the LORD.”
6 ULB ነቢዩ ኤርምያስ እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ነገረው። BSB BSB: In Jerusalem, then, Jeremiah the prophet relayed all these words to Zedekiah king of Judah
8 ULB ንጉሡ ሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ከነበሩ ሕዝብ ሁሉ ጋር ነፃነትን ለማወጅ ስምምነት ካደረገ በኋላ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው። BSB BSB: After King Zedekiah had made a covenant with all the people in Jerusalem to proclaim liberty, the word came to Jeremiah from the LORD
9 ULB እያንዳንዱ ሰው እስራኤላዊ የሆነውን ወንድ ባርያውንና ሴት ባርያውን ነፃነት ሊለቅ ይገባል። ማንም ሰው ከእንግዲህ ወዲህ በይሁዳ ውስጥ መሰል እስራኤላዊን ባርያ ሊያደርግ አይገባም። BSB BSB: that each man should free his Hebrew slaves, both male and female, and no one should hold his fellow Jew in bondage.
10 ULB ስለዚህም ስምምነቱን የተቀላቀሉት መሪዎች ሁሉ እና ሕዝቡ ታዘዙ። እያንዳንዱ ሰው ወንድ እና ሴት ባርያዎቻቸውን ከእንግዲህ ወዲህ ባርያ ላያደርጓቸው ነፃ አደረጓቸው። እነርሱም ሰሙ፣ ሰደዷቸውም። BSB BSB: So all the officials and all the people who entered into this covenant agreed that they would free their menservants and maidservants and no longer hold them in bondage. They obeyed and released them,
11 ULB ነገር ግን ከዚህ በኋላ አሳባቸውን ቀየሩ። ነፃነት የለቀቋቸውን ባርያዎቻቸውን መልሰው አመጡ። በድጋሚ ባርያዎች እንዲሆኑ አስገደዷቸው። BSB BSB: but later they changed their minds and took back the menservants and maidservants they had freed, and they forced them to become slaves again.
12 ULB ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፣ BSB BSB: Then the word of the LORD came to Jeremiah from the LORD, saying,
13 ULB "የእስራኤል አምላክ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'አባቶቻችሁን ከባርነት ቤት ከግብጽ አገር ባወጣኋቸው ቀን ከእነርሱ ጋር እንዲህ ብዬ ቃል ኪዳን አደረግሁ። BSB BSB: “This is what the LORD, the God of Israel, says: I made a covenant with your forefathers when I brought them out of the land of Egypt, out of the house of slavery, saying:
14 ULB "ሰባት ዓመት በተፈጸመ ጊዜ፣ ራሱን የሸጠላችሁን፣ ስድስትም ዓመት የተገዛላችሁን ዕብራዊ ወንድማችሁን እያንዳንዳችሁ ነፃነት ልታወጡት ይገባል። ነፃ አድርጋችሁ ስደዱት።" ነገር ግን አባቶቻችሁ አልሰሙኝም ጆሮአቸውንም አላዘነበሉም። BSB BSB: Every seventh year, each of you must free his Hebrew brother who has sold himself to you. He may serve you six years, but then you must let him go free. But your fathers did not listen or incline their ear.
15 ULB እናንተም ዛሬ ተመልሳችሁ ሰው ሁሉ ባልንጀራውን አርነት ለማውጣት ዐዋጅ በመንገር ለዐይኔ ትክክል የሆነውን ነገር አድርጋችሁ ነበር። በስሜም በሚጠራበት ቤት ውስጥ በፊቴ ቃል ኪዳን አድርጋችሁ ነበር። BSB BSB: Recently you repented and did what pleased Me; each of you proclaimed freedom for his neighbor. You made a covenant before Me in the house that bears My Name.
16 ULB ነገር ግን ያን ጊዜ ተመልሳችሁ ስሜን አስነቀፋችሁ፤ እያንዳንዳችሁም በፈቃዳቸው እንዲሄዱ ነፃነት ያወጣችኋቸውን ወንድና ሴት ባርያዎቻችሁን አስመለሳችሁ። በድጋሚ ወንዶችና ሴቶች ባርያዎች እንዲሆኑላችሁ አስገደዳችኋቸው።' BSB BSB: But now you have changed your minds and profaned My name. Each of you has taken back the menservants and maidservants whom you had set at liberty to go wherever they wanted, and you have again forced them to be your slaves.
17 ULB ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ 'እናንተ ራሳችሁ አልሰማችሁኝም። እያንዳንዳችሁ፣ ለወንድሞቻችሁና ለመሰል እስራኤላውያን ነፃነትን ልታውጁ በተገባ ነበር። ስለዚህ ተመልከቱ! እኔ ለሰይፍ፣ ለመቅሰፍት፣ ለራብም የነፃነት ዐዋጅ እናገርባችኋለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ መካከል አስደንጋጭ ነገር አደርጋችኋለሁ። BSB BSB: Therefore this is what the LORD says: You have not obeyed Me; you have not proclaimed freedom, each man for his brother and for his neighbor. So now I proclaim freedom for you, declares the LORD—freedom to fall by sword, by plague, and by famine! I will make you a horror to all the kingdoms of the earth.
18 ULB ከዚያም ቃል ኪዳኔን የተላለፉትን ሰዎች፣ እንቦሳውንም ቈርጠው በቍራጩ መካከል ባለፉ ጊዜ በፊቴ ያደረጉትን የቃል ኪዳንን ቃል ያልፈጸሙትን እቀጣለሁ፤ BSB BSB: And those who have transgressed My covenant and have not fulfilled the terms of the covenant they made before Me, I will treat like the calf they cut in two in order to pass between its pieces.
19 ULB ከዚያም የይሁዳንና የኢየሩሳሌምን አለቆች ጃንደረቦችን ካህናትንም፣ በእንቦሳም ቍራጭ መካከል ያለፉትን የአገሩን ሕዝብ ሁሉ። BSB BSB: The officials of Judah and Jerusalem, the court officials, the priests, and all the people of the land who passed between the pieces of the calf,
20 ULB ለጠላቶቻቸው እጅ፣ ሕይወታቸውንም ለሚሹአት ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል። BSB BSB: I will deliver into the hands of their enemies who seek their lives. Their corpses will become food for the birds of the air and the beasts of the earth.
21 ULB የይሁዳንም ንጉሥ ሴዴቅያስንና አለቆቹን ለጠላቶቻቸው እጅ፣ ሕይወታቸውንም ለሚሹአት እጅ፣ ከእናንተም ለተመለሱት ለባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ። BSB BSB: And I will deliver Zedekiah king of Judah and his officials into the hands of their enemies who seek their lives, to the army of the king of Babylon that had withdrawn from you.
22 ULB ተመልከቱ፣ ትእዛዝ እሰጣለሁ፣ ይላል እግዚአብሔር፤ ጦርነትን እንዲከፍቱባትና እንዲወስዷት፣ እንዲያቃጥሏትም ወደዚህች ከተማ እመልሳቸዋለሁ። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።" BSB BSB: Behold, I am going to give the command, declares the LORD, and I will bring them back to this city. They will fight against it, capture it, and burn it down. And I will make the cities of Judah a desolation, without inhabitant.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.