1 ULB ተወግተው ስለ ሞቱ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን አለቅስ ዘንድ ራሴ ውኃ፣ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ! BSB BSB: Oh, that my head were a spring of water, and my eyes a fountain of tears! I would weep day and night over the slain daughter of my people.
2 ULB ሁሉም አመንዝሮች፣ የከዳተኞች ጉባኤ በመሆናቸው ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ የመንገደኞች ማደሪያን ማን በሰጠኝ! BSB BSB: If only I had a traveler’s lodge in the wilderness, I would abandon my people and depart from them, for they are all adulterers, a crowd of faithless people.
3 ULB "አታላይ ቀስታቸው በሆነው በምላሳቸው ሐሰት ተናገሩ፣ ነገር ግን በምድር ላይ በታማኝነት ግሩም አይደሉም። ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉ። እኔንም አላወቁምና፣" ይላል እግዚአብሔር። BSB BSB: “They bend their tongues like bows; lies prevail over truth in the land. For they proceed from evil to evil, and they do not take Me into account,” declares the LORD.
4 ULB እያንዳንዱ ወንድም ሁሉ ያታልላልና፣ እያንዳንዱ ጎረቤትም ሁሉ ሐሜተኛ ስለሆነ እናንተ ሁሉ ከጎረቤቶቻችሁ ተጠንቀቁ፣ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ። BSB BSB: “Let everyone guard against his neighbor; do not trust any brother, for every brother deals craftily, and every friend spreads slander.
5 ULB እያንዳንዱ ሰውም ሁሉ ጎረቤቱን ያታልላል በእውነትም አይናገርም። ምላሶቻቸው የማታለል ነገሮችን ያስተምራል። በደልንም በማድረግ ይደክማሉ። BSB BSB: Each one betrays his friend; no one tells the truth. They have taught their tongues to lie; they wear themselves out committing iniquity.
6 ULB በማታለል መካከል ትኖራላችሁ፣ ከሽንገላም የተነሣ እኔን ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፣ ይላል እግዚአብሔር። BSB BSB: You dwell in the midst of deception; in their deceit they refuse to know Me,” declares the LORD.
7 ULB ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ተመልከቱ፣ እፈትናቸዋለሁ። እመረምራቸዋለሁ። ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድር ነው? BSB BSB: Therefore this is what the LORD of Hosts says: “Behold, I will refine them and test them, for what else can I do because of the daughter of My people?
8 ULB ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ያልታመኑ ነገሮችን ይናገራሉ። ከጎረቤቶቻቸው ጋር በአንደበታቸው በሰላም ይናገራሉ፣ በልባቸው ግን ያደቡበታል። BSB BSB: Their tongues are deadly arrows; they speak deception. With his mouth a man speaks peace to his neighbor, but in his heart he sets a trap for him.
9 ULB በውኑ ስለዚህ ነገር አልቀጣቸውምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንደዚህስ ባለ ሕዝብ ላይ አልበቀልምን? BSB BSB: Should I not punish them for these things? declares the LORD. Should I not avenge Myself on such a nation as this?”
10 ULB ለተራሮች የልቅሶና የዋይታን ዝማሬ እዘምራለሁ፣ ለምድረ በዳ ማሰማርያዎችም የቀብር ዋይታን እዘምራለሁ። ማንም ሰው እንዳያልፍባቸው በእሳት ተቃጥለዋልና። ሰዎችም የየትኛውንም ከብት ድምፅ አይሰሙም። የሰማይ ወፎች ጀምሮ እስከ እንስሳ ድረስ ሁሉ ሸሽተው ሄደዋል። BSB BSB: I will take up a weeping and wailing for the mountains, a dirge over the wilderness pasture, for they have been scorched so no one passes through, and the lowing of cattle is not heard. Both the birds of the air and the beasts have fled; they have gone away.
11 ULB ኢየሩሳሌምን የፍርስራሽ ክምር፣ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ። የይሁዳንም ከተሞች ሰው የማይኖርባት ወና አደርጋቸዋለሁ። BSB BSB: “And I will make Jerusalem a heap of rubble, a haunt for jackals; and I will make the cities of Judah a desolation, without inhabitant.”
12 ULB ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው? ለሌሎች እንዲነግር የእግዚአብሔር አፍ ምን ተናገረው? ምድሪቱስ ስለምን ጠፋች? ማንም እንደማያልፍባት እንደ ምድረ በዳስ ስለ ምን ተደመሰሰች? BSB BSB: Who is the man wise enough to understand this? To whom has the mouth of the LORD spoken, that he may explain it? Why is the land destroyed and scorched like a desert, so no one can pass through it?
13 ULB እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፣ "በፊታቸው የሰጠኋቸውን ሕጌን ስለተዉ፣ ድምጼንም አልሰሙምና ወይም አልተጓዙበትምና። BSB BSB: And the LORD answered, “It is because they have forsaken My law, which I set before them; they have not walked in it or obeyed My voice.
14 ULB አባቶቻቸው እንዳስተማሯቸው በልባቸውን ምኞት ተመላልሰዋልና፣ በኣሊምን ተከትለዋልና። BSB BSB: Instead, they have followed the stubbornness of their hearts and gone after the Baals, as their fathers taught them.”
15 ULB ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል 'ተመልከቱ፣ ይህን ሕዝብ እሬትን አበላዋለሁ የተመረዘንም ውኃ አጠጣዋለሁ። BSB BSB: Therefore this is what the LORD of Hosts, the God of Israel, says: “Behold, I will feed this people wormwood and give them poisoned water to drink.
16 ULB እነርሱና አባቶቻቸውም ባላወቁአቸው አሕዛብ መካከል እበትናቸዋለሁ፣ እስካጠፋቸውም ድረስ በበስተኋላቸው ሰይፍን እሰድድባቸዋለሁ።" BSB BSB: I will scatter them among the nations that neither they nor their fathers have known, and I will send a sword after them until I have finished them off.”
17 ULB የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ይህንን አስቡ፦ የቀብር አስለቃሾችን ጥሩ፤ ይምጡ። ወደ ብልሃተኛ አልቃሾች ላኩ። BSB BSB: This is what the LORD of Hosts says: “Take note, and summon the wailing women; send for the most skillful among them.
18 ULB ይፍጠኑና ዓይኖቻችንም እንባ እንዲያፈስሱ የዓይናችንም ሽፋሽፍቶች ውኃን እንዲያፈልቁ የለቅሶ ዝማሬን ይዘምሩልን። BSB BSB: Let them come quickly and take up a lament over us, that our eyes may overflow with tears, and our eyelids may gush with water.
19 ULB 'እንዴት ተበዘበዝን። ቤቶቻችን ስለፈረሱ ምድሪቱንም ትተናልና እንዴት አፈርን!' የሚል የልቅሶ ድምፅ በጽዮን ተሰምቶአል። BSB BSB: For the sound of wailing is heard from Zion: ‘How devastated we are! How great is our shame! For we have abandoned the land because our dwellings have been torn down.’”
20 ULB ስለዚህ እናንተ ሴቶች ሆይ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፣ ከአፉ ለሚወጣው ቃል ትኩረት ስጡ። ከዚያም ለሴቶች ልጆቻችሁም የልቅሶውን ዝማሬ አስተምሩ፣ ለእያንዳንዷም የጎረቤታችሁ ሴት የቀብሩን ሙሾ አስተምሩ። BSB BSB: Now, O women, hear the word of the LORD. Open your ears to the word of His mouth. Teach your daughters to wail, and one another to lament.
21 ULB ሞት ወደ መስኮታችን መጥቷልና፤ ወደ ቤተ መንግሥቶቻችን ሄዷል። ሕፃናቱን ከውጪ፣ ወጣቶቹንም ከከተማይቱ አደባባይ ያጠፋል። BSB BSB: For death has climbed in through our windows; it has entered our fortresses to cut off the children from the streets, the young men from the town squares.
22 ULB 'የሰውም ሬሳ በሜዳ ላይ እንደ ጕድፍ፣ ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል፣ ማንምም አይሰበስበውም። BSB BSB: Declare that this is what the LORD says: “The corpses of men will fall like dung upon the open field, like newly cut grain behind the reaper, with no one to gather it.”
23 ULB እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "ጠቢብ በጥበቡ እንዲመካ አትፍቀዱ፣ ወይም ጦረኛ በኃይሉ አይመካ። ባለ ጠጋም በብልጥግናው እንዲመካ አትፍቀዱ። BSB BSB: This is what the LORD says: “Let not the wise man boast in his wisdom, nor the strong man in his strength, nor the wealthy man in his riches.
24 ULB ሰው በየትኛውም ነገር የሚመካ ከሆነ፣ በዚህ ይሁን፣ ማስተዋል ያለውና የሚያውቀኝ በመሆኑ። የኪዳን ታማኝነት፣ ፍትሕንና ጽድቅንም በምድር ላይ የማደርግ እኔ እግዚአብሔር ነኝና። ደስ የሚያሰኙኝ እነዚህ ናቸውና፣ ይላል እግዚአብሔር። BSB BSB: But let him who boasts boast in this, that he understands and knows Me, that I am the LORD, who exercises loving devotion, justice and righteousness on the earth—for I delight in these things,” declares the LORD.
25 ULB ተመልከቱ፣ በሰውነታቸው ብቻ የተገረዙትን እቀጣለሁ። BSB BSB: “Behold, the days are coming,” declares the LORD, “when I will punish all who are circumcised only in the flesh—
26 ULB ግብጽንና ይሁዳን፣ የአሞን ሕዝቦች የሆኑትን ኤዶምያስና ሞዓብንም፣ እንዲሁም በምድረ በዳም የተቀመጡትን ፀጉራቸውን የተላጩትን ሁሉ፣ ባለመገረዛቸው ምክንያት የምቀጣበት ዘመን እነሆ ይመጣል። እነዚህ ሁሉ ሕዝቦች ያልተገረዙ ናቸውና፣ ደግሞም የእስራኤል ልብ አልተገረዘምና" ይላል እግዚአብሔር። BSB BSB: Egypt, Judah, Edom, Ammon, Moab, and all the inhabitants of the desert who clip the hair of their temples. For all these nations are uncircumcised, and the whole house of Israel is uncircumcised in heart.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.