1 ULB በመቀጠልም ኢዮብ መለሰ እንዲህም አለ፦ BSB BSB: Then Job answered:
2 ULB በእርግጥ እናንተ አዋቂ ሰዎች ናቸሁ፤ ጥበብ ከእናንተ ጋር ትሞታለች። BSB BSB: “Truly then you are the people with whom wisdom itself will die!
3 ULB ነገር ግን እኔ እንደ እናንተው ማስተዋል አለኝ፤ ከእናንተም የማንስ አይደለሁም፤ በእርግጥ እንደ እነዚህ ያሉትን ነገሮች የማያውቅ ማን ነው? BSB BSB: But I also have a mind; I am not inferior to you. Who does not know such things as these?
4 ULB እግዚአብሔርን ሲጠራ የሚመልስለት ሰው የነበርሁ እኔ አሁን ለጎረቤቶቼ መሳለቅያ ሆኛለሁ፤ ጻድቅና ነቀፋ የሌለበት የነበርሁ እኔ አሁን ማሾፊያ ሆኛለሁ። BSB BSB: I am a laughingstock to my friends, though I called on God, and He answered. The righteous and upright man is a laughingstock.
5 ULB በደላው ሰው ሃሳብ ውስጥ መከራ የተናቀ ነው፤ እግሩ ለሚሸራተት ሰው ችግሩን ሊጨምርበት ያስባል። BSB BSB: The one at ease scorns misfortune as the fate of those whose feet are slipping.
6 ULB የዘራፊዎች ድንኳን ይበለጥጋል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ በደህና ተቀምጠዋል፤ የገዛ እጃቸውን አምላካቸው አድርገዋል። BSB BSB: The tents of robbers are safe, and those who provoke God are secure—those who carry their god in their hands.
7 ULB አሁን ግን እንስሶችን ጠይቁ፥ ያስተምሯችኋል፤ የሰማይንም ወፎች ጠይቁ፥ ይነግሯችኋል። BSB BSB: But ask the animals, and they will instruct you; ask the birds of the air, and they will tell you.
8 ULB ወይም ለምድር ተናገሩ፥ እርስዋም ታስተምራችኋለች፤ የባሕርም ዓሣዎች በግልጥ ይነግሯችኋል። BSB BSB: Or speak to the earth, and it will teach you; let the fish of the sea inform you.
9 ULB ከእነዚህ ሁሉ እንስሳት የእግዚአብሔር እጅ ይህን እንዳደረገ፤ የሕያዋን ሁሉ ህይወት፤ BSB BSB: Which of all these does not know that the hand of the LORD has done this?
10 ULB የሰው ልጆችንም ሁሉ እስትንፋስ በእጁ እንደያዘ የማያውቅ ማን ነው?። BSB BSB: The life of every living thing is in His hand, as well as the breath of all mankind.
11 ULB ምላስ የምግብን ጣዕም እንደሚቀምስ፥ ጆሮ ቃላትን አይለይምን? BSB BSB: Does not the ear test words as the tongue tastes its food?
12 ULB እድሜ በገፉት ዘንድ ጥበብ፥ በዘመን ርዝማኔም ማስተዋል ይገኛል። BSB BSB: Wisdom is found with the elderly, and understanding comes with long life.
13 ULB በእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ኃይል አለ ምክርና ማስተዋልም በእርሱ ዘንድ ይገኛሉ። BSB BSB: Wisdom and strength belong to God; counsel and understanding are His.
14 ULB እነሆ፥ እርሱ ያፈርሳል፥ ተመልሶም አይሠራም፤ አንድን ሰው ቢያስር ሊፈታው የሚችል የለም። BSB BSB: What He tears down cannot be rebuilt; the man He imprisons cannot be released.
15 ULB እነሆ፥ ውኆቹን ቢከለክል፥ እነርሱ ይደርቃሉ፤ እንደ ገናም ቢለቃቸው፥ ምድርን ያጥለቀልቃሉ። BSB BSB: If He holds back the waters, they dry up, and if He releases them, they overwhelm the land.
16 ULB ብርታትና ጥበብ በእርሱ ዘንድ ናቸው፤ የሚስተውና የሚያስተው በእርሱ ስልጣን ስር ናቸው። BSB BSB: True wisdom and power belong to Him. The deceived and the deceiver are His.
17 ULB መካሪዎችንም ባዶአቸውን በሃዘን ይሰዳቸዋል፥ ፈራጆችንም አላዋቂ ያደርጋቸዋል። BSB BSB: He leads counselors away barefoot and makes fools of judges.
18 ULB የነገሥታትንም የስልጣን ሰንሰለት ይፈታል፥ ወገባቸውንም በመታጠቂያ ልብስ ያስርላቸዋል። BSB BSB: He loosens the bonds placed by kings and fastens a belt around their waists.
19 ULB ይሽራል ባዶአቸውንምይሰዳቸዋል፥ ኃያላንንም ይገለብጣቸዋል። BSB BSB: He leads priests away barefoot and overthrows the established.
20 ULB የታመኑ ሰዎችንም ንግግረ ያስወግዳል፥ የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስድባቸዋል። BSB BSB: He deprives the trusted of speech and takes away the discernment of elders.
21 ULB በአለቆች ላይ ንቀትን ያፈሳል፥ የብርቱ ሰዎችንም ቀበቶ ይፈታል። BSB BSB: He pours out contempt on nobles and disarms the mighty.
22 ULB ከጨለማ ውስጥ ጥልቅ ነገሮችን ይገልጣል፥ ከሙታንም ሰፈር የመታየትን ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል። BSB BSB: He reveals the deep things of darkness and brings deep shadows into light.
23 ULB ህዝቦችን ብርቱ ያደርጋል፥ ደግሞም ያጠፋቸዋል፤ ህዝቦችንም ያበዛል፥ ደግሞም ወደ ግዞት ይልካቸዋል። BSB BSB: He makes nations great and destroys them; He enlarges nations, then disperses them.
24 ULB ከምድር ሕዝብ አለቆች ማስተዋልን ይወስዳል፥ መንገድም በሌለበት ምድረበዳ ያቅበዘብዛቸዋል። BSB BSB: He deprives the earth’s leaders of reason and makes them wander in a trackless wasteland.
25 ULB ብርሃን በሌለበት በጨለማ ይዳክራሉ፤ እንደ ሰካራምም ይንገዳገዳሉ። BSB BSB: They grope in the darkness without light; He makes them stagger like drunkards.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.