1 ULB ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ BSB BSB: Then the LORD said to Moses,
2 ULB “አሮንንና ልጆቹን፣ የክህነት ልብሶቹን፣ የቅባት ዘይቱን፣የኃጢአት መስዋዕቱን ወይፈኖች፣ ሁለቱን ጠቦቶች፣ እርሾ የሌለበትን ህብስት መሶብ ከእርሱ ጋር ውሰድ፡፡ BSB BSB: “Take Aaron and his sons, their garments, the anointing oil, the bull of the sin offering, the two rams, and the basket of unleavened bread,
3 ULB በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ሁሉንም ጉባኤ ሰብስብ፡፡” BSB BSB: and assemble the whole congregation at the entrance to the Tent of Meeting.”
4 ULB ስለዚህም ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው አደረገ፣ ጉባኤውም በመገናኛው ድንኳን መግቢያ ላይ ተሰበሰበ፡፡ BSB BSB: So Moses did as the LORD had commanded him, and the assembly gathered at the entrance to the Tent of Meeting.
5 ULB ከዚያም ሙሴ ለጉባኤው እንዲህ አለ፣ “ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ይህ ነው፡፡” BSB BSB: And Moses said to them, “This is what the LORD has commanded to be done.”
6 ULB ሙሴ አሮንንና ልጆቹን አቀረበና በውሃ አጠባቸው፡፡ BSB BSB: Then Moses presented Aaron and his sons and washed them with water.
7 ULB አሮንን እጀ ጠባብ አለበሰውና በወገቡ ዙሪያ መቀነት አስታጠቀው፣ ቀሚ አጠለቀለትና ኤፉድ ደረበለት፣ ከዚያም ኤፉዱን በጥበብ በተጠለፈ መቀነት አስታጠቀው፡፡ BSB BSB: He put the tunic on Aaron, tied the sash around him, clothed him with the robe, and put the ephod on him. He tied the woven band of the ephod around him and fastened it to him.
8 ULB በቀሚሱ ላይ ደረት ኪስ አደረገለት፣ በደረት ኪሱ ውስጥ ኡሪምና ቱሚም አደረገበት፡፡ BSB BSB: Then he put the breastpiece on him and placed the Urim and Thummim in the breastpiece.
9 ULB ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው በራሱ ላይ ጥምጥሙን ጠመጠመለት፣ በጥምጥሙ ላይ ከፊት በኩል ወርቃማ ቅብና ቅዱስ አክሊል አደረገለት፡፡ BSB BSB: Moses also put the turban on Aaron’s head and set the gold plate, the holy diadem, on the front of the turban, as the LORD had commanded him.
10 ULB ሙሴ የቅባቱን ዘይት ወሰደ፣ ማደሪያ ድንኳኑንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቀባው፤ እናም ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡ BSB BSB: Next, Moses took the anointing oil and anointed the tabernacle and everything in it; and so he consecrated them.
11 ULB በመሰዊያው ላይ ዘይቱን ሰባት ጊዜ ረጨው፣ እናም መሰዊያውንና መገልገያዎቹን ሁሉ ቀባቸው፣ እንዲሁም የመታጠቢያ ሳህኑንና ማስቀመጫውን፣ ለያህዌ ቀደሳቸው፡፡ BSB BSB: He sprinkled some of the oil on the altar seven times, anointing the altar and all its utensils, and the basin with its stand, to consecrate them.
12 ULB አሮንን ያህዌ ለመለየት ከቅባቱ ዘይት ጥቂቱን በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰው፡፡ BSB BSB: He also poured some of the anointing oil on Aaron’s head and anointed him to consecrate him.
13 ULB ሙሴ ያህዌ እንዳዘዘው የአሮንን ወንድ ልጆች አቅርቦ እጀጠባብ አለበሳቸው፣ በወገባቸው ዙሪያ መታጠቂያ አሰረላቸው፣ በራሳቸው ላይ በፍታ ጨርቅ ጠቀለለላቸው፡፡ BSB BSB: Then Moses presented Aaron’s sons, put tunics on them, wrapped sashes around them, and tied headbands on them, just as the LORD had commanded him.
14 ULB ሙሴ ለኃጢአት መስዋዕት በሬ አመጣ፣ አሮንና ልጆቹ ለኃጢአት መስዋዕት ባመጡት በሬ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ፡፡ BSB BSB: Moses then brought the bull near for the sin offering, and Aaron and his sons laid their hands on its head.
15 ULB በሬውን አርዶ ደሙን በመሰዊያው ቀንዶች ውስጥ በጣቱ ጨመረ፣ በመሰዊያው ስር ደሙን አፈሰሰ፣ ለማስተስረይ ለእግዚአብሔር ለየው፡፡ BSB BSB: Moses slaughtered the bull, took some of the blood, and applied it with his finger to all four horns of the altar, purifying the altar. He poured out the rest of the blood at the base of the altar and consecrated it so that atonement could be made on it.
16 ULB በመስዋዕቱ ሆድ ዕቃ ውስጥ ያለውን ስብ ሁሉ አወጣ፣ በጉበቱ መሸፈኛና በሁለቱ ኩላሊቶች ላይ ያለውን ስብ ወስዶ በመሰዊያው ላይ ሁሉንም አቃጠለው፤ BSB BSB: Moses also took all the fat that was on the entrails, the lobe of the liver, and both kidneys and their fat, and burned it all on the altar.
17 ULB ነገር ግን በሬውን፣ ቆዳውን፣ ስጋውን እና ፈርሱን ያህዌ እንዳዘዘው ከሰፈር አውጥቶ አቃጠለው፡፡ BSB BSB: But the bull with its hide, flesh, and dung he burned outside the camp, as the LORD had commanded him.
18 ULB ሙሴ ለሚቃጠል መስዋዕት ጠቦቱን አቀረበ፣ አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፡፡ BSB BSB: Then Moses presented the ram for the burnt offering, and Aaron and his sons laid their hands on its head.
19 ULB ሙሴም ጠቦቱን አርዶ በመሰዊያው ዙሪያ ደሙን ረጨ፡፡ BSB BSB: Moses slaughtered the ram and splattered the blood on all sides of the altar.
20 ULB ጠቦቱን ቆራርጦ ራሱንና ቁርጥራጩን እንዲሁም ስቡን አቃጠለ፡፡ BSB BSB: He cut the ram into pieces and burned the head, the pieces, and the fat.
21 ULB የሆድ ዕቃውን ክፍሎችና እግሮቹን በውሃ አጠበ፣ ከዚያም ጠቦቱን በሙሉ በመሰዊያው ላይ አቃጠለ፡፡ ያህዌ ሙሴን እንዳዘዘው ይህ የሚቃጠል መስዋዕት ነው፤ ደግሞም ለያህዌ በእሳት የተዘጋጀ ጣፋጭ መዓዛ ነው፡፡ BSB BSB: He washed the entrails and legs with water and burned the entire ram on the altar as a burnt offering, a pleasing aroma, a food offering to the LORD, just as the LORD had commanded Moses.
22 ULB ከዚያም ሙሴ ሌላውን ጠቦት ያቀርባል፣ ይህም የክህነት ሹመት መስዋዕት ነው፣ እናም አሮንና ልጆቹ በጠቦቱ ራስ ላይ እጃቸውን ይጭናሉ፡፡ BSB BSB: After that, Moses presented the other ram, the ram of ordination, and Aaron and his sons laid their hands on its head.
23 ULB አሮን ጠቦቱን ያርዳል፣ ሙሴም ከደሙ ጥቂት ወስዶ በአሮን ቀኝ ጆሮ ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጁ አውራ ጣት እና በቀኝ እግሩ አውራ ጣት ላይ ያደርጋል፡፡ BSB BSB: Moses slaughtered the ram and took some of its blood and put it on Aaron’s right earlobe, on the thumb of his right hand, and on the big toe of his right foot.
24 ULB የአሮንን ልጆች አቅርቦ፣ በቀኝ ጆሯቸው ጫፍ ላይ፣ በቀኝ እጃቸው አውራ ጣት ላይ እና በቀኛ እግራቸው አውራ ጣት ላይ ከደሙ ጥቂት ወስዶ ያደርጋል፡፡ ከዚያ ሙሴ የበጉን ደም በመሰዊያው ጎኖች ሁሉ ይረጫል፡፡ BSB BSB: Moses also presented Aaron’s sons and put some of the blood on their right earlobes, on the thumbs of their right hands, and on the big toes of their right feet. Then he splattered the blood on all sides of the altar.
25 ULB ስቡን፣ ላቱን፣ በሆድ ዕቃ ክፍሎች ውስጥ ሁሉ የሚገኘውን ስብ፣ የጉበቱን መሸፈኛ፣ ሁለቱን ኩላሊቶች እና በላያቸው የሚገነውን ስብ እንዲሁም ቀኝ ወርቹን ወሰደ፡፡ BSB BSB: And Moses took the fat—the fat tail, all the fat that was on the entrails, the lobe of the liver, and both kidneys with their fat—as well as the right thigh.
26 ULB በያህዌ ፊት ከነበረው መሶብ እርሾ የሌለበት አንድ ህብስት ይወስዳል፣ደግሞም በዘይት ተለውሶ ከተሰራው ዳቦ አንዱን እና አንድ ስስ ቂጣ ይውሰድና በስቡና በቀኝ ወርች ላይ ያኖረዋል፡፡ BSB BSB: And from the basket of unleavened bread that was before the LORD, he took one cake of unleavened bread, one cake of bread made with oil, and one wafer, and he placed them on the fat portions and on the right thigh.
27 ULB ሁሉንም በአሮን እጆችና በአሮን ወንድ ልጆች እጆች ላይ ያስቀምጠዋል፣ ይህንንም ለሚወዘወዝ መስዋዕት በያህዌ ት ያቀርባሉ፡፡ BSB BSB: He put all these in the hands of Aaron and his sons and waved them before the LORD as a wave offering.
28 ULB ከዚያም ሙሴ ከእጃቸው ይወስድና የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቀርበው፡፡ እነዚህ የክህነት ሹመት መስዋዕት ናቸው፤ ጣፋጭ መዓዛ ሆነው ይቀርባሉ፡፡ ይህ በእሳት ለያህዌ የሚቀርብ መስዋዕት ነው፡፡ BSB BSB: Then Moses took these from their hands and burned them on the altar with the burnt offering. This was an ordination offering, a pleasing aroma, a food offering to the LORD.
29 ULB ሙሴ ፍርምባውን ወስዶ ለያህዌ መስዋዕት አድርጎ ይወዝውዘው፡፡ ያህዌ እንዳዘዘው ይህ ከጠቦቱ የክህነት ሹመት የሙሴ ድርሻ ነው፡፡ BSB BSB: He also took the breast—Moses’ portion of the ram of ordination—and waved it before the LORD as a wave offering, as the LORD had commanded him.
30 ULB ሙሴ በመሰዊያው ላይ ካለው ከቅባት ዘይቱና ከደሙ ጥቂት ወስዶ እነዚህን በአሮን ላይ፣ በልብሶ ላይ፣ በወንድ ልጆቹ ላይ እና ከእርሱ ጋር በልጆቹ ልብሶች ላይ ይረጫል፡፡ በዚህ መንገድ አሮንና የክህነት ልብሱን እንዲሁም ልጆቹንና ልብሳቸውን ለያህዌ ይቀድሳል፡፡ BSB BSB: Next, Moses took some of the anointing oil and some of the blood that was on the altar and sprinkled them on Aaron and his garments, and on his sons and their garments. So he consecrated Aaron and his garments, as well as Aaron’s sons and their garments.
31 ULB ደግሞም ሙሴ ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ አለ፣ “በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ስጋውን ቀቅሉት፣ በዚያም ስፍራ በሹመት መስጫው መሶብ ውስጥ ያለውን ህብስትም ‘አሮንና ልጆቹ ይብሉት’ ብዬ እንዳዘዝኩት ብሉት፡፡ BSB BSB: And Moses said to Aaron and his sons, “Boil the meat at the entrance to the Tent of Meeting and eat it there with the bread that is in the basket of ordination offerings, as I commanded, saying, ‘Aaron and his sons are to eat it.’
32 ULB ከስጋውና ከህብስቱ የተረፈውን በሙሉ አቃጥሉት፡፡ BSB BSB: Then you must burn up the remainder of the meat and bread.
33 ULB የሹመት ስርዓቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ለሰባት ቀናት ከመገናኛው ከመገናኛው ድንኳን መግቢያ አትለፉ፡፡ ያህዌ በሰባት ቀናት ውስጥ ይሾማችኋል፡፡ BSB BSB: You must not go outside the entrance to the Tent of Meeting for seven days, until the days of your ordination are complete; for it will take seven days to ordain you.
34 ULB በዚህ ቀን የሚሆነው እናንተን ለማስተረይ ያህዌ እንዲደረግ ያዘዘው ነው፡፡ BSB BSB: What has been done today has been commanded by the LORD in order to make atonement on your behalf.
35 ULB ለሰባት ቀናት ቀንም ሆነ ሌሊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ ትቆያላችሁ፣ ደግሞም የያህዌን ትዕዛዝ ትጠብቃላችሁ፣ ይህን ካደረጋችሁ አትሞቱም፣ ምክንያቱም የታዘዝኩት ይህንን ነው፡፡” BSB BSB: You must remain at the entrance to the Tent of Meeting day and night for seven days and keep the LORD’s charge so that you will not die, for this is what I have been commanded.”
36 ULB ስለዚህም አሮንና ልጆቹ ያህዌ በሙሴ በኩል እንዲያደርጉት ያዘዛቸውን ሁሉንም ነገር አደረጉ፡፡ BSB BSB: So Aaron and his sons did everything the LORD had commanded through Moses.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.