1 ULB ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤ "ወደ ኅጢአት የሚያመሩ ነገሮች መምጣታቸው የማይቀር ነው። ነገር ግን ለኅጢአት ምክንያት ለሚሆነው ሰው ወዮለት። BSB BSB: Jesus said to His disciples, “It is inevitable that stumbling blocks will come, but woe to the one through whom they come!
2 ULB በእምነት ደካማ ከሆኑት ከእነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን ከማስናከል ይልቅ ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ባሕር ቢጣል ይሻለዋል። BSB BSB: It would be better for him to have a millstone hung around his neck and to be thrown into the sea than to cause one of these little ones to stumble.
3 ULB ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። ወንድምህ ቢበድልህ ገሥጸው፤ ተመልሶ ከተጸጸተ ይቅር በለው፤ በቀንም ሰባት ጊዜ እንኳ ቢበድልህና ሰባት ጊዜ ተመላልሶ፤ BSB BSB: Watch yourselves. If your brother sins, rebuke him; and if he repents, forgive him.
4 ULB 'ስለ ሠራሁት ኅጢአት ተጸጸትሁ' እያለ ወደ አንተ ቢመለስ ይቅር ልትለው ይገባል።" BSB BSB: Even if he sins against you seven times in a day, and seven times returns to say, ‘I repent,’ you must forgive him.”
5 ULB ሐዋርያት ጌታን፣ "እምነት ጨምርልን" አሉት። BSB BSB: The apostles said to the Lord, “Increase our faith!”
6 ULB ጌታም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ "የሰናፍጭን ዘር ያህል እምነት ቢኖራችሁ፤ ይህን የሾላ ዛፍ፣ 'ከመሬት ተነቅለህ ወደ ባሕር ተተከል' ብትሉት ይታዘዝላችኋል። BSB BSB: And the Lord answered, “If you have faith the size of a mustard seed, you can say to this mulberry tree, ‘Be uprooted and planted in the sea,’ and it will obey you.
7 ULB "በዕርሻ ወይም በበጎች እረኝነት የተሰማራ አገልጋይ ካላችሁ፣ አገልጋዩ ከሥራ ደክሞ ሲመለስ፣ ወዲያውኑ "ና ተቀመጥና እራትህን ብላ የሚለው ከእናንተ ማን ነው?" BSB BSB: Which of you whose servant comes in from plowing or shepherding in the field will say to him, ‘Come at once and sit down to eat’?
8 ULB "እራቴን አዘጋጅልኝ፤ እስክበላና እስክጠጣም ወገብህን ታጥቀህ ቆመህ አስተናግደኝ፤ ከዚያ በኋላ አንተ ደግሞ ትበላለህ ትጠጣለህም አይለውምን?" BSB BSB: Instead, won’t he tell him, ‘Prepare my meal and dress yourself to serve me while I eat and drink, and afterward you may eat and drink’?
9 ULB ታዲያ አገልጋዩ የታዘዘውን ስለ ፈጸመ ጌታው ያመሰግነዋልን? BSB BSB: Does he thank the servant because he did what he was told?
10 ULB እንዲሁም እናንተም የታዘዛችሁትን ሁሉ ከፈጸማችሁ በኋላ የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ 'የፈጸምነውም የታዘዝንውን ግዳጃችንን ብቻ ነው' ማለት አለባችሁ።" BSB BSB: So you also, when you have done everything commanded of you, should say, ‘We are unworthy servants; we have only done our duty.’”
11 ULB ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሩሳሌም ሲሄዱ ሳለ፣ ሰማርያንና ገሊላን በሚያዋስነው መንገድ ያልፉ ነበር። BSB BSB: While Jesus was on His way to Jerusalem, He was passing between Samaria and Galilee.
12 ULB ኢየሱስም ወደ አንዲት መንደር በገባ ጊዜ ዐሥር ለምጻሞች አገኙት። እነርሱም ከእርሱ ርቀው ቆሙና BSB BSB: As He entered one of the villages, He was met by ten lepers. They stood at a distance
13 ULB ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ "ኢየሱስ ሆይ፣ መምህር ሆይ፣ እባክህ ማረን" እያሉ ጮኹ። BSB BSB: and raised their voices, shouting, “Jesus, Master, have mercy on us!”
14 ULB ኢየሱስ ባያቸው ጊዜ፣ "ሂዱና ራሳችሁን ለካህናት አሳዩ" አላቸው። እነርሱም እየሄዱ ሳሉ፣ ከለምጻቸው ነጹ። BSB BSB: When Jesus saw them, He said, “Go, show yourselves to the priests.” And as they were on their way, they were cleansed.
15 ULB ከእነርሱ አንዱ ከለምጹ መፈወሱን ባየ ጊዜ፣ ጮክ ብሎ እግዚአብሔርን እያከበረ ተመለሰ። BSB BSB: When one of them saw that he was healed, he came back, praising God in a loud voice.
16 ULB በኢየሱስ እግር ሥር በግንባሩ ተደፍቶ አመሰገነው። እርሱም የሰማርያ ሰው ነበር። BSB BSB: He fell facedown at Jesus’ feet in thanksgiving to Him—and he was a Samaritan.
17 ULB ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ፣ "ዐሥሩም ለምጻሞች ተፈውሰው አልነበረምን? ታዲያ ዘጠኙ የት አሉ? BSB BSB: “Were not all ten cleansed?” Jesus asked. “Where then are the other nine?
18 ULB ከዚህ ከባዕድ ሰው በቀር እግዚአብርሔን ለማመስገን ተመልሶ የመጣ ሌላ የለምን?" BSB BSB: Was no one found except this foreigner to return and give glory to God?”
19 ULB ኢየሱስ ሰውየውን፣ "ተነሥና ሂድ እምነትህ አድኖሃል" አለው። BSB BSB: Then Jesus said to him, “Rise and go; your faith has made you well!”
20 ULB ፈሪሳውያን ኢየሱስን፣ "የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች?" ብለው ለጠየቁት ጥያቄ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፤ "የእግዚአብሔር መንግሥት የምትታይ አይደለችም።" ወይም'እነሆ፣ እዚህ ናት' BSB BSB: When asked by the Pharisees when the kingdom of God would come, Jesus replied, “The kingdom of God will not come with observable signs.
21 ULB ወይም 'እነሆ፣እዚያ ናት' የምትባል አይደለችም። ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ናት።" BSB BSB: Nor will people say, ‘Look, here it is,’ or ‘There it is.’ For you see, the kingdom of God is in your midst.”
22 ULB ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፤" ከሰው ልጅ ቀኖች አንዱን ለማየት የምትናፍቁበት ቀን ይመጣል። ነገር ግን አታዩትም። BSB BSB: Then He said to the disciples, “The time is coming when you will long to see one of the days of the Son of Man, but you will not see it.
23 ULB ሰዎች፣ 'እነሆ፣ ክርስቶስ እዚህ ነው! ወይም እዚያ ነው!' ይሉአችኋል። ነገር ግን እነርሱን ሰምታችሁ አትፈልጉ፤ አትከተሉአቸውም። BSB BSB: People will tell you, ‘Look, there He is!’ or ‘Look, here He is!’ Do not go out or chase after them.
24 ULB መብረቅ በሰማይ ላይ ሲበርቅ ከዳር እስከ ዳር እንደሚያበራ፣ የሰው ልጅም በሚመጣበት ቀን እንዲሁ ይሆናል። BSB BSB: For just as the lightning flashes and lights up the sky from one end to the other, so will be the Son of Man in His day.
25 ULB ነገር ግን ይህ ከመሆኑ በፊት የሰው ልጅ ብዙ መከራ ሊቀበል ይገባል። በዚህ ዘመን ሰዎችም ሊናቅና ሊነቀፍ ግድ ነው። BSB BSB: But first He must suffer many things and be rejected by this generation.
26 ULB በኖኅ ዘመን እንደሆነው፣ በሰው ልጅ ዘመንም እንዲሁ ይሆናል። BSB BSB: Just as it was in the days of Noah, so also will it be in the days of the Son of Man:
27 ULB ኖኅ ወደ መርከብ እስከገባበት ቀን ድረስ ሰዎች ሲበሉና ሲጠጡ፣ ሲያገቡና ሲጋቡና ነበር። ነገር ግን በዚያን ጊዜ የጥፋት ውሃ መጥቶ ሁሉንም አጠፋቸው። BSB BSB: People were eating and drinking, marrying and being given in marriage, up to the day Noah entered the ark. Then the flood came and destroyed them all.
28 ULB እንደዚሁም በሎጥ ዘመን ሰዎች ይበሉ፣ ይጠጡ፣ ይሸጡ ይገዙ፣ አትክልት ይተክሉና ቤትም ይሠሩ እንደ ነበረ ይሆናል። BSB BSB: It was the same in the days of Lot: People were eating and drinking, buying and selling, planting and building.
29 ULB ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ቀን ግን እሳትና ዲን ከሰማይ ዘንቦ ሁሉንም አጠፋ። BSB BSB: But on the day Lot left Sodom, fire and sulfur rained down from heaven and destroyed them all.
30 ULB የሰው ልጅ በሚገለጥበት ቀንም እንዲሁ ይሆናል። BSB BSB: It will be just like that on the day the Son of Man is revealed.
31 ULB በዚያ ቀን በቤቱ ጣሪያ ላይ ያለ ሰው በቤቱ ውስጥ ያለውን ዕቃ ለመውሰድ አይውረድ። በዕርሻም ቦታ ያለ ሰው ወደ ቤቱ አይመለስ። BSB BSB: On that day, let no one on the housetop come down to retrieve his possessions. Likewise, let no one in the field return for anything he has left behind.
32 ULB የሎጥን ሚስት አስታውሱአት። ሕይወቱን ሊያድን በራሱ መንገድ ለመሄድ የሚፈልግ ሁሉ ያጣታል። BSB BSB: Remember Lot’s wife!
33 ULB ነገር ግን ሕይወቱን ለጌታ አሳልፎ የሚሰጥ ሁሉ ያድናታል። BSB BSB: Whoever tries to save his life will lose it, but whoever loses his life will preserve it.
34 ULB ይህን እላችሏለሁ፣ "በዚያች ሌሊት ሁለት ሰዎች በአንድ ዐልጋ ላይ ይተኛሉ። BSB BSB: I tell you, on that night two people will be in one bed: one will be taken and the other left.
35 ULB ከእነርሱም አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል። እንዲሁም ሁለት ሴቶች በአንድ ቦታ አብረው ይፈጫሉ፤ BSB BSB: Two women will be grinding grain together: one will be taken and the other left.”
36 ULB አንድዋ ትወሰዳለች ሌላዋ ትቀራለች። ሁለት ሰዎች በአንድ ዕርሻ ቦታ ያርሳሉ፤አንዱ ይወሰዳል፤ ሌላው ይቀራል።" BSB BSB: Not in the BSB
37 ULB ደቀ መዛሙርቱም ኢየሱስን፦ 'ጌታ ሆይ፤ ወዴት?' ብለው ጠየቁት። እርሱም፦ "በድን ባለበት አሞራዎች ይሰበባሉ።" ሲል መለሰላቸው። BSB BSB: “Where, Lord?” they asked. Jesus answered, “Wherever there is a carcass, there the vultures will gather.”