2 ULB ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን ጎህ በቀደደ ጊዜ ወደ መቃብሩ መጡ፡፡ BSB BSB: Very early on the first day of the week, just after sunrise, they went to the tomb.
3 ULB እርስ በርሳቸውም ድንጋዩን ከመቃብሩ መግቢያ ማን ያንከባልልናል ይባባሉ ነበር፡፡ BSB BSB: They were asking one another, “Who will roll away the stone from the entrance of the tomb?”
4 ULB አሻግረው ሲመለከቱም ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና ተንከባሎ አዩት፡፡ BSB BSB: But when they looked up, they saw that the stone had been rolled away, even though it was extremely large.
5 ULB ወደ መቃብሩም ገብተው የሚያንጸባርቅ ነጭ ልብስ የለበሰ አንድ ወጣት በስተቀኝ ተቀምጦ አዩና ተገረሙ፡፡ BSB BSB: When they entered the tomb, they saw a young man dressed in a white robe sitting on the right side, and they were alarmed.
6 ULB እርሱም አትገረሙ፣ የምትፈልጉት ተሰቅሎ የነበረውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ነው፡፡ ያኖሩበትን ቦታ ተመልከቱ፤ እርሱ በዚህ የለም፣ ተነሥቷል፡፡ BSB BSB: But he said to them, “Do not be alarmed. You are looking for Jesus the Nazarene, who was crucified. He has risen! He is not here! See the place where they put Him.
7 ULB ነገር ግን ሂዱ፣ ለጴጥሮስና ለደቀመዛሙርቱም እንደነገራችሁ ወደ ገሊላ ይቀድማችኋል፣ በዚያም ታዩታላችሁ ብላችሁ ንገሯቸው አላቸው፡፡ BSB BSB: But go, tell His disciples and Peter, ‘He is going ahead of you into Galilee. There you will see Him, just as He told you.’”
8 ULB እነርሱም መገረምና ፍርሃት ወድቆባቸው ነበርና ከዚያ ወጥተው ከመቃብሩ ሸሹ፡፡ ፈርተውም ነበርና ለማንም አንዳች አልተናገሩም፡፡ BSB BSB: So the women left the tomb and ran away, trembling and bewildered. And in their fear they did not say a word to anyone.
10 ULB እርሷም ከኢየሱስ ጋር የነበሩት እያዘኑና እያለቀሱ ሳሉ ሄዳ ነገረቻቸው፡፡ BSB BSB: She went and told those who had been with Him, who were mourning and weeping.
11 ULB እነርሱም ሕያው እንደሆነና ለእርሷም እንደታያት በሰሙ ጊዜ አላመኑም፡፡ BSB BSB: And when they heard that Jesus was alive and she had seen Him, they did not believe it.
12 ULB ከእነዚህ ነገሮች በኋላም ከእነርሱ ሁለቱ ወደ ገጠር በመሄድ ላይ ሳሉ ኢየሱስ በሌላ ሰው መልክ ተገለጠላቸው፡፡ BSB BSB: After this, Jesus appeared in a different form to two of them as they walked along in the country.
13 ULB እነርሱም ሄደው ለተቀሩት ነገሯቸው፤ እነርሱንም አላመኗቸውም፡፡ BSB BSB: And they went back and reported it to the rest, but they did not believe them either.
14 ULB ከዚያም በማዕድ ተቀምጠው ሳሉ ለአሥራ አንዱ ለራሳቸው ኢየሱስ ተገለጠላቸውና ስለ ልባቸው ጥንካሬና ከትንሳኤው በኋላ ያዩትን ስላላመኗቸው ወቀሳቸው፡፡ BSB BSB: Later, as they were eating, Jesus appeared to the Eleven and rebuked them for their unbelief and hardness of heart, because they did not believe those who had seen Him after He had risen.
15 ULB እንዲህም አላቸው፣ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ወንጌልንም ለፍጥረት በሙሉ ስበኩ አላቸው፡፡ BSB BSB: And He said to them, “Go into all the world and preach the gospel to every creature.
16 ULB ያመነና የተጠመቀም ይድናል፣ ያላመነ ግን ይፈረድበታል፡፡ BSB BSB: Whoever believes and is baptized will be saved, but whoever does not believe will be condemned.
17 ULB ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሏቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፣ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፣ BSB BSB: And these signs will accompany those who believe: In My name they will drive out demons; they will speak in new tongues;
18 ULB እባቦችን ይይዛሉ፣ የሚገድል ነገር እንኳን ቢጠጡ አይጎዳቸውም፣ እጆቻቸውን በህሙማን ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይፈወሳሉ፡፡ BSB BSB: they will pick up snakes with their hands, and if they drink any deadly poison, it will not harm them; they will lay their hands on the sick, and they will be made well.”
19 ULB ጌታ ኢየሱስ ይህንን ካላቸው በኋላ ወደ ሰማይ ወጥቶም በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀመጠ፡፡ BSB BSB: After the Lord Jesus had spoken to them, He was taken up into heaven and sat down at the right hand of God.
20 ULB እነርሱም ወጥተው በየቦታው ሰበኩ፡፡ ጌታም ቃሉን ተከትለው በሚመጡ ምልክቶች እያጸና ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፡፡ አሜን፡፡ BSB BSB: And they went out and preached everywhere, and the Lord worked through them, confirming His word by the signs that accompanied it.