1 ULB ኢየሱስ ወደ ጀልባ ገባ፤ ባሕሩንም አቋርጦ ወደ ገዛ ከተማው መጣ። BSB BSB: Jesus got into a boat, crossed over, and came to His own town.
2 ULB እነሆ፣ በምንጣፍ የተኛ አንድ ሽባ ሰው ወደ እርሱ አመጡ። ኢየሱስም እምነታቸውን በማየት ሽባውን፣ “አንተ ልጅ፣ አይዞህ፤ ኅጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል” አለው፡፡ BSB BSB: Just then some men brought to Him a paralytic lying on a mat. When Jesus saw their faith, He said to the paralytic, “Take courage, son; your sins are forgiven.”
3 ULB አንዳንድ ጸሐፍት ግን እርስ በርሳቸው፣ "ይህ ሰው እኮ እየተሳደበ ነው" ተባባሉ። BSB BSB: On seeing this, some of the scribes said to themselves, “This man is blaspheming!”
4 ULB ኢየሱስም ዐሳባቸውን ዐውቆ፣ “ስለ ምን በልባችሁ ክፉ ታስባላችሁ?” BSB BSB: But Jesus knew what they were thinking and said, “Why do you harbor evil in your hearts?
5 ULB ለመሆኑ የሚቀለው፣'ኃጢአትህ ይቅር ተብሎልሃል' ነው፣ ወይስ 'ተነሣና ሂድ ማለት ነው?' BSB BSB: Which is easier: to say, ‘Your sins are forgiven,’ or to say, ‘Get up and walk’?
6 ULB ነገር ግን የሰው ልጅ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር የማለት ሥልጣን እንዳለው ዕወቁ" አለ፡፡ ሽባውንም፣ "ተነሣና፣ምንጣፍህን ይዘህ ወደ ቤት ሂድ" አለው፡፡ BSB BSB: But so that you may know that the Son of Man has authority on earth to forgive sins...” Then He said to the paralytic, “Get up, pick up your mat, and go home.”
7 ULB ከዚያም ሰውየው ተነሥቶ ወደ ቤቱ ሄደ። BSB BSB: And the man got up and went home.
8 ULB ሕዝቡም ይህን ባዩ ጊዜ ተገርመው፣ ለሰው እንዲህ ያለ ሥልጣን የሰጠውን እግዚአብሔርን አመሰገኑ። BSB BSB: When the crowds saw this, they were filled with awe and glorified God, who had given such authority to men.
9 ULB ኢየሱስም ከዚያ አለፍ እንዳለ፣ ማቴዎስ የሚባለውን ሰው በቀረጥ መሰብሰቢያ ቦታ ላይ ተቀምጦ አየውና "ተከተለኝ" አለው።እርሱም ተነሥቶ ተከተለው፡፡ BSB BSB: As Jesus went on from there, He saw a man named Matthew sitting at the tax booth. “Follow Me,” He told him, and Matthew got up and followed Him.
10 ULB ኢየሱስም በቤቱ ውስጥ ለመመገብ በተቀመጠ ጊዜ፣ ቀረጥ የሚሰበስቡ ብዙ ሰዎችና ኃጢአተኞች መጥተው፣ ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርት ጋር አብረው ተመገቡ። BSB BSB: Later, as Jesus was dining at Matthew’s house, many tax collectors and sinners came and ate with Him and His disciples.
11 ULB ፈሪሳውያንም ይህን ሲያዩ፣ደቀ መዛሙርቱን "ለምንድን ነው መምህራችሁ፣ ከግብር ሰብሳቢዎችና ከኃጢአተኞች ጋር የሚበላው?" አሏቸው፡፡ BSB BSB: When the Pharisees saw this, they asked His disciples, “Why does your Teacher eat with tax collectors and sinners?”
12 ULB ኢየሱስም ይህንን ሲሰማ ፣"ሕመምተኞች እንጂ ጤነኞች ሐኪም አያስፈልጋቸውም፡፡ BSB BSB: On hearing this, Jesus said, “It is not the healthy who need a doctor, but the sick.
13 ULB 'ሂዱና' ምሕረት እንጂ መሥዋዕትን አልፈልግም' የሚለውን ተማሩ፣ እኔ የመጣሁት ጻድቃንን ሳይሆን ኅጥአንን ወደ ንስሓ ለመጥራት" ነው አለ። BSB BSB: But go and learn what this means: ‘I desire mercy, not sacrifice.’ For I have not come to call the righteous, but sinners.”
14 ULB ከዚያም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት መጥተው፣" እኛና ፈሪሳውያን ብዙ ጊዜ እንጾማለን ፣የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ለምንድን ነው?" አሉት። BSB BSB: Then John’s disciples came to Jesus and asked, “Why is it that we and the Pharisees fast so often, but Your disciples do not fast?”
15 ULB ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “ሰርገኞች ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ እንዴት ሊያዝኑ ይችላሉ? ሆኖም ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፣በእነዚያ ቀናት ይጾማሉ። BSB BSB: Jesus replied, “How can the guests of the bridegroom mourn while He is with them? But the time will come when the bridegroom will be taken from them; then they will fast.
16 ULB ማንም ሰው በአሮጌ ልብስ ላይ ዐዲስ ቊራጭ ጨርቅ አይለጥፍም፤ ምክንያቱም አሮጌውን ልብስ ይቦጭቀዋል፣ ልብሱም የባሰ ይጐዳል። BSB BSB: No one sews a patch of unshrunk cloth on an old garment. For the patch will pull away from the garment, and a worse tear will result.
17 ULB ሰዎች ዐዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቁማዳ ውስጥ አያስቀምጡም፤ እንደዚያ ካደረጉ አቁማዳው ይፈነዳል፣ የወይን ጠጁ ይፈሳል፣ አቁማዳውም ይቀደዳል። ይልቁንም ዐዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ውስጥ ያስቀምጡታል፣ ሁለቱም ይጠበቃሉ፡፡" BSB BSB: Neither do men pour new wine into old wineskins. If they do, the skins will burst, the wine will spill, and the wineskins will be ruined. Instead, they pour new wine into new wineskins, and both are preserved.”
18 ULB ኢየሱስ ይህን እየተናገራቸው እያለ፣ አንድ ሹም እየሰገደ ወደ እርሱ መጣ። “ልጄ አሁን ገና ሞተች፣ ነገር ግን ና ና እጅህን ጫንባት በሕይወትም ትኖራለች አለው”። BSB BSB: While Jesus was saying these things, a synagogue leader came and knelt before Him. “My daughter has just died,” he said. “But come and place Your hand on her, and she will live.”
19 ULB ኢየሱስም ተነሥቶ ተከትሎት ሄደ፤ ደቀ ዛሙርቱም ደግሞ አብረውት ሄዱ። BSB BSB: So Jesus got up and went with him, along with His disciples.
20 ULB አንዲት ለዐሥራ ሁለት ዓመት ከባድ የደም መፍሰስ የነበረባት ሴት፣ ከኢየሱስ ኋላ መጥታ የልብሱን ጠርዝ ነካች፤ BSB BSB: Suddenly a woman who had suffered from bleeding for twelve years came up behind Him and touched the fringe of His cloak.
21 ULB "የልብሱን ጫፍ ብቻ ብነካ ደኅና እሆናለሁ" ብላ ነበርና። BSB BSB: She said to herself, “If only I touch His cloak, I will be healed.”
22 ULB ኢየሱስም ዞር ብሎ አያትና፣ “ልጄ ሆይ፣ አይዞሽ እምነትሽ አድኖሻል” አላት። ሴቲቱም ወዲያውኑ ደኅና ሆነች። BSB BSB: Jesus turned and saw her. “Take courage, daughter,” He said, “your faith has healed you.” And the woman was healed from that very hour.
23 ULB ኢየሱስም ወደ ሹሙ ቤት በገባ ጊዜ፣ዋሽንት የሚነፉትንና የሚንጫጩትን አይቶ፣ BSB BSB: When Jesus entered the house of the synagogue leader, He saw the flute players and the noisy crowd.
24 ULB "ወደዚያ ዞር በሉ፣ ልጅቷ ተኝታለች እንጂ አልሞተችም"አላቸው። እነርሱ ግን በማፌዝ ሳቁበት። BSB BSB: “Go away,” He told them. “The girl is not dead, but asleep.” And they laughed at Him.
25 ULB ሕዝቡን ወደ ውጭ ባስወጡ ጊዜ፥ ኢየሱስ ወደ ክፍሉ ገብቶ እጅዋን ያዘ፤ልጅቱም ተነሣች። BSB BSB: After the crowd had been put outside, Jesus went in and took the girl by the hand, and she got up.
26 ULB ወሬውም በዚያ አካባቢ ሁሉ ተዳረሰ። BSB BSB: And the news about this spread throughout that region.
27 ULB ኢየሱስም በዚያ ሲያልፍ፣ ሁለት ዐይነ ስውሮች ተከተሉት፣ ያለ ማቋረጥም፣ "የዳዊት ልጅ ማረን!" እያሉ ይጮኹ ነበር። BSB BSB: As Jesus went on from there, two blind men followed Him, crying out, “Have mercy on us, Son of David!”
28 ULB ኢየሱስም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ፣ ዐይነ ስውሮቹ ወደ እርሱ መጡ። ኢየሱስም፣ "ይህን ለማድረግ እንደምችል ታምናላችሁ?" አላቸው። እነርሱም "አዎን፣ ጌታ ሆይ" አሉት፡፡ BSB BSB: After Jesus had entered the house, the blind men came to Him. “Do you believe that I am able to do this?” He asked. “Yes, Lord,” they answered.
29 ULB ከዚያም ኢየሱስ ዐይኖቻቸውን ዳስሶ፣ "እንደ እምነታችሁ ይሁንላችሁ" አላቸው። BSB BSB: Then He touched their eyes and said, “According to your faith will it be done to you.”
30 ULB ዐይኖቻቸውም ተከፈቱ። ከዚያም ኢየሱስ፣"ይህንን ማንም እንዳያውቅ" ብሎ በጥብቅ አዘዛቸው። BSB BSB: And their eyes were opened. Jesus warned them sternly, “See that no one finds out about this!”
31 ULB ሁለቱ ሰዎች ግን ሄደው ወሬውን በየቦታው አዳረሱት። BSB BSB: But they went out and spread the news about Him throughout the land.
32 ULB ሁለቱ ሰዎች እየሄዱ እያሉ እነሆ፣ በጋኔን የተያዘ ዲዳ ወደ ኢየሱስ አመጡ። BSB BSB: As they were leaving, a demon-possessed man who was mute was brought to Jesus.
33 ULB ጋኔኑም ከወጣ በኋላ ዲዳው ተናገረ። ሕዝቡም ተገርመው፣ "እንዲህ ያለ ከዚህ በፊት በእስራኤል አልታየም" አሉ። BSB BSB: And when the demon had been driven out, the man began to speak. The crowds were amazed and said, “Nothing like this has ever been seen in Israel!”
34 ULB ፈሪሳውያን ግን "አጋንንትን የሚያወጣው በአጋንንት አለቃ ነው" ይሉ ነበር። BSB BSB: But the Pharisees said, “It is by the prince of demons that He drives out demons.”
35 ULB ኢየሱስ ወደ ከተሞችና መንደሮች ሁሉ ሄደ፣ በየምኩኲራቦቻቸውም ማስተማሩን፣ የመንግሥትን ወንጌል መስበኩንና፣ ማንኛውንም ዐይነት በሽታና ደዌ መፈወሱን ቀጠለ። BSB BSB: Jesus went through all the towns and villages, teaching in their synagogues, preaching the gospel of the kingdom, and healing every disease and sickness.
36 ULB ሕዝቡንም ሲያይ፣ ጠባቂ እንደሌላቸው በጎች ተጨንቀውና ግራ ተጋብተው ነበርና ራራላቸው። BSB BSB: When He saw the crowds, He was moved with compassion for them, because they were harassed and helpless, like sheep without a shepherd.
37 ULB ለደቀ መዛሙርቱም፣ "መከሩ ብዙ ነው ሠራተኞች ግን ጥቂት ናቸው። BSB BSB: Then He said to His disciples, “The harvest is plentiful, but the workers are few.
38 ULB ስለዚህ፣ ሠራተኞችን ወደ መከሩ እንዲልክ፣ ወደ መከሩ ጌታ አጥብቃችሁ ጸልዩ" አላቸው። BSB BSB: Ask the Lord of the harvest, therefore, to send out workers into His harvest.”