1 ULB ደም ለሞላባት ከተማ ወዮላት! ሐሰትና የተዘረፈ ንብረት ሞልቶበታል፡፡ BSB BSB: Woe to the city of blood, full of lies, full of plunder, never without prey.
2 ULB አሁን ግን የአላንጋ ድምፅና የመንኰራኩር ኳኳታ ድምፅ፣ የፈጣን ፈረስ ኮቴ፣ የሰረገሎች መንጓጓት ይሰማል፡፡ BSB BSB: The crack of the whip, the rumble of the wheel, galloping horse and bounding chariot!
3 ULB የሚያብረቀርቅ ሰይፍና የሚያንጸባርቅ ጦር የያዙ ፈረሰኞች ጥቃት ያደርሳሉ፤ የሞተው ብዙ ነው፤ ሬሳ በሬሳ ተከምሮአል እጅግ ከመብዛቱ የተነሣ አጥቂዎቹ በሞቱት ሰዎች ሬሳ ይሰናከላሉ፡፡ BSB BSB: Charging horseman, flashing sword, shining spear; heaps of slain, mounds of corpses, dead bodies without end—they stumble over their dead—
4 ULB ይህ ሁሉ የሆነው ገደብ በሌለው የአመንዝራዋ ፍትወት ምክንያት ነው፤ እርሷ በዝሙቷ መንግሥታን፣ በጥንቆላዋም ሕዝቦችን ባሪያ አድርጋለች፡፡ BSB BSB: because of the many harlotries of the harlot, the seductive mistress of sorcery, who betrays nations by her prostitution and clans by her witchcraft.
5 ULB የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል፣ «እኔ በጠላትነት ተነሥቼብሻለሁ ዕርቃንሽን ለሕዝቦች፣ ኅፍረተ ሥጋሽን ለመንግሥታት አሳያለሁ፡፡ BSB BSB: “Behold, I am against you,” declares the LORD of Hosts. “I will lift your skirts over your face. I will show your nakedness to the nations and your shame to the kingdoms.
6 ULB በጣም የሚያስጸይፍ ቆሻሻ እደፋብሻለሁ፤ እንቅሻለሁ፤ ሰው ሁሉ እንዲሳለቅብሽ አደርጋለሁ፡፡ BSB BSB: I will pelt you with filth and treat you with contempt; I will make a spectacle of you.
7 ULB የሚያይሽ ሁሉ ከአንቺ እየሸሸ፣ «ነነዌ ፈራርሳለች፤ ማን ያለቅስላታል? የሚያጽናናትንስ ከወዴት አገኛለሁ?» ይላል፡፡ BSB BSB: Then all who see you will recoil from you and say, ‘Nineveh is devastated; who will grieve for her?’ Where can I find comforters for you?”
8 ULB ነነዌ ሆይ፣ ለመሆኑ አንቺ ዐባይ ወንዝ አጠገብ ከተሠራችውና በውሃ ከተከበበችው፣ ወንዙ መከላከያ፣ ባሕሩ ራሱ ቅጥራ ከሆነለት ከቴብስ ትበልጫለሽን? BSB BSB: Are you better than Thebes, stationed by the Nile with water around her, whose rampart was the sea, whose wall was the water?
9 ULB ኢትዮጵያና ግብፅ ወሰን የለሽ ኃይሏ ነበሩ ፉጥና ሊቢያም ረዳቶቿ ነበሩ፡፡ BSB BSB: Cush and Egypt were her boundless strength; Put and Libya were her allies.
10 ULB ያም ሆኖ፣ ቴብስ ተጋዘች፤ በምርኮም ተወሰደች ሕፃናቷ በየመንገዱ ማእዘን ላይ ተፈጠፈጡ፤ በመኳንንቷ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፤ ታላላቅ ሰዎቿ ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ፡፡ BSB BSB: Yet she became an exile; she went into captivity. Her infants were dashed to pieces at the head of every street. They cast lots for her dignitaries, and all her nobles were bound in chains.
11 ULB አንቺ ደግሞ ትሰክሪያለሽ መደበቅ ትሞክሪያለሽ ከጠላቶችሽ መሸሸጊያም ትፈልጊያለሽ፡፡ BSB BSB: You too will become drunk; you will go into hiding and seek refuge from the enemy.
12 ULB ምሽጐችሽ ሁሉ ቀድሞ እንደ ደረሰ፣ ሲነቀነቅ በላተኛው አፍ ውስጥ እንደሚወድቅ የበለስ ፍሬ ሆነዋል፡፡ BSB BSB: All your fortresses are fig trees with the first ripe figs; when shaken, they fall into the mouth of the eater!
13 ULB ወታደሮችሽ እንደ ሴት ፈሪዎች ሆነዋል የምድርሽ በሮች ወለል ብለው ለጠላቶችሽ ተከፍተዋል፡፡ መዝጊያዎቻቸውን እሳት በልቷቸዋል፡፡ BSB BSB: Look at your troops—they are like your women! The gates of your land are wide open to your enemies; fire consumes their bars.
14 ULB ለከበባው ውሃ ቅጂ፣ ምሽጐችሽን አጠናክሪ፤ ጭቃ ረግጠሸ የሸክላ መሥሪያ አዘጋጂ፤ ጡብም ሥሪ፡፡ BSB BSB: Draw your water for the siege; strengthen your fortresses. Work the clay and tread the mortar; repair the brick kiln!
15 ULB በዚያ እሳት ይበላሻል፤ ሰይፍ ያጠፋሻል፤ አንበጣ ማንኛውንም ነገር እንደሚጠፉ ያጠፋሻል፡፡ ስለዚህ እንደ አንበጣ እርቢ እንደ ኩብኩባም ተባዢ፡፡ BSB BSB: There the fire will devour you; the sword will cut you down and consume you like a young locust. Make yourself many like the young locust; make yourself many like the swarming locust!
16 ULB ነጋዴዎችሽን ከሰማይ ከዋክብት ይበልጥ አብዝተሻል፤ ይሁን እንጂ፣ ምድሪቱን እንደ አንበጣ ጋጡ፤ ከዚያም በርረው ሄዱ፡፡ BSB BSB: You have multiplied your merchants more than the stars of the sky. The young locust strips the land and flies away.
17 ULB መኳንንቶችሽ የአንበጦችን ያህል ብዙ ናቸው፣ የጦር መሪዎችሽ በብርድ ቀን ቅጥር ሥር እንደሚቀመጥ የኩብኩባ መንጋ ናቸው፡፡ ፀሐይ ሲወጣ ግን በርረው ይሄዳሉ፤ የት እንደሚሄዱም አይታወቅም፡፡ BSB BSB: Your guards are like the swarming locust, and your scribes like clouds of locusts that settle on the walls on a cold day. When the sun rises, they fly away, and no one knows where.
18 ULB የአሦር ንጉሥ ሆይ፣ እረኞችህ አንቀላፉ መኳንንትህ ዐርፈው ተኙ፡፡ ሕዝብህ ሰብሳቢ አጥተው በየተራሮች ተበትነዋል፡፡ BSB BSB: O king of Assyria, your shepherds slumber; your officers sleep. Your people are scattered on the mountains with no one to gather them.
19 ULB ቁስልህን መፈወስ የሚችል የለም፤ ቁስልህ እጅግ ጽኑ ነው፡፡ ስለ አንተ የሚሰማ ሁሉ በውድቀትህ ደስ ብሎት ያጨበጭባል፡፡ ወሰን ከሌለው ጭካኔህ ማን ያመለጠ አለ? BSB BSB: There is no healing for your injury; your wound is severe. All who hear the news of you applaud your downfall, for who has not experienced your constant cruelty?