2 ULB በዚያን ቀን ግን፣ ንጉሱ እኔን ተመልክቶ እንዲህ አለኝ፣ “ለምን እንዲህ እጅግ አዘንህ? የታመምክ አትመስልም፡፡ ምናልባት መንፈስህ ታውኮ ይሆንን?” እኔም በጣም ፈርቼ ነበር፡፡ BSB BSB: so the king said to me, “Why is your face sad, though you are not ill? This could only be sadness of the heart.” I was overwhelmed with fear
3 ULB እንዲህ ስል መለስኩ፣ “ንጉስ ሆይ፣ ለዘለዓለም ንገስ! ያዘንኩት ያለ ምክንያት አይደለም፣ አባቶቼ የተቀበሩባት ከተማ ፍርስራሽ ሆናለች፣ በከተማዋ ዙሪያ ያሉ በሮቿ በሙሉ ተቃጥለው አመድ ሆነዋል፡፡” BSB BSB: and replied to the king, “May the king live forever! Why should I not be sad when the city where my fathers are buried lies in ruins, and its gates have been destroyed by fire?”
4 ULB ንጉሱ እንዲህ ሲል መለሰልኝ፣ “ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ?” እናም ለእርሱ መልስ ከመስጠቴ አስቀድሞ፣ በሰማይ ወዳለው አምላክ ጸለይኩ፡፡ BSB BSB: “What is your request?” replied the king. So I prayed to the God of heaven
5 ULB ከዚያ እንዲህ ሲል ምላሽ ሰጠሁ፣ “ታደርገው ዘንድ ፈቃድህ ከሆነ፣ እኔም አንተን ደስ አሰኝቼ ከሆነ፣ አባቶቼ የተቀበሩባትን ከተማ ኢየሩሳሌምን መልሼ እንድገነባ ወደዚያ እንድሄድ ፈቀድልኝ፡፡” BSB BSB: and answered the king, “If it pleases the king, and if your servant has found favor in your sight, I ask that you send me to Judah, to the city where my fathers are buried, so that I may rebuild it.”
6 ULB ንጉሱ (ንገስቲቱ አጠገቡ ተቀምጣ ሳለ) እንደህ ሲል ጠየቀኝ፣ “እንድትሄድ ብፈቅድልህ፣ ለስንት ጊዜ በዚያ ትቆያለህ? ደግሞስ መቼ ትመለሳለህ?” እርሱም፣ ወደዚያ የምሄድበትንና ተመልሼ የምመጣበትን ቀን እንዳሳወቅሁት፣ ወዲያውኑ እንድሄድ ፈቃድ ሰጠኝ፡፡ BSB BSB: Then the king, with the queen seated beside him, asked me, “How long will your journey take, and when will you return?” So it pleased the king to send me, and I set a time.
7 ULB ደግሞም ለንጉሱ እንዲህ አልኩት፣ “ለአንተ ለሰጠሁት ታማኝ አገልግሎቴ እንደ ሽልማት አድርገህ፣ ከአፍራጦስ ወንዝ ባሻገር ለሚያስተዳድሩ ገዥዎች ደብዳቤ ስጠኝ፡፡ ወደ ይሁዳ ስገባና ስወጣ በግዛቶቻቸው በደህንነት መጓዝ እችል ዘንድ እንዲፈቅዱልኝ እባክህን ትዕዛዝ ስጣቸው፡፡ BSB BSB: I also said to him, “If it pleases the king, may letters be given to me for the governors west of the Euphrates, so that they will grant me safe passage until I reach Judah.
8 ULB እንዲሁም፣ እባክህን ደኖችህን ለሚያስተዳድረው ለአሳፍ ደብዳቤ ፃፍልኝ፣ ደግሞም በቤተ መቅደሱ አጠገብ የሚገኘውን ግንብ በሮች አምዶቹን ለማበጀት፣ የከተማዋን ቅሮች ለመጠገን፣ እና የምኖርበትን ቤት እንዲሰጠኝ ፃፍለት፡፡” እግዚአብሔር ለዚህ ስራ የሚያስፈልገኝን እንዳገኝ እየረዳኝ ስለነበር፣ ንጉሱ እንዲያደርግ የጠየቅኩትን አደረገልኝ፡፡ BSB BSB: And may I have a letter to Asaph, keeper of the king’s forest, so that he will give me timber to make beams for the gates of the citadel to the temple, for the city wall, and for the house I will occupy.” And because the gracious hand of my God was upon me, the king granted my requests.
9 ULB ወደ ይሁዳ ለመሄድ ተነሳሁ፡፡ ንጉሱ፣ እኔን እንዲያጅቡኝና እንዲጠብቁኝ አንዳንድ ፈረሰኛ የጦር መኮንኖችንና ወታደሮችን ላከ፡፡ ገዥዎቹ ወደሚያስተዳድሩት ግዛት ስንደርስ፣ ከንጉሱ ዘንድ የተላከውን ደብዳቤ ሰጠኋቸው፡፡ BSB BSB: Then I went to the governors west of the Euphrates and gave them the king’s letters. The king had also sent army officers and cavalry with me.
11 ULB ስለዚህም እኔ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቼ በዚያ ለሶስት ቀናት ቆየሁ፡፡ BSB BSB: After I had arrived in Jerusalem and had been there three days,
12 ULB በምሽት ከከተማ ወጣሁ፣ ከእኔ ጋርም ጥቂት ሰዎች ነበሩ፡፡ እኛ የነበረን እኔ የተቀመጥኩበት አንድ እንስሳ ብቻ ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም አደርገው ዘንድ እግዚአብሔር በልቤ ስላስቀመጠው ነገር ለማንም ሰው ምንም አልተናገርኩም፡፡ BSB BSB: I set out at night with a few men. I did not tell anyone what my God had laid on my heart to do for Jerusalem. The only animal with me was the one on which I was riding.
13 ULB በሸለቆው መግቢያ አለፍኩና ከከተማው ቅጥር ውጭ ሄድኩ፡፡ ከዚያ በከተማዋ ዙሪያ ተዟዙሬ የቀበሮዎች ጉድጓድ በሚባለው ጉድጓድ በኩል አለፍኩ፡፡ ከዚያ ወደ ፋንድያ መድፊያ በር አለፍኩ፡፡ በኢየሩሳሌም ዙሪያ የሚገኙ ቅጥሮችን ሁሉ ዞሬ ተመለከትኩ፣ እናም ሁሉም በሮች ተሰባብረው ቅጥሮቹ ክፍት መሆናቸውን አየሁ፣ ደግሞም በቅጥሩ ዙሪያ የነበሩ የእንጨት በሮች ሁሉ አመድ እስኪሆኑ ተቃጥለው ነበር፡፡ BSB BSB: So I went out at night through the Valley Gate toward the Well of the Serpent and the Dung Gate, and I inspected the walls of Jerusalem that had been broken down and the gates that had been destroyed by fire.
14 ULB ከዚያ ወደ ፏፏቴ በር እና የንጉስ ገንዳ ወደሚባለው ገንዳ ሄድኩ፣ ነገር ግን የተቀመጥኩበት አህያ በጠባቡ መተላለፊያ ማለፍ አልቻለችም፡፡ BSB BSB: Then I went on to the Fountain Gate and the King’s Pool, but there was no room for the animal under me to get through;
15 ULB ስለዚህ ወደ ኋላ ዞሬ ወደ በቄድሮን ሸለቆ አጠገብ እያለፍኩ ወደ ኋላ ከመመለሴና ወደ ሸለቆው በር ወደ ከተማዋ ከመግባቴ አስቀድሞ በዚያ የነበሩ ቅጥሮችን ተመለከትኩ፡፡ BSB BSB: so I went up the valley by night and inspected the wall. Then I headed back and reentered through the Valley Gate.
16 ULB የከተማዋ ባለስልጣናት እኔ ወዴት እንደሄድኩ ወይም ምን እንዳደረግኩ አላወቁም ነበር፡፡ ለአይሁድ መሪዎች ወይም ለባለስልጣናቱ ወይም ለካህናቱ ወይም በእድሳቱ ስራ ለሚሳተፉ ለማናቸው ሌሎች ሰዎች ስለዚህ ምንም ነገር አልተናገርኩም፡፡ BSB BSB: The officials did not know where I had gone or what I was doing, for I had not yet told the Jews or priests or nobles or officials or any other workers.
17 ULB እንዲህ አልኩ፣ “በከተማችን ላይ የደረሰውን መጥፎ ነገሮች ሁሉ ሁላችሁም በሚገባ ታውቃላችሁ፡፡ ከተማዋ ፍርስራሽ ሆናለች፣ ሌላው ቀርቶ በሮቿ ተቃጥለው ወድቀዋል፡፡ ኑ፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንደገና ለመገንባት ስራውን እንጀምር፡፡ እኛ ያንን ብናደርግ፣ ከዚህ በኋላ በከተማችን አናፍርም፡፡” BSB BSB: Then I said to them, “You see the trouble we are in. Jerusalem lies in ruins, and its gates have been burned down. Come, let us rebuild the wall of Jerusalem, so that we will no longer be a disgrace.”
18 ULB ከዚያ ከንጉሱ ጋር በተነጋገርኩ ጊዜ እግዚአብሔር እንዴት በመልካምነቱ እንዲረዳንና ንጉሱ ምን እንዳለኝ ነገርኳቸው፡፡ እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ተነስተን የእድሳቱን ስራ እንጀምር!” ስለዚህም ይህን መልካም ሥራ ለመስራት ተነሱ፡፡ BSB BSB: I also told them about the gracious hand of my God upon me, and what the king had said to me. “Let us start rebuilding,” they replied, and they set their hands to this good work.
19 ULB ነገር ግን ሰንበላጥ፣ አሞናዊው አገልጋይ ጦቢያ፣ እና አረባዊው ጌሻም፣ እኛ ለመስራት ያቀድነውን ሰሙ፡፡ በእኛ ላይ ቀለዱ አፌዙብንም፡፤ እንዲህም አሉ፣ “ይህ እናንተ የምትሰሩት ስራ ምንድን ነው? በንጉሱ ላይ እያመጻችሁ ነውን?” BSB BSB: But when Sanballat the Horonite, Tobiah the Ammonite official, and Geshem the Arab heard about this, they mocked us and ridiculed us, saying, “What is this you are doing? Are you rebelling against the king?”
20 ULB እኔ ግን እንዲህ አልኳቸው፣ “በሰማይ ያለው አምላክ ስኬት ይሰጠናል፡፡ እናንተ ግን በዚህ ከተማ ላይ መብት የላችሁም፣ ተሳትፎ የላችም፣ በዚህ ላይ ህጋዊ መብት የላችሁም፣ በኢየሩሳሌም ከተማ ላይ ምንም ታሪካዊ መታሰቢያ የላችሁም፡፡” BSB BSB: So I answered them and said, “The God of heaven is the One who will grant us success. We, His servants, will start rebuilding, but you have no portion, right, or claim in Jerusalem.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.