1 ULB ቆይቶ፣ ሌሎቹ አንዳንድ አይሁዶች በሚያደርጉት ብዙዎቹ ወንዶችና ሚስቶቻቸው ፍትህ ለማግኘት ጮኹ፡፡ BSB BSB: About that time there was a great outcry from the people and their wives against their fellow Jews.
2 ULB አንዳንዶቹ እንዲህ አሉ፣ “እኛ ብዙ ልጆች አሉን፡፡ በልተን ለማደርና በህይወት ለመቆየት እንኳን ብዙ እህል ያስፈልገናል፡፡” BSB BSB: Some were saying, “We and our sons and daughters are numerous. We must get grain in order to eat and stay alive.”
3 ULB ሌሎቹ ደግሞ እንዲህ አሉ፣ “በዚህ የረሃብ ወቅት የምንበላው እህል ለማግኘት የእርሻ መሬታችንን፣ የወይን ተክላችንንና ቤቶቻችንን ማስያዝ ግድ ሆኖብናል፡፡ BSB BSB: Others were saying, “We are mortgaging our fields, our vineyards, and our homes to get grain during the famine.”
4 ULB ሌሎቹም እንዲህ አሉ፣ “ለእርሻ መሬቶቻችንና ለወይን ተክላችን ለንጉሱ ግብር ለመክፈል ገንዘብ መበደር የግድ ሆኖብናል፡፡ BSB BSB: Still others were saying, “We have borrowed money to pay the king’s tax on our fields and vineyards.
5 ULB እኛም እንደ ሌሎቹ አይሁዶች አይሁዳውያን ነን፡፡ የእነርሱ ልጆች ለእነርሱ ጠቃሚ እንደሆኑ ሁሉ፤ የእኛም ልጆች ለእኛ እንደዚያው ናቸው፡፡ ነገር ግን መክፈል የሚገባንን ለመክፈል ስንል ልጆቻችንን ለባርነት ለመሸጥ ተገደናል፡፡ አንዳንድ ሴት ልጆቻችንን አሁን ለባርነት ሸጠናል፡፡ የእርሻ መሬቶቻችንና የወይን ተክሎቻችን ከእኛ ተወስደዋል፣ ስለዚህም መክፈል ያለብንን ገንዘብ ለመክፈል ገንዘቡ የለንም፡፡” BSB BSB: We and our children are just like our countrymen and their children, yet we are subjecting our sons and daughters to slavery. Some of our daughters are already enslaved, but we are powerless to redeem them because our fields and vineyards belong to others.”
6 ULB እነዚህን እነርሱ የተጨነቁባቸውን ነገሮች በሰማሁ ጊዜ በጣም ተቆጣሁ፡፡ BSB BSB: When I heard their outcry and these complaints, I became extremely angry,
7 ULB ስለዚህም ማድረግ ያለብኝን ነገር አሰብ፡፡ ለመሪዎችና ለሹማምንቱ እንዲህ አልኳቸው፣ “ገንዘብ ሲበደሯችሁ የገዛ ዘመዶቻችሁን ወለድ ታስከፍላላችሁ፡፡ ይህ ልክ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ!” ከዚያም ክስ እንዲያቀርቡባችሁ ብዙ ሰዎችን በእነርሱ ላይ ሰብስቤ ጠራሁ፡፡ BSB BSB: and after serious thought I rebuked the nobles and officials, saying, “You are exacting usury from your own brothers!” So I called a large assembly against them
8 ULB እንዲህም አልኳቸው፣ “አንዳንድ አይሁዳዊ ወገኖቻችን የአህዛብ ባሪያዎች ለመሆን ራሳቸውን ለመሸጥ ተገደው ነበር፡፡ የቻልነውን ያህል፣ መልሰን ገዝተናቸው ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን እናንተ የገዛ ወገኖችሁን እንኳን እየሸጣችሁ ነው፤ ይኸውም የገዛ ወገኖቻቸው ወደ ሆኑ አይሁዶች ተመልሰው ይሸጡ ዘንድ ነው!” ይህን ስናገራቸው፣ ምላሽ አልሰጡም፡፡ አንዲት ቃል እንኳን አልመለሱም፡፡ BSB BSB: and said, “We have done our best to buy back our Jewish brothers who were sold to foreigners, but now you are selling your own brothers, that they may be sold back to us!” But they remained silent, for they could find nothing to say.
9 ULB ከዚያ እንዲህ አልኳቸው፣ “የምታደርጉት ነገር ክፉ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ልትታዘዙና ትክክል የሆነውን ልታደርጉ አይገባችሁምን? ይህን ብታደርጉ፣ ጠላቶቻችን በንቀት እንዳያዩን ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ BSB BSB: So I continued, “What you are doing is not right. Shouldn’t you walk in the fear of our God to avoid the reproach of our foreign enemies?
10 ULB እኔና አይሁዳዊ ወገኖቼ እንዲሁም አገልጋዮቼ ለህዝቡ ገንዘብና እህል አበደርን፡፡ ነገር ግን ሁላችንም ከእነዚህ ብድሮች በአንዱም ወለድ መቀበል እናቁም፡፡ BSB BSB: I, as well as my brothers and my servants, have been lending the people money and grain. Please, let us stop this usury.
11 ULB እንደዚሁም፣ የወሰዳችሁባቸውን የእርሻ መሬቶቻቸውን፣ የወይን ስፍራቸውን፣ የወይራ ዛፍ ቦታቸውን እንዲሁም ቤቶቻቸውን ልትመልሱላቸው ይገባል፡፡ እንደዚሁም ገንዘብ፣ እህል፣ ወይን፣ እና የወይራ ዘይት ሲበደሯችሁ ያስከፈላችኋቸውን ወለዶች ልትመልሱላቸው ይገባል፡፡ ይህን ዛሬውን ልታደርጉ ይገባል!” BSB BSB: Please restore to them immediately their fields, vineyards, olive groves, and houses, along with the percentage of the money, grain, new wine, and oil that you have been assessing them.”
12 ULB መሪዎች እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “ያልከንን እናደርጋለን፡፡ እንዲሰጡን ያስገደድናቸውን ነገር ሁሉ እንመልስላቸዋለን፣ ደግም ሌላ ተጨማሪ ነገር እንዲሰጡን አንጠይቅም፡፡” ከዚያ ካህናቱን ሰበሰብኩ፣ እናም ቃል የገቡትን እንዲያደርጉት አስማልኳቸው፡፡ BSB BSB: “We will restore it,” they replied, “and will require nothing more from them. We will do as you say.” So I summoned the priests and required of the nobles and officials an oath that they would do what they had promised.
13 ULB የክህነት ልብሴን እጥፋት አራግፌ እንዲህ አልኳቸው፣ “ልታደርጉት አሁን ቃል የገባችሁትን ባታደርጉ፣ እኔ ልብሴን እንዳራገፍኩ እግዚአብሔር ያራግፋችኋል፡፡” እነርሱም “አሜን እንዳልከው ይሁን!” ሲሉ መለሱ፤ ደግሞም ያህዌን አወደሱ፡፡ ከዚያ ለማድረግ ቃል የገቡትን አደረጉ፡፡ BSB BSB: I also shook out the folds of my robe and said, “May God likewise shake out of his house and possessions every man who does not keep this promise. May such a man be shaken out and have nothing!” The whole assembly said, “Amen,” and they praised the LORD. And the people did as they had promised.
14 ULB አርጤክስስ የፋርስ ንጉስ በነበረበት በሀያኛው ዓመት የይሁዳ ገዥ ሆኜ ተሹሜ ነበር፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ እስከ ሰላሳ ሁለተኛው የንግስናው አመት ድረስ እኔም ሆንኩ የእኔ ሹማምንት ገዥ በመሆኔ ለቀለብ የተፈቀደልኝን ገንዘብ አልተቀበልንም፡፡ BSB BSB: Furthermore, from the day King Artaxerxes appointed me to be their governor in the land of Judah, from his twentieth year until his thirty-second year (twelve years total), neither I nor my brothers ate the food allotted to the governor.
15 ULB ከእኔ አስቀድሞ ገዥ የነበሩ ሰዎች በየቀኑ አርባ የብር ሳንቲሞች ለምግብና ለወይን በመጠየቅ በህዝቡ ላይ ሸክም አክብደውበት ነበር፡፡ አገልጋዮቻቸው ጭምር ህዝቡን ይጨቁኑ ነበር፡፡ እኔ ግን ያን አላደረግኩም፣ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ክብር መስጠት እፈልግ ነበር፡፡ BSB BSB: The governors before me had heavily burdened the people, taking from them bread and wine plus forty shekels of silver. Their servants also oppressed the people. But I did not do this, because of my fear of God.
16 ULB በዚህ ቅጥር ላይ መስራቴንም ቀጠልኩ፣ እኛም ከህዝቡ ምንም መሬት አልገዛንም፡፡ ለእኔ የሚሰሩት ሁሉ በቅጥሩ ስራ ተባበሩን፡፡ BSB BSB: Instead, I devoted myself to the construction of the wall, and all my servants were gathered there for the work; we did not acquire any land.
17 ULB እንዲሁም፣ በየዕለቱ ከገበታችን አይሁዶችንና ሹማምንቱን፣ አንድ መቶ ሀምሳ ሰዎችን፣ እና በዙሪያችን ካሉ አገሮች የመጡ ጎብኚዎችን እንመግብ ነበር፡፡ BSB BSB: There were 150 Jews and officials at my table, besides the guests from the surrounding nations.
18 ULB በየቀኑ አገልጋዮቼ አንድ በሬ፣ ስድስት ሙክቶች እና የዶሮዎች ስጋ እንዲያቀርቡ አደርግ ነበር፡፡ በየአስሩ ቀን ብዙ የሆነ አዲስ ወይን ጠጅ አቀርብላቸው ነበር፡፡ ነገር ግን ህዝቡ እጅግ ብዙ ግብር በመክፈል ጫና እንደሚበዛበት አውቅ ነበር፣ ስለዚህም እንደ አገረ ገዥ የተፈቀደልኝን ገንዘብ እንኳን አልቀበልም ነበር፡፡ BSB BSB: Each day one ox, six choice sheep, and some fowl were prepared for me, and once every ten days an abundance of all kinds of wine was provided. But I did not demand the food allotted to the governor, because the burden on the people was so heavy.
19 ULB አምላኬ፣ አስበኝ፣ እናም ለዚህ ህዝብ ላደረግኩት ሽልማት ስጠኝ፡፡ BSB BSB: Remember me favorably, O my God, for all that I have done for this people.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.