1 ULB ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ BSB BSB: Then the LORD said to Moses,
2 ULB ”ሁለት የብር መለከቶች አብጁ፡፡ በብር ቀጥቅጠህ አብጃቸው፡፡ መለከቶቹን ማህበረሰቡን በጋራ ለመጥራትና ከመንደሮቸው እንዲንቀሳቀሱ ጥሪ ለማሰማት ተጠቀምባቸው፡፡ BSB BSB: “Make two trumpets of hammered silver to be used for calling the congregation and for having the camps set out.
3 ULB ካህናቱ ማህበረሰቡን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ በፊትህ ለመሰብሰብ መለኮቶቹን ይንፉ፡፡ BSB BSB: When both are sounded, the whole congregation is to assemble before you at the entrance to the Tent of Meeting.
4 ULB ካህናቱ አንድ መለከት ብቻ ከነፉ፣ የእስራኤል ነገድ መሪዎች ይሰበስቡ፡፡ BSB BSB: But if only one is sounded, then the leaders, the heads of the clans of Israel, are to gather before you.
5 ULB ከፍ ባለ ድምጽ ስትነፉ፣ በስተምስራቅ የሰፈሩት ጉዟቸውን ይጀምሩ፡፡ BSB BSB: When you sound short blasts, the camps that lie on the east side are to set out.
6 ULB ለሁለተኛ ጊዜ ከፍ ባለ ድምጽ ስትነፋ በደቡብ በኩል የሰፈሩት ጉዟቸውን ይጀምሩ፡፡ ለጉዟቸው ከፍ ያለ የመለከት ድምጽ ያሰሙ፡፡ BSB BSB: When you sound the short blasts a second time, the camps that lie on the south side are to set out. The blasts are to signal them to set out.
7 ULB ማህበረሰቡ በአንድነት ሲበሰበሰብ፣ መለከቶች ይነፉ ነገር ግን ድምጹ ከፍ አይበል፡፡ BSB BSB: To convene the assembly, you are to sound long blasts, not short ones.
8 ULB የካህኑ የአዘሮን ልጆች፣ መለኮቶቹን ይንፉ፡፡ በትውልዶቻችሁ ሁሉ ዘንድ ይህ ለእናንተ ሁልጊዜም ስርዓት ይሆናል፡፡ BSB BSB: The sons of Aaron, the priests, are to sound the trumpets. This shall be a permanent statute for you and the generations to come.
9 ULB በሚወሯችሁ ተቃዋሚዎቻች ላይ በምድራች ለጦርነት ስትወጡ፣ ለማንቂያ የመለከት ድምጽ ታሰማላችሁ፡፡ እኔ፣ አምላካችሁ ያህዌ፣ አስባችኋለሁ ደግሞም ከጠላቶቻችሁ አድናችኋለሁ፡፡ BSB BSB: When you enter into battle in your land against an adversary who attacks you, sound short blasts on the trumpets, and you will be remembered before the LORD your God and saved from your enemies.
10 ULB እንደዚሁም፣ በመደበኛ ባዕላቶቻችሁም ሆነ በወራቶች መጀመሪያ ላይ በክብረ በዓል ወቅት ለሚቃጠል መስዋዕቶቻችሁ ክብርና በህብረት መስዋዕቶቻችሁ መስዋዕቶች ላይ መለኮቶችን መንፋት አለባች፡፡ እነዚህ እናንተ የእኔ የአምላካችሁ ለመሆናችሁ መታሰቢያ ሆነው ያገለግላሉ፡፡ እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፡፡” BSB BSB: And on your joyous occasions, your appointed feasts, and the beginning of each month, you are to blow the trumpets over your burnt offerings and peace offerings to serve as a reminder for you before your God. I am the LORD your God.”
11 ULB በሁለተኛው አመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በወሩ ሀያኛ ቀን ደመናው ከቃል ኪዳኑ ምስክር ማደሪያ ላይ ተነሳ፡፡ BSB BSB: On the twentieth day of the second month of the second year, the cloud was lifted from above the tabernacle of the Testimony,
13 ULB የመጀመሪያ ጉዟቸው፣ በሙሴ በኩል የተሰጣቸውን የያህዌን ትዕዛዝ ተከትለው አደረጉ፡፡ BSB BSB: They set out this first time according to the LORD’s command through Moses.
14 ULB በይሁዳ ትውልዶች ዓርማ ስር ያለው ሰፋሪዎች በመጀመሪያ ተንቀሳቀሱ፡፡ የይሁዳን ሠራዊት የሚመራው የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነበር፡፡ BSB BSB: First, the divisions of the camp of Judah set out under their standard, with Nahshon son of Amminadab in command.
15 ULB የይሳኮርን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የሶገር ልጅ ናትናኤል ነበር፡፡ BSB BSB: Nethanel son of Zuar was over the division of the tribe of Issachar,
16 ULB የዛብሎንን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የኬሎን ልጅ ኤልያብ ነበር፡፡ BSB BSB: and Eliab son of Helon was over the division of the tribe of Zebulun.
17 ULB የማደሪያ ድንኳኑን የተሸከሙት የጌድሶን እና የሜራሪ ትውልዶች፣ ማደሪያ ድንኳኑን ነቅለው ጉዟቸውን ጀመሩ፡፡ BSB BSB: Then the tabernacle was taken down, and the Gershonites and the Merarites set out, transporting it.
18 ULB ቀጥሎ፣ በሮቤል ሰፈር ሰራዊት ዓርማ ስር የነበሩት ጉዟቸውን ቀጠሉ፡፡ የሮቤልን ሰራዊት የሚመራው የሶዲዮር ልጅ ኤሊሱር ነበር፡፡ BSB BSB: Then the divisions of the camp of Reuben set out under their standard, with Elizur son of Shedeur in command.
19 ULB የስምዖንን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራዊ የሱሪስዓይ ልጅ ስለሚኤል ነበር፡፡ BSB BSB: Shelumiel son of Zurishaddai was over the division of the tribe of Simeon,
20 ULB የጋድን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የራጉኤል ልጅ ኤሊሳፍ ነበር፡፡ BSB BSB: and Eliasaph son of Deuel was over the division of the tribe of Gad.
21 ULB ቀዓታውያን ተነሱ፡፡ እነርሱ የቅድስተ ቅዱሳኑን ቅዱስ ዕቃዎች ተሸከሙ፡፡ ቀዓታውያን ቀጣዩ ሰፈር ከመድረሳቸው አስቀድሞ ሌሎች ማደሪያ ድንኳን ይተክላሉ፡፡ BSB BSB: Then the Kohathites set out, transporting the holy objects; the tabernacle was to be set up before their arrival.
22 ULB የኤፍሬምን ሰራዊት የሚመራው የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ነበር፡፡ BSB BSB: Next, the divisions of the camp of Ephraim set out under their standard, with Elishama son of Ammihud in command.
23 ULB የምናሴን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ነበር፡፡ BSB BSB: Gamaliel son of Pedahzur was over the division of the tribe of Manasseh,
24 ULB የብንያምን ትውልዶች ሠራዊት የሚመራው የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ነበር፡፡ BSB BSB: and Abidan son of Gideoni was over the division of the tribe of Benjamin.
25 ULB በዳን ትውልዶች ዓርማ ስር የሰፈሩት ሠራዊቶች በመጨረሻ ይወጣሉ፡፡ የዳንን ሰራዊት የሚመራው የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ነበር፡፡ BSB BSB: Finally, the divisions of the camp of Dan set out under their standard, serving as the rear guard for all units, with Ahiezer son of Ammishaddai in command.
26 ULB የአቤርን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የኤክራን ልጅ ፋግኤል ነበር፡፡ BSB BSB: Pagiel son of Ocran was over the division of the tribe of Asher,
27 ULB የንፍታሌምን ትውልዶች ሰራዊት የሚመራው የዔናን ልጅ አኪሬ ነበር፡፡ BSB BSB: and Ahira son of Enan was over the division of the tribe of Naphtali.
28 ULB የእስራኤል ሰዎች ሰራዊቶች ጉዟቸውን ያደረጉት በዚህ መልክ ነው፡፡ BSB BSB: This was the order of march for the Israelite divisions as they set out.
29 ULB ሙሴ ከምድያማዊው የራጉኤል ልጅ ከአባብ ጋር ተነጋገረ፡፡ ራጉኤል የሙሴ ሚስት አባት ነበር፡፡ ሙሴ ከአባብ ጋር ተነጋገረ እንዲህም አለ፣ “ያህዌ እሰጣችኋለሁ ወዳለን ስፍራ እየተጓዝን ነው፡፡ ያህዌ እንዲህ ብሎን ነበር፣ ‘እኔ ለእናንተ የተናገርኩትን እርሷኑ ስፍራ እሰጣችኋለሁ፡፡’ አንተ ከእኛ ጋር አብረኸን ና እኛም መልካም እናደርግልሃለን፡፡ ያህዌ ለእስራኤል መልካም ለማድረግ ቃል ገብቷል፡፡” BSB BSB: Then Moses said to Hobab, the son of Moses’ father-in-law Reuel the Midianite, “We are setting out for the place of which the LORD said: ‘I will give it to you.’ Come with us, and we will treat you well, for the LORD has promised good things to Israel.”
30 ULB አባብ ግን ሙሴን እንዲህ አለው፣ “እኔ ከአንተ ጋር አልሄድም፡፡ እኔ ወደ ገዛ ምድሬና ወደ ራሴ ህዝብ እሄዳለሁ፡፡” BSB BSB: “I will not go,” Hobab replied. “Instead, I am going back to my own land and my own people.”
31 ULB ከዚያም ሙሴ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “እባክህን ከእኛ አትለይ፡፡ በበረሃ እንዴት መስፈር እንደሚቻል ታውቃለህ፡፡ ስንሰፍር ልትመለከተን ይገባል፡፡ BSB BSB: “Please do not leave us,” Moses said, “since you know where we should camp in the wilderness, and you can serve as our eyes.
32 ULB ከእኛ ጋር ብትሄድ፣ ያህዌ ለእኛ የሚያደርግልንን በጎነት ያንኑ እኛም ለአንተ እናደርግልሃለን፡፡” BSB BSB: If you come with us, we will share with you whatever good things the LORD gives us.”
33 ULB ከያህዌ ተራራ ተነስተው ለሶስት ቀናት ተጓዙ፡፡ የያህዌ የቃልዳኑ ታቦት የሚያርፍበትን ስፍራ እንዲያገኙ ለመፈለግ ለሶስት ቀናት በፊታቸው ተጓዘ፡፡ BSB BSB: So they set out on a three-day journey from the mountain of the LORD, with the ark of the covenant of the LORD traveling ahead of them for those three days to seek a resting place for them.
34 ULB ሲጓዙ የያህዌ ደመና በቀን ብርሃን በላያቸው ነበር፡፡ BSB BSB: And the cloud of the LORD was over them by day when they set out from the camp.
35 ULB ታቦቱ በተነሳበት ጊዜ ሁሉ፣ ሙሴ እንዲህ ይላል፣ “ያህዌ ሆይ፣ ተነስ፡፡ ጠላቶችህን በትን፡፡ የሚጠሉህ ከአንተ እንዲሸሹ አድርግ፡፡” BSB BSB: Whenever the ark set out, Moses would say, “Rise up, O LORD! May Your enemies be scattered; may those who hate You flee before You.”
36 ULB ታቦቱ በቆመ ጊዜ ሁሉ፣ ሙሴ “ያህዌ ሆይ፣ ብዙ አስር ሺህ ወደሚሆኑት እስራኤላውያን ተመለስ” ይል ነበር፡፡ BSB BSB: And when it came to rest, he would say: “Return, O LORD, to the countless thousands of Israel.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.