1 ULB ያህዌ ሙሴን እንዲህ አለው፣ BSB BSB: And the LORD said to Moses,
2 ULB “ለእስራኤል ሰዎች ተናገራቸው፡፡ እንዲህ በላቸው፣ ‘አንድ ወንድ ወይም አንዲት ሴት ናዝራዊ ሆኖ ራሱን ለያህዌ በተለየ ስዕለት ሲለይ፣ BSB BSB: “Speak to the Israelites and tell them that if a man or woman makes a special vow, the vow of a Nazirite, to separate himself to the LORD,
3 ULB ከወይንና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን ይለይ፡፡ ከወይን ወይም ከሚያሰክር መጠጥ የተሰራ ኮምጣጤ አይጠጣ፡፡ ማናቸውንም የወይን ጭማቂ አይጠጣ ወይም የወይን ፍሬ ወይም ዘቢብ አይብላ፡፡ BSB BSB: he is to abstain from wine and strong drink. He must not drink vinegar made from wine or strong drink, and he must not drink any grape juice or eat fresh grapes or raisins.
4 ULB ለእኔ በተለየባቸው ቀናት ሁሉ፣ ከፍሬያቸው ግልፋፊ የተሰራ ማናቸውንም ነገር ጨምሮ ከወይን የተሰራ ምንም ነገር አይብላ፡፡ BSB BSB: All the days of his separation, he is not to eat anything that comes from the grapevine, not even the seeds or skins.
5 ULB ለያህዌ ራሱን የለየባቸው ቀናት እስኪያበቁ ድረስ በስለቱ ጊዜያት ሁሉ ራሱን ምላጭ አይንካው፡፡ ለያህዌ የተለየ ይሁን፡፡ ፀጉሩ በራሱ ላይ እንዲያድግ ይተወው፡፡ BSB BSB: For the entire period of his vow of separation, no razor shall touch his head. He must be holy until the time of his separation to the LORD is complete; he must let the hair of his head grow long.
6 ULB ራሱን ለያህዌ በለየባቸው ጊዜያት ሁሉ፣ ወደ ሞተ ሰው አይቅረብ፡፡ BSB BSB: Throughout the days of his separation to the LORD, he must not go near a dead body.
7 ULB አባቱ፣ እናቱ፣ ወንድሙ ወይም እህቱ ቢሞቱ እንኳን ራሱን ማርከስ የለበትም፡፡ ይህም የሚሆነው ማንም ሰው በረጅም ጠጉሩ እንደሚመለከተው፣ ለእግዚአብሔር የተለየ ነው፡፡ BSB BSB: Even if his father or mother or brother or sister should die, he is not to defile himself, because the symbol of consecration to his God is upon his head.
8 ULB በተለየበት ጊዜ ሁሉ ለያህዌ የተለየ ቅዱስ ነው፡፡ BSB BSB: Throughout the time of his separation, he is holy to the LORD.
9 ULB አንድ ሰው ድንገት አጠገቡ ቢሞት እና ማንነቱን የለየበትን ፀጉሩን ቢያረክስበት፣ መንጻት ባለበት ከሰባተኛው ቀን በኋላ ራሱን ይላጭ፡፡ ራሱን መላጨት ያለበት በዚያን ጊዜ ነው፡፡ BSB BSB: If someone suddenly dies in his presence and defiles his consecrated head of hair, he must shave his head on the day of his cleansing—the seventh day.
10 ULB በስምተኛው ቀን ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለካህኑ ያቅርብ፡፡ BSB BSB: On the eighth day he must bring two turtledoves or two young pigeons to the priest at the entrance to the Tent of Meeting.
11 ULB ካህኑ አንዱን ወፍ ለኃጢአት መስዋዕት ሌላውን የሚቃተል መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ ሬሳ አጠገብ በመሆን ኃጢአት ሰርቷልና እነዚህ ለእርሱ ስርየት ይቀርባሉ፡፡ በዚያው ዕለት ራሱን መልሶ ለያህዌ ይስጥ፡፡ BSB BSB: And the priest is to offer one as a sin offering and the other as a burnt offering to make atonement for him, because he has sinned by being in the presence of the dead body. On that day he must consecrate his head again.
12 ULB ለተለየበት ጊዜ ራሱን ለያህዌ መልሶ ይስጥ፡፡ ለበደል መስዋዕት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት ያምጣ፡፡ ራሱን ከማርከሱ በፊት የነበሩ ቀናት አይቆጠሩም፣ ምክንያቱም ለእግዚአብሔር ተለይቶ ባለበት ጊዜ ረክሷል፡፡ BSB BSB: He must rededicate his time of separation to the LORD and bring a year-old male lamb as a guilt offering. But the preceding days shall not be counted, because his separation was defiled.
13 ULB ናዝራዊ መለየቱ ስለሚያበቃበት ጊዜ የተሰጠው ህግ ይህ ነው፡፡ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ያምጡት፡፡ BSB BSB: Now this is the law of the Nazirite when his time of separation is complete: He must be brought to the entrance to the Tent of Meeting,
14 ULB መስዋዕቱን ለያህዌ ያቅርቡ ነውር የሌለበት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት የሚቃጠል መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ ለህብረት መስዋዕት ነውር የሌለበት አውራ በግ ያምጣ፡፡ BSB BSB: and he is to present an offering to the LORD of an unblemished year-old male lamb as a burnt offering, an unblemished year-old female lamb as a sin offering, and an unblemished ram as a peace offering—
15 ULB እንደዚሁም እርሾ ያልገባበት አንድ መሶብ ዳቦ፣ በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት ዳቦዎች፣ በዘይት የተቀባ እርሾ የሌለበት የገብስ ቂጣ፣ ከእህል ቁርባንና ከመጠጥ መስዋዕቶች ጋር ያምጣ፡፡ BSB BSB: together with their grain offerings and drink offerings—and a basket of unleavened cakes made from fine flour mixed with oil and unleavened wafers coated with oil.
16 ULB ካህኑ እነዚህን በያህዌ ፊት ያቅርባቸው፡፡ እርሱ የኃጢአት መስዋዕቱንና የሚቃጠል መስዋዕቱን ያቅርብ፡፡ BSB BSB: The priest is to present all these before the LORD and make the sin offering and the burnt offering.
17 ULB ለያህዌ የህብረት መስዋዕቱን፣ እርሾ ካልገባበት ከመሶቡ ዳቦ ጋር፣ አውራ በጉን መስዋዕት አድርጎ ያቅርብ፡፡ እንዲሁም ካህኑ የእህል ቁርባኑን እና የመጠጥ መስዋዕቱን ጭምር ያቅርብ፡፡ BSB BSB: He shall also offer the ram as a peace offering to the LORD, along with the basket of unleavened bread. And the priest is to offer the accompanying grain offering and drink offering.
18 ULB ናዝራዊው ለእግዚአብሔር መለየቱን የሚያሳየውን ፀጉሩን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጭ፡፡ ፀጉሩን ከራሱ ወስዶ የህብረት መስዋዕቶቹ በሚቀርቡበት በሚነደው እሳት ውስጥ ይጨምረው፡፡ BSB BSB: Then at the entrance to the Tent of Meeting, the Nazirite is to shave his consecrated head, take the hair, and put it on the fire under the peace offering.
19 ULB ካህኑ የተቀቀለውን አውራ በግ ወርች፣ ከመሶቡ ውስጥ እርሾ ያልገባበትን አንድ ዳቦ፣ እና አንድ እርሾ ያልገባበት የገብስ ቂጣ ይውሰድ፡፡ ናዝራዊው መለየቱን የሚያሳየውን ጸጉሩን ከተላጨ በኋላ ካህኑ እነዚህን በእጆቹ ያስይዘው፡፡ BSB BSB: And the priest is to take the boiled shoulder from the ram, one unleavened cake from the basket, and one unleavened wafer, and put them into the hands of the Nazirite who has just shaved the hair of his consecration.
20 ULB ካህኑ እነዚህን መስዋዕት አድርጎ በያህዌ ፊት ከፍ አድርጎ ያንሳቸውና ለእርሱ ያቅርባቸው፡፡ ይህ ከፍ ተደርጎ ከተነሳው ፍርምባና ከቀረበው ወርች ጋር ለካህኑ ተለየ ቅዱስ ምግብ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ናዝራዊው ወይን ሊጠጣ ይችላል፡፡ BSB BSB: The priest shall then wave them as a wave offering before the LORD. This is a holy portion for the priest, in addition to the breast of the wave offering and the thigh that was presented. After that, the Nazirite may drink wine.
21 ULB ለያህዌ ለመለየት ስዕለቱን ያቀረበ ናዝራዊ ህጉ ይህ ነው፡፡ ማናቸውንም ሌሎች ነገሮች ቢሰጥ በናዝራዊነት ህግ መሠረት እንዲጠብቃቸው የተሰጡትን ቃል ኪዳኖች ለመጠበቅ የገባውን የስዕለት ግዴታዎች መጠበቅ አለበት፡፡” BSB BSB: This is the law of the Nazirite who vows his offering to the LORD for his separation, in addition to whatever else he can afford; he must fulfill whatever vow he makes, according to the law of his separation.”
22 ULB ያህዌ እንደገና ሙሴን ተናገረው፡፡ እንዲህም አለው፣ BSB BSB: Then the LORD said to Moses,
23 ULB “ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ በላቸው፣ ‘የእስራኤልን ሰዎች በዚህ መንገድ ባርኳቸው፡፡ እንደዚህ በሏቸው፣ BSB BSB: “Tell Aaron and his sons: This is how you are to bless the Israelites. Say to them:
25 ULB ያህዌ ብርሃኑን በእናንተ ላይ ያብራራ ፊቱን ይመልስላችሁ፣ ይራራላች፡፡ BSB BSB: may the LORD cause His face to shine upon you and be gracious to you;
26 ULB ያህዌ በሞገስ ያጥግባችሁ፣ ሰላምንም ይስጣችሁ፡፡’” BSB BSB: may the LORD lift up His countenance toward you and give you peace.’
27 ULB ለእስራኤል ሕዝብ ስሜን የሚያስተዋውቁት በዚህ መንገድ ነው፡፡ እኔም እባርካቸዋለሁ፡፡” BSB BSB: So they shall put My name on the Israelites, and I will bless them.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.