1 ULB ጥበብ እየጮኸች አይደለምን? ማስተዋልስ ድምጿን ከፍ አላደረገችምን? BSB BSB: Does not wisdom call out, and understanding raise her voice?
2 ULB ከመንገድ አጠገብ ባሉት ኮረብታዎች ጫፍ ላይ፣ መንገዶች በሚገናኙበት ቦታ፣ ጥበብ ትቆማለች፡፡ BSB BSB: On the heights overlooking the road, at the crossroads she takes her stand.
3 ULB ወደ ከተማይቱ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣ በከተማይቱ መግቢያ አጠገብ፣ ትጣራለች፡፡ BSB BSB: Beside the gates to the city, at the entrances she cries out:
4 ULB እናተ ሰዎች፣ ወደ እናንተ እጣራለሁ፣ ድምጼንም ከፍ አድርጌ ወደ ሰው ልጆች እጮኸለሁ፡፡ BSB BSB: “To you, O men, I call out, and my cry is to the sons of men.
5 ULB እናንተ ትምህርት ያላገኛችሁ፣ ጠንቃቃነትን ተማሩ፣ እናንተ እውቀትን የምትጠሉ፣ የሚያስተውል ልብ ይኑራችሁ፡፡ BSB BSB: O simple ones, learn to be shrewd; O fools, gain understanding.
6 ULB የከበሩ ነገሮችን እናገራለሁና አድምጡኝ፣ ከንፈሮቼ ሲከፈቱ ቀና የሆነውን ነገር እናገራለሁ BSB BSB: Listen, for I speak of noble things, and the opening of my lips will reveal right.
7 ULB አንደበቴ እውነትን ይናራልና፣ ከንፈሮቼም ክፋትን ይጠላሉና፡፡ BSB BSB: For my mouth will speak the truth, and wickedness is detestable to my lips.
8 ULB ከአንደበቴ የሚወጡ ቃሎች ሁሉ ጽድቅ ናቸው፤ በእነርሱ ውስጥ ጠማማ ወይም አሳሳች ነገር የለውም፡፡ BSB BSB: All the words of my mouth are righteous; none are crooked or perverse.
9 ULB ለሚያስተውል ሰው ቃሎቼ በሙሉ ቀና ናቸው፤ እውቀትን ለሚያገኙ ቃሎቼ ትክክለኛ ናቸው፡፡ BSB BSB: They are all plain to the discerning, and upright to those who find knowledge.
10 ULB ከብር ይልቅ ተግሳጼን ምረጡ፣ ከንጹህ ወርቅም ይልቅ እውቀትን ምረጡ፡፡ BSB BSB: Receive my instruction instead of silver, and knowledge rather than pure gold.
11 ULB እኔ ጥበብ፣ ከከበረ ዕንቁ እበልጣለሁና፤ ከምትመኙት ነገር በሙሉ ከእኔ ጋር የሚስተካከል የለም፡፡ BSB BSB: For wisdom is more precious than rubies, and nothing you desire compares with her.
12 ULB እኔ ጥበብ፣ ከጥንቃቄ ጋር እኖራለሁ፣ እውቀትና ነገሮችን ለይቶ ውሳኔ የመስጠት ኃይልም አለኝ፡፡ BSB BSB: I, wisdom, dwell together with prudence, and I find knowledge and discretion.
13 ULB እግዚአብሔርን መፍራት ክፋትን ይጠላል፤ ትዕቢት፣ እብሪት፣ ክፉ መንገድና ጠማማ ንግግር እጠላለሁ፣ ፈጽሞም እጠላቸዋለሁ፡፡ BSB BSB: To fear the LORD is to hate evil; I hate arrogant pride, evil conduct, and perverse speech.
14 ULB እኔ መልካም ምክርና እውነተኛ ጥበብ አለኝ፤ ማስተዋል አለኝ፣ ብርታትም የእኔ ነው፡፡ BSB BSB: Counsel and sound judgment are mine; I have insight and strength.
15 ULB ነገስታት፣ የከበሩ ሰዎችና በፍትሃዊነት ሕዝብን የሚመሩ ሁሉ በእኔ ያስተዳድራሉ፡፡ BSB BSB: By me kings reign, and rulers enact just laws;
16 ULB መሳፍንቶች፣ የከበሩ ሰዎችና በፍትህ ሕዝብን የሚመሩ ሁሉ በእኔ ያስተዳድራሉ፡፡ BSB BSB: By me princes rule, and all nobles who govern justly.
17 ULB የሚወዱኝን እወዳቸዋለሁ፣ ተግተው የሚፈልጉኝም ያገኙኛል፡፡ BSB BSB: I love those who love me, and those who seek me early shall find me.
18 ULB ባለጠግነትና ክብር፣ ዘላቂነት ያለው ሃብትና ጽድቅም በእኔ ዘንድ አሉ፡፡ BSB BSB: With me are riches and honor, enduring wealth and righteousness.
19 ULB ፍሬየ ከወርቅ ይበልጣል፣ ከነጠረ ወርቅም ይበልጣል፤ ስጦታየም ከንጹህ ብር ይበልጣል፡፡ BSB BSB: My fruit is better than gold, pure gold, and my harvest surpasses choice silver.
20 ULB እኔ በጽድቅ መንገድ እሄዳለሁ፣ ወደ ፍትህ በሚወስድ ጎዳና እጓዛለሁ፣ BSB BSB: I walk in the way of righteousness, along the paths of justice,
21 ULB ስለዚህ ለሚወዱኝ ሀብትን እሰጣቸዋለሁ፣ ግምጃ ቤታቸውንም እሞላለሁ፡፡ BSB BSB: bestowing wealth on those who love me and making their treasuries full.
23 ULB ከመጀመርያ፣ ምድር ከመፈጠሯ በፊት፣ ከረጅም ዘመናት ጀምሮ ተሾምሁ፡፡ BSB BSB: From everlasting I was established, from the beginning, before the earth began.
24 ULB ውቅያኖሶች ሳይኖሩ፣ የውኃ ምንጮች ሳይፈልቁ በፊት፣ እኔ ተወልጄ ነበር፣ BSB BSB: When there were no watery depths, I was brought forth, when no springs were overflowing with water.
25 ULB ተራሮች ገና ሳይመሰረቱ፣ ከኮረብቶችም በፊት፣ እኔ ተወለድሁ፡፡ BSB BSB: Before the mountains were settled, before the hills, I was brought forth,
26 ULB እግዚአብሔር ምድርንና ሜዳዎቿን፣ የመጀመርያውን የዓለም አፈር እንኳ ከመፍጠሩ በፊት እኔ ተወለድሁ፡፡ BSB BSB: before He made the land or fields, or any of the dust of the earth.
27 ULB እርሱ ሰማያትን ሲመሰርት፣ በውቅያኖስ ገጽ የአድማስን ምልክት ባደረገ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡ BSB BSB: I was there when He established the heavens, when He inscribed a circle on the face of the deep,
28 ULB እርሱ በላይ ያሉትን ደመናት ባጸና ጊዜ፣ የውቅያኖስን ምንጮች በመሰረተ ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡ BSB BSB: when He established the clouds above, when the fountains of the deep gushed forth,
29 ULB ውሆች የእርሱን ትዕዛዝ አልፈው እንዳያጥለቀልቁ እርሱ ለባህር ድንበርን ባበጀለት ጊዜ፣ የምድርም መሰረት የት መሆን እንዳለበት በወሰነበት ጊዜ እኔ እዚያ ነበርሁ፡፡ BSB BSB: when He set a boundary for the sea, so that the waters would not surpass His command, when He marked out the foundations of the earth.
30 ULB እኔ ዋና ሰራተኛ ሆኜ በአጠገቡ ነበርሁ፣ እኔ ዕለት በዕለት እርሱን ደስ አሰኘው ነበርሁ፣ ሁልጊዜ በፊቱ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ BSB BSB: Then I was a skilled craftsman at His side, and His delight day by day, rejoicing always in His presence.
31 ULB የእርሱ በሆነው በመላው ዓለም ደስ ይለኝ ነበር፣ ደስታየም በሰው ልጅ ነበር፡፡ BSB BSB: I was rejoicing in His whole world, delighting together in the sons of men.
32 ULB አሁንም፣ ልጆቼ ሆይ፣ አድምጡኝ፣ መንገዴን የሚጠብቁ ሁሉ ደስተኞች ይሆናሉና፡፡ BSB BSB: Now therefore, my sons, listen to me, for blessed are those who keep my ways.
33 ULB ምክሬን አድምጡ፣ ጥበበኞችም ሁኑ፤ ቸልም አትበሉት፡፡ BSB BSB: Listen to instruction and be wise; do not ignore it.
34 ULB እኔን የሚያደምጠኝ ደስተኛ ይሆናል፣ ዕለት በዕለት በመግቢያየ የሚተጋ፣ በቤቴም በሮች አጠገብ የሚጠብቀኝ፡፡ BSB BSB: Blessed is the man who listens to me, watching daily at my doors, waiting at the posts of my doorway.
35 ULB እኔን ያገኘ ሕይወትን ያገኛልና፣ የእግዚአብሔርንም ሞገስ ያገኛል፡፡ BSB BSB: For whoever finds me finds life and obtains the favor of the LORD.
36 ULB እኔን ያጣ ግን ራሱን ይጎዳል፤ እኔን የሚጠሉኝ በሙሉ ሞትን ይወድዳሉ፡፡ BSB BSB: But he who fails to find me harms himself; all who hate me love death.”
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.