1 ULB ልቤ መልካም ሐሳብ አፈለቀ ለንጉሡ የተቀኘሁትን ቅኔ አሰማለሁ አንደበቴ እንደ መልካም ጸሐፊ ብዕር ነው፡፡ BSB BSB: For the choirmaster. To the tune of “The Lilies.” A Maskil of the sons of Korah. A love song. My heart is stirred by a noble theme as I recite my verses to the king; my tongue is the pen of a skillful writer.
2 ULB አንተ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ ውብ ነህ ከከንፈሮችህ ጸጋ ይፈስሳል፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘላለም ባርኮሃል፡፡ BSB BSB: You are the most handsome of men; grace has anointed your lips; therefore God has blessed you forever.
3 ULB ኃያል ሆይ፣ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ ግርማ ሞገስንም ተላበስ BSB BSB: Strap your sword at your side, O mighty warrior; appear in your majesty and splendor.
4 ULB ስለ እውነት ስለ ፍትሕ ግርማን ተጐናጽፈህ ድል ለማድረግ ገሥግሥ ቀን እጅህ ድንቅ ነገር ታሳይ፡፡ BSB BSB: In your splendor ride forth in victory on behalf of truth and humility and justice; may your right hand show your awesome deeds.
5 ULB ፍላጻዎችን የሾሉ ናቸው ሕዝቦች ከእግርህ በታች ይወድቃሉ፡፡ ፍላጻዎችህ የንጉሡ ጠላቶችን ልብ ይወጋል፡፡ BSB BSB: Your arrows pierce the hearts of the king’s foes; the nations fall beneath your feet.
6 ULB አምላክ ሆይ፣ ዙፋንህ የዘላለም ዙፋን ነው በትረ መንግሥትህም የፍትሕ በትረ መንግሥት ነው፡፡ BSB BSB: Your throne, O God, endures forever and ever, and justice is the scepter of Your kingdom.
7 ULB ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃንም ጠላህ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ በደስታ ዘይት ቀባህ፡፡ BSB BSB: You have loved righteousness and hated wickedness; therefore God, your God, has anointed you above your companions with the oil of joy.
8 ULB ልብስህ ሁሉ ከከርቤ፣ ከእሬትና ከብርጉድ በተቀመመ ሽቱ ያውዳል፤ በዝሆን ጥርስ ከተዋቡ ቤተ መንግሥቶች የሚወጣ የበገናና የመሰንቆ ድምፅ ደስ ያሰኝሃል፡፡ BSB BSB: All your garments are fragrant with myrrh and aloes and cassia; from palaces of ivory the harps make you glad.
9 ULB በቤተ መንግሥትህ ከሚገኙ ወይዛዝርት መካከል፤ የነገሥታት ልጆች ይገኛሉ፤ ንግሥቲቱም በንጹሕ ወርቅ ያሸበረቀ ጌጤኛ ልብስ ተጐናጽፋ በቀኝህ በኩል ትቆማለች፡፡ BSB BSB: The daughters of kings are among your honored women; the queen stands at your right hand, adorned with the gold of Ophir.
10 ULB ልጄ ሆይ፣ አድምጪ አስተውይ፣ ጆሮሽንም አዘንብይ ሕዝብሽንና የአባትሽን ቤት እርሺ፡፡ BSB BSB: Listen, O daughter! Consider and incline your ear: Forget your people and your father’s house,
11 ULB ንጉሥ በውበትሽ ተማርኮአል እርሱ ጌታሽ ነውና አክብሪው፡፡ BSB BSB: and the king will desire your beauty; bow to him, for he is your lord.
12 ULB የጢሮስ ሴት ልጅ ስጦታ ይዛ ትመጣለች፤ ሀብታሞች ደጅ ይጠኑሻል፡፡ BSB BSB: The Daughter of Tyre will come with a gift; men of wealth will seek your favor.
13 ULB በቤተ መንግሥት ያለችው ልዕልት አጊጣለች ልብሷም በወርቅ አሸብርቋል፡፡ BSB BSB: All glorious is the princess in her chamber; her gown is embroidered with gold.
14 ULB ጌጠኛ ልብሷን ለብሳ ወደ ንጉሡ ትገባለች፤ ደናግል ጓደኞቿም አጅበዋት ወደ አንተ ይመጣሉ፡፡ BSB BSB: In colorful garments she is led to the king; her virgin companions are brought before you.
15 ULB በደስታና በሐሤትም አብረው ወደ ንጉሡ ቤት ይገባሉ፡፡ BSB BSB: They are led in with joy and gladness; they enter the palace of the king.
16 ULB ወንዶች ልጆችህ በአባቶችህ እግር ይተካሉ በምድር ሁሉ ላይ ገዦች አድርገህ ትሾማቸዋለህ፡፡ BSB BSB: Your sons will succeed your fathers; you will make them princes throughout the land.
17 ULB ስምህን በትውልድ ሁሉ ዘንድ ለመታሰቢያ አደርጋለሁ ስለዚህ ሕዝቦች ከዘላለም እስከ ዘላለም ይወድሱሃል፡፡ BSB BSB: I will commemorate your name through all generations; therefore the nations will praise you forever and ever.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.