1 ULB ዮሴፍን እንደ በግ መንጋ የምትመራ፣ የእስራኤል እረኛ ሆይ፣ ስማን፡፡ በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋን የምትቀመጥ ሆይ፣ ብርሃንህ ይብራልን! BSB BSB: For the choirmaster. To the tune of “The Lilies of the Covenant.” A Psalm of Asaph. Hear us, O Shepherd of Israel, who leads Joseph like a flock; You who sit enthroned between the cherubim, shine forth
2 ULB በኤፍሬም፣ በብንያምና በምናሴ ፊት ኃይልህን ግለጥ፤ መጥተህም አድነን፡፡ BSB BSB: before Ephraim, Benjamin, and Manasseh. Rally Your mighty power and come to save us.
3 ULB አምላክ ሆይ፣ መልሰን ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡ BSB BSB: Restore us, O God, and cause Your face to shine upon us, that we may be saved.
4 ULB የሰራዊት ጌታ ያህዌ ሆይ፣ በሕዝብህ ጸሎት ላይ የምትቆጣው እስከ መቼ ነው? BSB BSB: O LORD God of Hosts, how long will Your anger smolder against the prayers of Your people?
5 ULB የእንባ እንጀራ አበላሃቸው ስፍር የሞላ እንባም አጠጣሃቸው፡፡ BSB BSB: You fed them with the bread of tears and made them drink the full measure of their tears.
6 ULB የጐረቤቶቻችን መከራከሪያ አደረግኸን ጠላቶቻችንም ተሣሣቁብን፡፡ BSB BSB: You make us contend with our neighbors; our enemies mock us.
7 ULB የሰራዊት አምላክ ሆይ፣ ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡ BSB BSB: Restore us, O God of Hosts, and cause Your face to shine upon us, that we may be saved.
8 ULB የወይን ግንድ ከግብፅ አመጣህ አሕዛብን አባርረህ እርሷን ተከልህ፡፡ BSB BSB: You uprooted a vine from Egypt; You drove out the nations and transplanted it.
9 ULB መሬቱን መነጠርህላት፣ እርሷም ሥር ሰድዳ መሬቱን ሞላች፡፡ BSB BSB: You cleared the ground for it, and it took root and filled the land.
10 ULB ተራሮችም በጥላዋ ተሸፈኑ የቅርንጫፎቿም ጥላ የሊባኖስን ዛፎች ሸፈነ፡፡ BSB BSB: The mountains were covered by its shade, and the mighty cedars with its branches.
11 ULB ቅርንጫፎቿን እስከ ባሕሩ ቁጥቋጦዋንም እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ዘረጋች፡፡ BSB BSB: It sent out its branches to the Sea, and its shoots toward the River.
12 ULB ታዲያ፣ አላፊ፣ አግዳሚው ፍሬዋን እንዲቀጥፍ በዙሪያዋ የነበሩ አጥሮችን ለምን አፈረስህ፡፡ BSB BSB: Why have You broken down its walls, so that all who pass by pick its fruit?
13 ULB የዱር አሳማ ያበላሻታል በሜዳ የሚንጋጋም አራዊት ይበላታል፡፡ BSB BSB: The boar from the forest ravages it, and the creatures of the field feed upon it.
14 ULB የሰራዊት አምላክ ሆይ፣ ወደ እኛ ተመለስ፣ ከሰማይ ተመልከት እይም ይህችን የወይን ተክልም ተንከባከባት፡፡ BSB BSB: Return, O God of Hosts, we pray! Look down from heaven and see! Attend to this vine—
15 ULB ይህች ቀኝ እጅህ የተከላት ተክል አንተም ያጸደቅሃት ተክል ናት፡፡ BSB BSB: the root Your right hand has planted, the son You have raised up for Yourself.
16 ULB ነገር ግን ቆራርጠው በእሳት አቃጠሏት ከቁጣህ የተነሣ ይጠፋሉ፡፡ BSB BSB: Your vine has been cut down and burned; they perish at the rebuke of Your countenance.
17 ULB እጅህ የቀኝ እጅህ የሆነው ሰው ላይ፣ አንተ ራስህ ብርቱ ያደረግኸው የሰው ልጅ ላይ ትሁን BSB BSB: Let Your hand be upon the man at Your right hand, on the son of man You have raised up for Yourself.
18 ULB እኛም ከአንተ ወደ ኋላ አንልም፤ በሕይወት ጠብቀን፤ እኛም ስምህን እንጠራለን፡፡ BSB BSB: Then we will not turn away from You; revive us, and we will call on Your name.
19 ULB ሰራዊት አምላክ ያህዌ ሆይ፣ መልሰን ፊትህን አብራልን እኛም እንድናለን፡፡ BSB BSB: Restore us, O LORD God of Hosts; cause Your face to shine upon us, that we may be saved.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.