1 ULB ሰባቱን መላእክት፣ “ሂዱና ሰባቱን የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች ምድር ላይ አፍስሱ” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሲወጣ ሰማሁ። BSB BSB: Then I heard a loud voice from the temple saying to the seven angels, “Go, pour out on the earth the seven bowls of God’s wrath.”
2 ULB የመጀመሪያው መልአክ ጽዋውን ምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬው ምልክት ባላቸውና ለምስሉ በሰገዱት አስከፊና የሚያሠቃይ ቁስል ወጣባቸው። BSB BSB: So the first angel went and poured out his bowl on the earth, and loathsome, malignant sores broke out on those who had the mark of the beast and worshiped its image.
3 ULB ሁለተኛው መልአክ ጽዋውን ባሕር ላይ አፈሰሰ፤ ባሕሩ እንደ ሞተ ሰው ደም ሆነ፤ ባሕር ውስጥ የነበረ ሕያው ፍጡር ሁሉ ሞተ። BSB BSB: And the second angel poured out his bowl into the sea, and it turned to blood like that of the dead, and every living thing in the sea died.
4 ULB ሦስተኛው መልአክ ጽዋውን ወንዞችና የውሃ ምንጮች ላይ አፈሰሰ እነርሱም ደም ሆኑ። BSB BSB: And the third angel poured out his bowl into the rivers and springs of water, and they turned to blood.
5 ULB የውሃውም መልአክ፣ “ያለህና የነበርህ ቅዱስ ጌታ እንዲህ ስለ ፈረድህ ትክክል ነህ፣ BSB BSB: And I heard the angel of the waters say: “Righteous are You, O Holy One, who is and was, because You have brought these judgments.
6 ULB ምክንያቱም የቅዱሳንህና የነበያትን ደም ስላፈሰሱ፣ ደም አጠጣሃቸው፤ ይህም የሚገባቸው ነው” ሲል ሰማሁ። BSB BSB: For they have spilled the blood of saints and prophets, and You have given them blood to drink, as they deserve.”
7 ULB ከመሠዊያውም፣ “አዎን፣ ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ፍርድህ እውነትና ትክክል ነው” የሚል ድምፅ ወጣ። BSB BSB: And I heard the altar reply: “Yes, Lord God Almighty, true and just are Your judgments.”
8 ULB አራተኛው መልአክ ጽዋውን ፀሐይ ላይ አፈሰሰ፤ ለእርሷም ሰዎችን በግለትዋ የማቃጠል ሥልጣን ተሰጣት። BSB BSB: Then the fourth angel poured out his bowl on the sun, and it was given power to scorch the people with fire.
9 ULB ሰዎች በከባድ ሙቀቷ ተቃጠሉ፤ በእነዚህ መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔር ስም ሰደቡ። ንሰሐ አልገቡም፤ ክብርም አልሰጡትም። BSB BSB: And the people were scorched by intense heat, and they cursed the name of God, who had authority over these plagues. Yet they did not repent and give Him glory.
10 ULB አምስተኛው መልአክ ጽዋውን በአውሬው ዙፋን ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም መንግሥት በጨለማ ተዋጠ። ከሥቃያቸውም የተነሣ ምላሳቸውን ያኝኩ ነበር። BSB BSB: And the fifth angel poured out his bowl on the throne of the beast, and its kingdom was plunged into darkness, and men began to gnaw their tongues in anguish
11 ULB ከሥቃያቸውና ከደረሰባቸው ቁስል የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፤ ያም ሆኖ ግን ስላደረጉት ክፉ ሥራ ንስሐ ለመግባት ፈቃደኞች አልሆኑም። BSB BSB: and curse the God of heaven for their pains and sores. Yet they did not repent of their deeds.
12 ULB ስድስተኛው መልአክ ጽዋውን ታላቁ ወንዝ ኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለመጡ ነገሥታት መንገድ ለማዘጋጀት የወንዙ ውሃ ደረቀ። BSB BSB: And the sixth angel poured out his bowl on the great river Euphrates, and its water was dried up to prepare the way for the kings of the East.
13 ULB ከዘንዶው አፍና ከአውሬው አፍ እንዲሁም ከሐስተኛው ነቢይ አፍ እንቁራሪት የሚመስሉ ሦስት ርኩሳን መናፍስት ስወጡ አየሁ። BSB BSB: And I saw three unclean spirits that looked like frogs coming out of the mouths of the dragon, the beast, and the false prophet.
14 ULB እነዚህ ተአምራዊ ምልክቶች የሚያደርጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸው። ሁሉን በሚገዛ አምላክ ታላቅ ቀን ለሚደረገው ጦርነት የዓለም መንግሥታችን ሁሉ ለመሰብሰብ ወደ ወጥተው ሄዱ። BSB BSB: These are demonic spirits that perform signs and go out to all the kings of the earth, to assemble them for battle on the great day of God the Almighty.
15 ULB “ልብ በሉ! እኔ እንደ ሌባ እመጣለሁ! ራቁቱን እንዳይገኝና ሰዎችም ሐፍረቱን እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ የተባረከ ነው።” BSB BSB: “Behold, I am coming like a thief. Blessed is the one who remains awake and clothed, so that he will not go naked and let his shame be exposed.”
16 ULB መናፍስቱ ነገሥታቱን ሰብስበው በዕብራይስጥ አርማጌደን ወደሚባል ቦታ አመጧቸው። BSB BSB: And they assembled the kings in the place that in Hebrew is called Armageddon.
17 ULB ሰባተኛው መልአክ ጽዋውን አየር ላይ አፈሰሰ። በዚያን ጊዜ፣ “ተፈጸመ!” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱና ከዙፋኑ ወጣ። BSB BSB: Then the seventh angel poured out his bowl into the air, and a loud voice came from the throne in the temple, saying, “It is done!”
18 ULB ከዚያም የመብረቅ ብልጥታ፣ ሁካታ ነጎድጓድና ከባድ የመሬት መናወጥ ሆነ፤ የዚያ ዓይነት የምድር ነውጥ የሰው ልጅ ምድር ላይ መኖር ከጀመረ አንሥቶ ሆኖ የማያውቅ እጅግ ከባድ ነበር። BSB BSB: And there were flashes of lightning, rumblings, peals of thunder, and a great earthquake the likes of which had not occurred since men were upon the earth—so mighty was the great quake.
19 ULB ታላቂቷ ከተማ ለሦስት ተከፈለች፤ የሕዝቦች ከተሞችም ተደመሰሱ። እግዚአብሔር ታላቂቱ ባቢሎንን አስታወሰ፤ ለዚያች ከተማም የብርቱ ቁጣው ወይን ጠጅ የሞላበት ጽዋ እንድትጠጣ ሰጣት። BSB BSB: The great city was split into three parts, and the cities of the nations collapsed. And God remembered Babylon the great and gave her the cup of the wine of the fury of His wrath.
20 ULB ደሴቶች ሁሉ ጠፋ፤ ተራሮችም በቦታቸው አልተገኙም። BSB BSB: Then every island fled, and no mountain could be found.
21 ULB አንድ ታለንት የሚመዝን የበረዶ ድንጋይ ከሰማይ ወርዶ ሰዎች ላይ ወደቀ፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሰቃቂ ከመሆኑ የተነሣ ሰዎች ስለ በረዶው ድንጋይ እግዚአብሔርን ተራገሙ። BSB BSB: And great hailstones weighing almost a hundred pounds each rained down on them from above. And men cursed God for the plague of hail, because it was so horrendous.
Select verses for actions: Enter goes to them and Escape comes back.